Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየሦስት ጎረቤት አገሮች መሪዎች የዓባይ ተፋሰስ አገሮች በውኃው የመጠቀም መብት መረጋገጥ አለበት...

የሦስት ጎረቤት አገሮች መሪዎች የዓባይ ተፋሰስ አገሮች በውኃው የመጠቀም መብት መረጋገጥ አለበት አሉ

ቀን:

የዓባይ ውኃና የህዳሴ ግድብን ውዝግብን በተመለከተ የግብፅ መንግሥት የሚያራምደውን አቋም በመንቀፍ፣ ሁሉም የዓባይ ተፋሰስ አገሮች በተፈጥሮ ሀብታቸው የመጠቀም መብታቸው መረጋገጥ እንዳለበት የሩዋንዳ፣ኡጋንዳናኬንያ መሪዎች አሳሰቡ። ኡጋንዳ የተፋሰሱ አገሮች መሪዎች አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ ጠይቃለች፡፡

መሪዎቹ የመንግሥቶቻቸውን አቋም በተናጠል በመግለጽ የዓባይ ተፋሰስ አገሮች በውኃው የመጠቀም መብት እንዳላቸው አስረግጠው የተናገሩት፣ በፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለተመራው የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ልዑክ ነው።

የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ ልዑካን በመምራት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በሦስቱ አገሮች ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ያደረጉት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ፣ በኢትዮጵያና በግብፅ መካከል ህዳሴ ግድቡን አስመልክቶ ስለተፈጠረው ውዝግብ ለመሪዎቹ ማስረዳታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሪፖርተር ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

መጋቢት 3 ቀን 2012 ዓ.ም. ከኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጋር የተገናኙት ፕሬዚዳንቷ፣ በመቀጠል ከኡጋንዳ ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ፣ ሰኞ መጋቢት 7 ቀን 2012 ዓ.ም. ደግሞ ከሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ ጋር ተወያይተዋል። ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ የህዳሴ ግድቡን በተመለከተለተፈጠረው ውዝግብና የኢትዮጵያን መንግሥት የትብብር አቋም ያስረዱ ሲሆን፣ ፕሬዚዳንት ካጋሜም የኢትዮጵያን ጥረት ማድነቃቸው ታውቋል።

ሁለቱ መሪዎች ባደረጉት ውይይት ወቅትም፣ በዓባይ ተፋሰስ አገሮች መካከል የሚደረገው የትብብር እንቅስቃሴ ከሁሉ በፊት ቴክኒካዊ ለሆኑ ጉዳዮች ቅድሚያ መስጠት እንዳለበት፣ የሚደረጉ ትብብሮችም በዚህ ላይ የተመሠረቱ ሊሆኑ እንደሚገባ የሩዋንዳ ፕሬዚዳንት ማሳሰባቸውን የተገኘ መረጃ ያመለክታል።

ፕሬዚዳንት ካጋሜ በቴክኒክ ባለሙያዎች የሚቀርቡ ሳይንሳዊ ትንተናዎች እስከተያዙ ድረስ፣ ውጤቱም የጋራ ፍላጎትን የሚያንፀባርቅ እንደሚሆን መግለጻቸውን  መረጃው ያመለክታል።

‹‹ከመርህ አንፃርም በግብፅ በኩል ወንዙ የህልውና ጉዳይ ተደርጎ የሚነሳውን ያህል፣ የሌሎች የተፋሰሱ አገሮች በዓባይ ውኃ የመጠቀምና የመልማት ተፈጥሯዊ መብትም ዕውቅና ሊሰጠው ይገባል፤›› ሲሉ የመንግሥታቸውን አቋም እንደገለጹ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርተገኘው መረጃ ለመረዳት ተችሏል።

በዓባይ ወንዝ አጠቃቀም ላይ የሚነሱ አለመግባባቶች በአፍሪካውያን የውይይትና የድርድር መድረኮች ሊፈቱ እንደሚገባ፣ ለዚህም ስኬታማነት አገራቸው የሚጠበቅባትን አስተዋጽኦ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን ፕሬዚዳንት ካጋሜ ገልጸዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በኡጋንዳ ባደረጉት ተመሳሳይ ጉብኝት፣ ከፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ጋር ተገናኝተው በህዳሴ ግድቡ ላይ መክረዋል። ፕሬዚዳንት ሙሴቬኒ ኡጋንዳ የዓባይ ወንዝ የትብብር ማዕቀፍን ማፅደቋን ለፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ገልጸው፣ ይህም በዓባይ ውኃ ላይ የተፋሰሱ አገሮች ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ሊኖራቸው ይገባል የሚለውን የመንግሥታቸውን አቋም እንደሚያንፀባርቅ አመልክተዋል።

የህዳሴ ግድብን በተመለከተ የተፈጠረው ውዝግብ በአፍሪካዊ መንፈስውይይት ሊፈታ እንደሚገባ የገለጹት ፕሬዚዳንት ሙሴቬኒ፣ ይህንንም ለማመቻቸት የናይል ቤዚን ኢንሼቲቭ አስቸኳይ የሚኒስትሮች ስብሰባ እንዲጠራና በዚህ ሥር ያሉ አገሮች መሪዎች ተሰብስበው ሊነጋገሩ ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በበኩላቸው፣ የአፍሪካ አገሮች የሕዝባቸውን ፍላጎቶች ለማሟላት የተፈጥሮ ሀብታቸውን ምክንያታዊና ፍትሐዊ መርሆች ላይ በመመሥረት በዘላቂነት ሊያለሙ እንደሚገባ መናገራቸው ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...