Tuesday, April 16, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበኮሮና ቫይረስ ሥርጭት ሥጋት በአዲስ አበባ የሚገኙ በርካታ ዓለም አቀፍ ተቋማት መሥሪያ...

በኮሮና ቫይረስ ሥርጭት ሥጋት በአዲስ አበባ የሚገኙ በርካታ ዓለም አቀፍ ተቋማት መሥሪያ ቤቶቻቸውን እየዘጉ ነው

ቀን:

የምርጫ ቦርድ የቴክኒክ ድጋፍ ሰጪ ከቫይረሱ ነፃ ሆነ

የኮሮና ቫይረስ ቀስ በቀስ እየተዛመተ በመምጣቱና በኢትዮጵያም የቫይረሱ መገኘት ያሳሰባቸው የውጭ ተቋማት፣ መሥሪያ ቤቶቻቸውን በመዝጋት ላይ ናቸው፡፡

ሪፖርተር እንዳረጋገጠው ከሆነ የዓለም ባንክን ጨምሮ በርካታ የውጭ ድርጅቶችና ኤምባሲዎች ቢሮዎቻቸውን በመዝጋት፣ ሠራተኞቻቸውን ከቤት ሆነው እንዲሠሩ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ ለቅድመ ጥንቃቄ ሲባል እየተወሰዱ የሚገኙ እንዲህ ያሉት ዕርምጃዎች፣ የኮሮና ቫይረስ ሥርጭትን ለመግታት ከሚያስችሉ ቅድመ ጥንቃቄዎች መካከል ታሳቢ በመደረጋቸው ነው፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በመሆኑም በርካቶች ሠራተኞቻቸው ወደ መሥሪያ ቤት ሄደው ከመሥራት እንዲታቀቡ እያደረጉ ሲሆን፣ ጥቂት የማይባሉትም ከዋና መሥሪያ ቤቶቻቸው የሚመጡ ትዕዛዞችን እየተጠባበቁ ነው፡፡

በኮሮና ቫይረስ ምልክቶች በመጠርጠሩ ምርመራ የተደረገለት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የቴክኒክ ድጋፍ ሰጪ የውጭ አገር ባለሙያ፣ ከቫይረሱ ነፃ መሆኑ ተገለጸ፡፡ ምርጫ ቦርድ ለቅድመ ጥንቃቄ ሲል ሠራተኞቹ ከቤታቸው ሆነው ሥራቸውን እንዲያከናውኑ ሰኞ መጋቢት 7 ቀን 2012 ዓ.ም. መወሰኑ ይታወሳል፡፡ ግለሰቡ ከቫይረሱ ነፃ መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ፣ ቦርዱ በይፋ ሥራ መጀመሩን አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ይፋ እንዳደረገው፣ በአሁኑ ወቅት ስድስት ግለሰቦች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፡፡ ኢንስቲትዩቱ በዚሁ ቀን ይፋ ባደረገው መሠረት በሽታው መኖሩ ሪፖርት ከተደረገባቸው አገሮች የመጡ ተጓዦችን ጨምሮ በኮሮና ቫይረስ ከተያዙት ስድስቱ ግለሰቦች ጋር የቅርብ ንክኪ የነበራቸው 992 ግለሰቦች፣ በያሉበት ቦታ 14 ቀናት ተለይተው የጤና ክትትል እየተደረገላቸው ናቸው፡፡ ሌሎች 1,285 ግለሰቦችም 14 ቀናት የጤና ክትትል ሲደረግላቸው ቆይተው ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው በመረጋገጡ የጤና ክትትላቸው እንዲቋረጥ መደረጉ ተገልጿል፡፡

ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው ምልክቶችን በማሳየታቸውና ከመጀመሪያው ታማሚዎች ጋር ንክኪ የነበራቸውን ጨምሮ በአሁኑ ወቅት 113 ተጠርጣሪዎች በተለያዩ ጊዜያት በለይቶ መቆያ ማዕከል እንዲቆዩ ሲደረግ፣ የላብራቶሪ ምርመራ ውጤታቸው ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው በመረጋገጡ ከእነዚህ ውስጥ 74 ሰዎች ወደ መደበኛው ኑሯቸው እንዲመለሱና ከኅብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ መደረጋቸውን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ኤባ አባተ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

ይህም ሆኖ 34 ተጠርጣሪዎች በለይቶ ማቆያ ውስጥ ሆነው የላቦራቶሪ ምርመራ ውጤታቸው እስኪደርስ እየተጠበቀ ይገኛሉ ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፣ አምስቱ የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች በጥሩ የጤንነት ሁኔታ ላይ እንደሚገኙም አስታውቀዋል፡፡ ቀስ በቀስ በአፍሪካ አገሮች እየተስፋፋ የመጣው የኮሮና ቫይረስ፣ ከወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ ወደ 30 አገሮች በመዛመት 420 ገደማ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች እንዳሉ ተረጋግጧል፡፡

የበሽታውን መስፋፋት ከወዲሁ ለመግታትና ሥርጭቱን ለመከታተል ይረዳ ዘንድ የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ፣ ትልልቅ ስብሰባዎችና ስፖርታዊ ክንወኖች ለ15 ቀናት እንዲዘጉ መንግሥት መወሰኑ ይታወቃል፡፡ እንደ ኢትዮጵያ ሁሉ ሌሎችም የአፍሪካ አገሮች ተመሳሳይ ዕርምጃዎችን መውሰድ የጀመሩ ሲሆን፣ ለዚህም ሩዋንዳ ተጠቃሽ ነች፡፡ በሩዋንዳ ከጥቂት ቀናት በፊት አምስት ብቻ የነበሩት የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች እስከ መጋቢት 8 ቀን 2012 ዓ.ም. በነበረው መረጃ መሠረት 15 መድረሳቸውን የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ጽሕፈት ቤት ይፋ አድርጓል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም...

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...