Saturday, September 30, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር በአዲስ አበባ የነበራቸውን ስብሰባ አራዘሙ

የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር በአዲስ አበባ የነበራቸውን ስብሰባ አራዘሙ

ቀን:

የህዳሴ ግድብ ውዝግብ አንደኛው የመወያያ አጀንዳ ነበር

 የወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ ሊቀመንበር የሆኑት የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲርል ራማፎዛ፣ በአዲስ አበባ ዓርብ መጋቢት 11 ቀን 2012 ዓም ከኅብረቱ ኮሚሽን ጋር በአዲስ አበባ ሊያደርጉት የነበረውን ስብሰባ ለመጪው ወር እንዲተላለፍ ወሰኑ።

የአፍሪካ መሪዎች ከአንድ ወር በፊት በአዲስ አበባ ባደረጉት ስብሰባ የኅብረቱ ጠቅላላ ጉባዔ ሊቀመንበር አድርገው የመረጧቸው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ተይዞ የነበረውን ስብሰባ የሰረዙት፣ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ በአገራቸው የተፈጠረውን አስቸኳይ ሁኔታ ለመምራት መሆኑ ታውቋል።

የህዳሴ ግድቡ ውዝግብ በአፍሪካ ኅብረት አሸማጋይነት እንዲፈታ ኢትዮጵያ በያዘችው አቋም መሠረት ጥያቄዋን ለኅብረቱ ሊቀመንበር ፕሬዚዳንት ራማፎዛ ማቅረቧ ያስታወሱት የሪፖርተር የዲፕሎማቲክ ምንጮች፣ ፕሬዚዳንቱ ከኅብረቱ አመራሮች ጋር ሊያደርጉት በነበረው ውይይት ከተያዙ አጀንዳዎች መካከልም ይህ ጉዳይ እንደሚገኝበት ጠቁመዋል።

የኅብረቱ ሊቀመንበር በአዲስ አበባ ሊያደርጉት የነበረው ስብሰባ ኃላፊነቱን ከተረከቡ በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ ከኅብረቱ ኮሚሽነሮች ጋር ተገናኝተው ውይይት የሚያደርጉበት፣ እንዲሁም የዓመቱን ቀዳሚ የሥራ ዕቅዶቻቸውን የሚነድፉበት ነበር።

ታስቦ የነበረው ይህ ስብሰባ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽን በታቀደው ቀን ማካሄድ ባይቻልም፣ የጋራ ስምምነት በሚደረስበት ቀን በቀጣዩ ወር ውስጥ እንደሚካሄድ ታውቋል።

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሚ ሹክሪ በህዳሴ ግድቡ ውዝግብ ላይ እያደረጉ በሚገኘው የዲፕሎማሲ ጉዞ ከተካተቱ መዳረሻ አገሮች መካከል ደቡብ አፍሪካ አንዷ የነበረች ሲሆን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩም ከፕሬዚዳንት አልሲሲ ለፕሬዚዳንት ራማፎዛ የተላከ ደብዳቤ ለአቻቸው የደቡብ አፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማድረሳቸው ታውቋል።

ከዚህ በተጨማሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ወደ ኡጋንዳ፣ ሩዋንዳ፣ ታንዛኒያና ሌሎች የአፍሪካ አገሮች በማምራት ፕሬዚዳንት አልሲሲ የላኳቸውን መልዕክቶች ለየአገራቱ ማድረሳቸው ታውቋል። በኢትዮጵያ በኩልም ተመሳሳይ የዲፕሎማሲ ጉዞዎች በአፍሪካና በአውሮፓ መደረጋቸው ይታወሳል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...