Friday, January 27, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትፌዴሬሽኖች ብሔራዊ ዝግጅቶችን ጨምሮ ውድድሮችን አቋረጡ

ፌዴሬሽኖች ብሔራዊ ዝግጅቶችን ጨምሮ ውድድሮችን አቋረጡ

ቀን:

የቻይና ግዛት በሆነችው ውሃን ከተማ የተከሰተው ኮሮና ቫይረስ በዓለም ዙሪያ በመስፋፋቱ እያስከተለ ያለው ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እንደቀጠለ ነው፡፡ አሁን ላይ አገሮች ዜጎቻቸው ከአገር አገር አይደለም በአካባቢያቸው ከቦታ ቦታ እንኳ እንዳይንቀሳቀሱ ገደብ እንዲጥሉ አስገድዷቸዋል፡፡ የዓለም ሥጋት ሆኖ የቀጠለው ኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ ባለፈው ዓርብ መጋቢት 4 ቀን 2012 ዓ.ም. መከሰቱ ከተረጋገጠ በኋላ ትምህርት ቤቶች፣ ሰዎች በርከት ብለው የሚገናኙባቸው እግር ኳሳዊና መሰል እንቅስቃሴዎችና ሕዝባዊ ስብሰባዎች ለሁለት ሳምንታት ዝግ ሆነው እንዲቆዩ በመንግሥት ተወስኗል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በየደረጃው የሚያወዳድራቸው ሊጎችም እንዲቋረጡ ሲደረግ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በበኩሉ በሐምሌ በጃፓን ቶኪዮ ለሚከናወነው ኦሊምፒክና ከወር በኋላ በቶጎ ለሚካሄደው የአፍሪካ አገር አቋራጭ ሻምፒዮና እያዘጋጃቸው የሚገኙ ብሔራዊ አትሌቶች ከሆቴል ወጥተው በግላቸው ዝግጅት እንዲያደርጉ ማድረጉ ታውቋል፡፡

ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ባለፈው ሰኞ መጋቢት 7 ቀን 2012 ዓ.ም. ጉርድ ሾላ በሚገኘው ጽሕፈት ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ለስድስተኛው የአፍሪካ አገር አቋራጭ ከየካቲት 12 ቀን ጀምሮ ብሔራዊ አትሌቶች በሆቴል ተሰባስበው ሥልጠና ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ ይሁንና የአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን (ሲኤኤ) ዘንድሮ የሚያከናውነው ስድስተኛው የአፍሪካ አገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ወደ ሚቀጥለው ዓመት ማዘዋወሩን መጋቢት 3 ቀን 2012 ዓ.ም. ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑም ይህንኑ ውሳኔ ተከትሎ ብሔራዊ አትሌቶች ከሆቴል እንዲወጡ ስለመደረጉ ጭምር ተናግሯል፡፡ ለቶኪዮ ኦሊምፒክ ዝግጅት የጀመሩ አትሌቶችም በግላቸው እንዲሠሩ ተደርጓል፡፡

በሌላ በኩል በቅርቡ አትሌቲክስ ኢንቴግሪቲ ዩኒት የተሰኘ ተቋም ይፋ ባደረገው ዘገባው፣ ኢትዮጵያ 2020 የውድድር ዓመት በስፖርት አበረታች ቅመሞች (ዶፒንግ) ጉዳይ ጋር ተያይዞ ለስፖርቱ ሥጋት ከሚባሉ አገሮች “ኤ” ወይም ከመጀመሪያዎች ተርታ ማስቀመጡ ይታወሳል፡፡ ይህ በተለይ ለአትሌቲክሱ ቤተሰብ ትልቅ ሥጋት ፈጥሮ ሲያነጋግር መቆየቱ የሚዘነጋ አይደለም፡፡

ኢትዮጵያ በስፖርት አበረታች ቅመሞች ጋር ስሟ ተያይዞ ሥጋት ከሆኑ አገሮች ተርታ ገብታለች ሲባል ምን ማለት እንደሆነ የኢትዮጵያ የፀረ አበረታች ቅመሞች ብሔራዊ ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎችና ሙያተኞች በዕለቱ በነበረው ጋዜጣዊ መግለጫ ተገኝተው ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

“ኢትዮጵያ በኤ ምድብ እንድትቀመጥ አንዱና የመጀመሪያው መነሻ በጎዳናና በረዥም ርቀት ውድድሮች በውጤት ዓለም ላይ ካሉ ጥቂት አገሮች አንዷ ነች፡፡ በዚሁ ርቀት ውጤታማ አትሌቶች በብዛት የሚገኝባቸው አገሮች ማለትም ምሥራቅ አፍሪካዊቷ ኬንያን ጨምሮ ሌሎችም አገሮች ምድባቸው “ኤ” ናቸው ሲባል ተጠርጣሪ አገሮች ሆኑ ማለት አይደለም፡፡ መረጃውን ያሠራጨው ተቋም መነሻ ይህ ነው፣” በማለት የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ መኮንን ይደርሳል ብዥታው መጥራት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

ስፖርቱ አሁን ካለበት ደረጃ በመነሳት ለአበረታች ቅመሞች ተጋላጭነቱ የሚያጠያይቅ እንዳልሆነ ያከሉት ኃላፊው፣ በዓለም አትሌቲክስ ከፍተኛ ደረጃ አትሌቶች ብዛት ከ30 እስከ 50 ያለው አገር ከሆነ የምርመራ ቋት ውስጥ ማለፍ የግድ እንደሚልም ተናግረዋል፡፡ ይህ ኢትዮጵያውያውያን ባይመለከትም በመስፈርትነት ግን ሊቀመጥ ግድ ስለመሆኑ ጭምር ተናግረዋል፡፡

እ.ኤ.አ በ2019 በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕግድ ከተጣለባቸው አትሌቶች የአገሮች ዝርዝር ይፋ ሲሆን ኢትዮጵያ በጣም አነስተኛ ካሏቸው አንዷ እንደነበረች ያብራሩት ኃላፊው፣ ለዚህ ዋናው ምክንያት በጎዳና ውድድሮች ውጤታማ የሆኑ 85 በመቶ አትሌቶች መገኛ መሆኗ በመስፈርቱ ውስጥ እንደምትገኝም መናገራቸው በመግለጫው ተካቷል፡፡

በስፖርቱ ቤተሰብ ዘንድ ያለው ግንዛቤ ኢትዮጵያ በስፖርት አበረታች ቅመሞች ችግር ውስጥ እንዳለች አድርጎ መቁጠር ተገቢ እንዳልሆነ ያብራሩት ደግሞ የፌዴሬሽኑ የሕክምና ባለሙያ አያሌው ጥላሁን (ዶ/ር) እና ወ/ት ቅድስት ታደሰ፣ “እንዲህ ዓይነቱ አስተሳሰብ ስህተት ነው፡፡ ምክንያቱም የዓለም አቀፍ የፀረ አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ (ዋዳ) በ2019 ኢትዮጵያ ኮድ ኮምፕሊያንት ተብላ የተመረጠች መሆኗ፣ ይህ ሲባልም በዓመቱ ውስጥ የተሠሩ ሥራዎች በማስረጃ በማስደገፍ በወጉ ማቅረብን የሚይዝ ነው፣” በማለት ጉዳዩን ለማብራራት መሞከራቸው በመግለጫው ተኳቷል፡፡     

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቅዱስ ሲኖዶስ ሦስቱን ጳጳሳት ስልጣነ ክህነታቸውን አንስቶ አወገዘ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ሰሞኑን ጥር 14...

አቶ እየሱስወርቅ ዛፉ ከህብረት ባንክ ቦርድ አባልነት ለቀቁ

አንጋፋው የፋይናንስ ባለሙያ አቶ እየሱስወርቅ ዛፉ ከህብረት ባንክ ቦርድ...

አቶ በረከት ስምኦን ከእስር ተፈቱ

ከአራት ዓመታት በፊት በተከሰሱበት በከባድሙስና ወንጀል ስድስት ዓመታት ተፈርዶባቸው...

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ ቢሯቸው እንደገቡ የፖለቲካ አማካሪያቸው ስለ ሰሜኑ ግጭት የሰላም ስምምነት አተገባበር ማብራሪያ ለመጠየቅ ገባ]

ክቡር ሚኒስትር ጥሰውታል? እንዴ? እስኪ ተረጋጋ ምንድነው? መጀመርያ ሰላምታ አይቀድምም? ይቅርታ...