Friday, June 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊ“ከኮረና ቫይረስ ተጠበቁ”

“ከኮረና ቫይረስ ተጠበቁ”

ቀን:

የዓለም ጤና ድርጅት በድረ ገጹ እንደገለጸው፣ ኮሮና ቫይረስ የተለያዩ የቫይረስ ዓይነቶችን የያዘ የቫይረስ ቤተሰብ ነው፡፡ ይህ ቫይረስ በሰዎችና በእንስሳት ላይ በሽታን ያስከትላል፡፡ በሰዎች ላይ የሚከሰተው ኮሮና ቫይረስ የመተንፈሻ አካላትን በመጉዳት ከተራ ጉንፋን እስከ ከፍተኛ የመተንፈሻ አካል ችግር የሚያደርስ ነው፡፡

የኖቭል ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ከቀላል እስከ ከባድ የመተንፈሻ አካል ሕመም የሚያስከትል የቫይረስ ዝርያ ሲሆን በበሽታው የተያዙ ሰዎች ትኩሳት፣ ሳል፣ የትንፋሽ መቆራረጥና የመተንፈስ ችግር ምልክቶች ይታይባቸዋል፡፡

በሽታው በጠናባቸው ታማሚዎች ላይ ደግሞ እንደ ሳንባ ምች (ኒሞኒያ) ከባድ የመተንፈሻ አካላት ሕመም የሚያሳይ ሲሆን የኩላሊት ሥራ ማቆምና ሞትን ሊያስከትል የሚችል በሽታ ነው፡፡

የጤና ሚኒስቴር ሐሙስ መጋቢት 10 ቀን 2012 ዓ.ም. ምሽት እንዳስታወቀው፣ በኢትዮጵያ የኮረና ቫይረስ የተገኘባቸው ተጨማሪ ሦስት ሰዎች በመገኘታቸው  የተጠቂዎች ቁጥር ዘጠኝ ሆኗል (ለኅትመት እስከገባንበት ዓርብ ምሽት ድረስ)፡፡

በመግለጫው እንደተብራራው፣ አንደኛዋ ከዚህ በፊት በቫይረሱ መያዙ ከተረጋገጠ ግለሰብ ጋር ንክኪ የነበራቸው የ44 ዓመት ጃፓናዊት ሲሆኑ እየተደረገላቸው በነበረው የጤና ክትትልና የላቦራቶሪ ምርመራ ውጤት በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፡፡ ሁለተኛዋ ግለሰብ የ85 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ኢትዮጵያዊት መሆናቸውና ከውጪ ከመጡበት ከየካቲት 23 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ራሳቸውን ለይተው ጤናቸውን በመከታተል ላይ የነበሩና የበሽታውን ምልክት ማሳየታቸውን ከታከሙበት ሆስፒታል በተደረገ ጥቆማ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፡፡ ሦስተኛው ግለሰብ የ39 ዓመት ኦስትሪያዊ መጋቢት 6 ቀን ኢትዮጵያ የገቡ ናቸው፡፡ ሁለቱ ታማሚዎች በጥሩ ሁኔታ ላይ ሲሆኑ ኢትዮጵያዊቷ ታማሚ ግን ከባድ የሚባል ሕመም ሲኖራቸው አስፈላጊው የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

ቀደም ሲል በኮሮና ቫይረስ ተይዘው የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው ከነበሩት ውስጥ አራቱ የሕመም ምልክቶችን ማሳየት ያቆሙና በደህና ሁኔታ ላይ እንደሚገኙም የጤና ሚኒስቴር መጋቢት 9 ቀን ማሳወቁ ይታወሳል።

ኅብረተሰቡ ከዚህ በፊት ማንኛውንም በሽታ ለመከላከል ሲጠቀምባቸው የነበረውን የበሽታ መከላከያ መንገዶች ችላ ሳይልና ሳይደናገጥ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን ያስተላለፈው የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ የበሽታውን ሥርጭት ለመቀነስ ቀጥለው የተዘረዘሩትን መልዕክቶች እንዲተገበሩ ጥሪ አቅርቧል፡፡ 

ተተኳሪ ጉዳዮች

  • ሳል ወይም ትኩሳት ካለው ግለሰብ ቢያንስ ሁለት የአዋቂ ዕርምጃ ርቀት ያህል መራቅ፣
  • እጅዎን በአግባቡ ሳይታጠቡ አይንና አፍንጫዎን አይንኩ
  • ከሰዎች ጋር አይጨባበጡ፣
  • እጅን በንጹህ ውሃና ሳሙና አዘውትረው ይታጠቡ፣
  • ሰዎች ወደ በሚበዙባቸው ቦታዎች በተለይም የህመም ስሜት ካልዎት አይሂዱ፣
  • በሚያነጥሱበት እና በሚያስሉበት ጊዜ አፍና አፍንጫዎን በሶፍት ወይም ክርንዎን አጥፈው በመጠቀም ወደ ሌሎች እንዳያስተላልፉ ይጠንቀቁ፣
  •  የተጠቀሙበትን ሶፍትና ተመሳሳይ ነገሮች በቆሻሻ ክዳን ባላቸው ማጠራቀሚያ ያስወግዱ፣
  • በስራ ቦታ፣ በትራንስፖርትና መኖሪያ ወይም የመኝታ ክፍል መስኮት በመክፈት በቂ አየር እንዲኖር ያድርጉ፣
  • መረጃዎችን ከአስተማማኝ ምንጮች ብቻ በመቀበል፣ የተሳሳቱ መረጃዎች የሚያስከትሉትን መደናገርና ፍርሀት ይከላከሉ!
  • በሽታውን ሪፖርት ካደረጉ አገሮች የሚመጡ ሰዎች ወይም ንክኪ ያላቸው ማንኛወም ግለሰብ ራሱን 14 ቀን በመለየት በበሽታው አለመያዛቸውን ሲያረጋግጡ ወደ ህብረተሰቡ እንዲቀላቀሉ እንመክራለን

ለተጨማሪ መረጃ

በነፃ የስልክ መስመር 8335 ወይም በመደበኛ የስልክ ቁጥር 0118276796 ወይም በኢሜል አድራሻችን [email protected] በመጠቀም ማግኘት ይቻላል፡፡

ከኮሮና ቫይረስ እንዴት እንጠበቅ?

መተላለፊያ መንገዶች

  • በሽታው በሳልና በማስነጠስ ወቅትና ከታማሚ ሰው ጋር በሚደረግ የቅርብ ንክኪ፣ ባልታጠበ እጅና በመሳሰሉት ይተላለፋል፡፡ በሽታውን ሪፖርት ወደ አደረጉ አገሮች የሚጓዙ መንገደኞች ሊያደረጓቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች፣
  • የትኩሳትና የሳል ምልክት ከሚያሳዩ ሰዎች ጋር ንክኪ አለማድረግ፣
  • እጅን በሳሙናና ውኃ መታጠብ በተለይ ደግሞ ከታመሙ ሰዎች ወይም ከአካባቢያቸው ጋር ንክኪ ካደረጉ፣
  • ያልበሰሉ የእንስሳት ተዋፅኦ የሆኑ ምግቦችን ከመመገብ መቆጠብ፣
  • ምክንያቱ ባልታወቀ በሽታ በታመሙም ሆነ ከሞቱ የቤትና የዱር እንስሳት ጋር ንክኪ አለማድረግ

በበሽታው መያዛቸውን የጠረጠሩ ሰዎች ማድረግ ያለባቸው ጥንቃቄዎች

  • ወደ ሀገር በተመለሱ 14 ቀናት ጊዜ ውስጥ የመተንፈሻ አካል ሕመም፣ ትኩሳትና እንደ ሳል ያሉ የሕመም ምልክቶች ካሳዩ፣ በተጨማሪ የበሽታው ስሜት ከመፈጠሩ አሥራ አራት ቀናት በፊት በሽታውን ሪፖርት ወዳደረጉ አገሮች ሄደው ከነበረ፣ በሽታውን ሪፖርት ወደ አደረጉ አገሮች ሄዶ የበሽታውን ምልከቶች ማሳየት የጀመረ ሰውን የሚያውቅ ማንኛውም ግለሰብ እንዲሁም የበሽታውን ምልክት ማሳየት የጀመረ ሰውን የሚያውቅ በአስቸኳይ 8335 ነጻ የስልክ መስመር በመደወል ሪፖርት ያድርጉ፡፡
  • በሚያስሉበትና በሚያስነጥሱበት ጊዜ በሽታው ወደ ጤነኛ ሰው እንዳይተላለፍ አፍና አፍንጫን በክንድ ወይም በሶፍት መሽፈን፣
  • አፍና አፍንጫን ለመሽፈን የተጠቀምንበትን ሶፍት በአግባቡ በቆሻሻ መጣያ ውስጥ ማስወገድና እጅን ሁልጊዜ በውኃና በሳሙና መታጠብ ያስፈልጋል፡፡
spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...