Sunday, March 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህል‹‹ሰምና ወርቅ››

‹‹ሰምና ወርቅ››

ቀን:

‹‹ሥነ ጽሑፍን ሥነ ሥዕልን በፊደላትና በኅብረ ቀለማት አዋዶና አዋህዶ በቤተ ጥበባት የውበት እልፍኝ ለመሞሸር የተሞከረበት ነው ይህ መጽሐፍ፤›› የሚለው ባለፈው ሳምንት የኅትመት ብርሃን ያየው የሦስት ጥበባት ባለሙያው አሰፋ ጉያ ‹‹ሰምና ወርቅ›› መጽሐፍ ነው፡፡

በአራት ዓበይት ክፍሎች የተከፈለው መጽሐፉ፣ በቀዳሚው ክፍሉ ከሕይወት ገጠመኙ የመዘዛቸው ልዩ ልዩ መጣጥፎችን ያቀፈ ሲሆን፣ በክፍል ሁለት በሦስት አሠርታት ውስጥ ከቋጠራቸው ስንኞች መካከል የተወሰኑትን በሥነ ግጥም ክፍሉ አካቶበታል፡፡

በቀለም ቅብ፣ በሞዛይክና በተለያዩ የአሣሣል ስልቶች፣ በተለያዩ ሦስት ሥፍራዎችና ጊዜያት ካቀረባቸው የሥዕል ትርኢቶች ጋር የተያያዙ ገጠመኞቹን እስከ ትዕይንት ሥዕሎቹ የሚያስቃኘው ክፍል ሦስት ሲሆን፣ በመጨረሻው ክፍል መገናኛ ብዙኃን የጽሑፍና የሥዕል ሥራዎቹን አስመልክተው በተለያዩ ጊዜያት ከዘገቧቸው ሒሶችና ቃለ መጠይቆች መካከል አደራጅቶ ማቅረቡን ደራሲው በመግቢያው ገልጿል፡፡ ሰምና ወርቅ በ185 ብር ለሸመታ ቀርቧል፡፡

ደራሲው ከዚህ ቀደም ራህማቶ (ልብ ወለድ) እና የከንፈር ወዳጅ (ሥነ ግጥም) ማሳተሙ ይታወቃል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...