Thursday, June 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊየመጀመርያው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ በኢትዮጵያ

የመጀመርያው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ በኢትዮጵያ

ቀን:

የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ግለሰብ ኢትዮጵያ ውስጥ ለመጀመወያ ጊዜ መገኘቱን፣ ዓርብ መጋቢት 4 ቀን 2012 ዓ.ም. ማረጋገጣቸው ይታወሳል፡፡ የ48 ዓመቱ የጃፓን ዜጋ የካቲት 25 ቀን 2012 ዓ.ም. ከቡርኪናፋሶ ወደ አዲስ አበባ ከመጣ በኋላ፣ በተዘረጋው የቅኝት መስመር መሠረት ኢትዮጵያ የመጀመርያውን ተጠቂ ለመለየት መቻሏ ተገልጿል፡፡ ከበሽተኛው ጋር የቅርብ ንክኪ የነበራቸው 25 ግለሰቦችም ተለይተው ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑ፣ በጋዜጣዊ መግለጫው ወቅት ተወስቷል፡፡ ታማሚውም አስቀድሞ በተዘጋጀው የለይቶ ማከሚያ ተገቢው የሕክምና ክትትል እየተደረገለት መሆኑን፣ እስካሁንም ባለው ሁኔታ የከፋ የጤና እክል እንዳልገጠመው ተነግራል፡፡ የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መንግሥት የበሽታውን ሥርጭት ለመግታትና ለመቆጣጠር ተገቢውን ዕርምጃ እየወሰደ መሆኑን እንደሚያረጋግጡ በመግለጽ፣ ማኅበረሰቡ የመከላከያ መንገዶችን ችላ ሳይልና ሳይደናገጥ ተግባር ላይ በማዋል የበሽታውን ሥርጭት ለመግታት የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል። መረጃዎችን ከአስተማማኝ ምንጮች ብቻ በመቀበል የተሳሳቱ መረጃዎች የሚያስከትሉትን መደናገርና ፍርኃት መከላከል እንደሚገባም ማሳሰቢያ ተሰጥቷል፡፡ የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰና የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ኤባ አባተ፣ ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ የተነሱ ዋና ዋና ጉዳዮችን በገጽ 16 ላይ ይመልከቱ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...