Wednesday, May 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዓለምኮሮና ቫይረስ በፖለቲከኞችና ዝነኞች ቤት

ኮሮና ቫይረስ በፖለቲከኞችና ዝነኞች ቤት

ቀን:

በዓለም ደረጃ ሥጋት የሆነው ኖቭል ኮሮና ቫይረስ ደሃ ከሀብታም፣ ባለሥልጣን ከተርታው፣ ተዋናይ ከተመልካቹ እንዲሁም ስፖርተኞች ሳይል ሁሉንም አዳርሷል፡፡ ለወትሮ አንድ ወረርሽኝ ተከሰተ ሲባል አፍሪካና እስያ ብሎም ላቲን አሜሪካ ቀድመው የሚጠሩ ቢሆንም፣ የዛሬው ግን ባለሀብቱን ከደሃው ታዋቂውን ከጎጋው አልለየም፡፡

የችግሩ ተጋላጮች ተብለው በድህነታቸው ምክንያት ለበሽታው ይበልጥ ተጋላጭ ሊሆኑ ይችላሉ የተባሉ የአፍሪካ አገሮችም እስከ ትናንት ባለው መረጃ ከአውሮፓ የተሻለ የመቋቋም ኃይልን አሳይተዋል፡፡ እስካሁንም በአኅጉሪቱ የተከሰተው ሞትም ሆነ መጠነ መያዝ በየአገሮቹ ቁጥጥሩን አስቀጥሎ መሄድ ከተቻለ ተስፋ የሚሰጥ ነው፡፡

 በሌላ በኩል ደግሞ አድገዋል፣ ሠልጥነዋል በሚባሉ አገሮች የሚታየው የቫይረሱ ሥርጭት ግን ይኖራቸዋል ተብሎ ከሚገመተው የመቋቋም አቅም ተቃራኒ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ዕድሜያቸው የገፋ የማኅበረሰብ ክፍሎች በአደጉ አገሮች መኖራቸው አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡

- Advertisement -

ከዚሁ ጎን ለጎንም ይህንንም ያህል እንደ ደሃው የኅብረተሰብ ክፍል ይጋለጣሉ ተብለው የማይጠበቁ ግለሰቦች በቫይረሱ ተጠቅተዋል፡፡ አልጀዚራ እንዳሰፈረው፣ ታላላቅ ባለሥልጣናት፣ ዝነኞችና ስፖርተኞች በቫይረሱ ተጠቅተዋል፡፡

በ146 አገሮች የተሠራጨውና ከ7,000 በላይ የገደለው ቫይረስ፣ በዓለም ደረጃ በአጠቃላይ ያጠቃው 175,000 ያህል ሰዎችን ነው፡፡ ከእነዚህ ውስጥ የሆሊውድ ተዋናይ ቶም ሃንክሰን እና ባለቤቱ ተዋናይትና አቀንቃኝ ሪታ ዊልሰን፣ የብሪታኒያ ተዋናይ ኢድሪስ ኢልባ፣ የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ባለቤት ሶፊ ትሩዶ ይገኙበታል፡፡

የጃፓን እግር ኳስ ማኅበር ፕሬዚዳንትና የኦሊምፒክ ኮሚቴ ምክትል ሊቀመንበር ኮዞ ታሺማ በስፖርቱ ዘርፍ በቫይረሱ ከተጠቁት ሲገኙበት፣ በኮሮና ቫይረስ በመያዝ የመጀመርያዋ የእንግሊዝ ባለሥልጣን ናዲያን ዶሪስ ናቸው፡፡ ናዲያን ዶሪስ የእንግሊዝ የጤና ሚኒስትር ሲሆኑ፣ በቫይረሱ መያዛቸው የተገለጸው ከሳምንት በፊት ነበር፡፡

የአውስትራሊያ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ፒተር ዱቶን እንዲሁም የኢራን ምክትል ፕሬዚዳንት ማሾሜህ ኢብትካር በቫይረሱ ከተያዙ ትልልቅ ባለሥልጣናት ይጠቀሳሉ፡፡

ኮሮና ቫይረስ በፖለቲከኞችና ዝነኞች ቤት

ስፔን ከስድስት ሺሕ በላይ ሰዎች በቫይረሱ በመያዛቸው ድንበሯን ዘግታለች፡፡ ከተራው ሕዝብ ባለፈም የስፔን ጠቅላይ ሚኒስትር ባለቤት ቦኛ ጎሜዝም ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፔድሮ ጎንቼዝም ሆነ የባለቤታቸው ጤና በጥሩ ሁኔታ እንደሚገኝም ዘገባው ያሳያል፡፡ በስፔን የካታሎኒያ ክልል መሪ ዄይም ቶራ በቫይረሱ ከተያዙ ባለሥልጣናት አንዱ ናቸው፡፡ የካታሎኒያ ምክትል ገዥ ፒር አራጎኔስም በቫይረሱ ተጠቅተዋል፡፡

የኮቪድ 19ኝን ሥርጭት ለመገምገም የአገሪቱን እንቅስቃሴ በከፊል ያገደችው ፈረንሣይ፣ የጤና ሚኒስትሯ በበሽታው ተይዘዋል፡፡

ፋቢዩ ዋጃንጋርተን፣ የብራዚል ፕሬዚዳንት ጄር ቦልሶናሮ ዋና አማካሪ ናቸው፡፡ እኚህ ሰው አሜሪካ ተጉዘውና ከፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር መክረው አገራቸው ሲመለሱ ባደረጉት ምርመራ ቫይረሱ እንዳለባቸው ተረጋግጧል፡፡

የእሳቸውን በቫይረሱ መያዝ የሰሙ መገናኛ ብዙኃን፣ ፕሬዚዳንት ትራምፕ መመርመር አለባቸው የሚሉ ዘገባዎችን ባለፈው ሳምንት ሲያሠራጩ ነበር፡፡ ባለፈው ዓርብ ምሽት መግለጫ የሰጡት ትራምፕ ለምርመራ ናሙና ሰጥተው እንደነበር የገለጹ ሲሆን፣ በኋላ ላይ የወጡ መረጃዎች ፕሬዚዳንቱ ከቫረሱ ነፃ መሆናቸውን አመላክተዋል፡፡

የፖላንድ የአየር ንብረት ሚኒስትር ማይክል ዎስ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሌላው ባለሥልጣን ናቸው፡፡ በፖርቱጋል በተዘጋጀ የሥነ ጽሑፍ ፌስቲቫል ላይ የተካፈለውና ከፍተኛ ሽያጭ የሚያስመዘግበው ቺሊያዊ ደራሲ ሉዊስ ሱፑልቪዳ፣ ከፖርቱጋል ሲመለስ ነበር በቫይረሱ ስለመያዙ ያወቀው፡፡

የኮሎምቢያ ብስክሊተኛ ፈርናንዶ ጋቫሪያ፣ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ ዲሚትሪ ስትራኮቭ፣ በጣሊያን መቀመጫውን ያደረገው የአርጀንቲና ኳስ ተጫዋች ፓውሎ እንዲሁም የአርሰናል ማናጀር ማይክል አርቴታ ከስፖርቱ ዘርፍ በቫይረሱ የተያዙ ናቸው፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚለው፣ ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ከማንኛውም ነገር ንክኪ በፊትና በኋላ እጅን በሳሙናና በውኃ ለ20 ሰኮንድ ያህል በመታጠብ ቫይረሱን መከላከል ይቻላል፡፡ ባልታጠበ እጅ ፊትን መንካት አይመከርም፡፡ በሽታው ካለባቸው ሰዎች እንዳይተላለፍ አብረው ካሉ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ መጠቀም ይመከራል፡፡ ሰው ላይ አለማስነጠስ፣ ከአፍንጫ የሚወጣ ቆሻሻ ካለ በአግባቡ ማስወገድ፣ የተጠቀሙበትን መጠራረጊያ በየቦታው አለመጣል፣ በየአካባቢው አለመትፋት መፀዳጃ ቤት ከገቡ በኋላ እንዲሁም ከምግብ በፊት እጅን መታጠብ በአጠቃላይ የግልና አካባቢን ንፅሕናን መጠበቅ ቫይረሱን ለመከላከል ይረዳሉ፡፡

ኮሮና ቫይረስ በፖለቲከኞችና ዝነኞች ቤት

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የማዳበሪያ አቅርቦትና ውጣ ውረዱ

በቅፅል ስሙ “The Father of Chemical Warfare” እየተባለ የሚጠራው...

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የትርፍ ምጣኔውን ከ70 በመቶ በላይ አሳደገ

ከሁለቱ መንግሥታዊ ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ...