Thursday, February 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየኮሮና ቫይረስን የመከላከል አቅም የሚጨምር መድኃኒት በኢትዮጵያ ማግኘት እንደተቻለ ተገለጸ

የኮሮና ቫይረስን የመከላከል አቅም የሚጨምር መድኃኒት በኢትዮጵያ ማግኘት እንደተቻለ ተገለጸ

ቀን:

እ.ኤ.አ. በጃንዋሪ 2020 በቻይና ሁቤይ ግዛት ውሃን ከተማ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ከተገኘበት ጊዜ አንስቶ ዓለም ቫይረሱን ለመከላከያ፣ ለማከሚያና ለማዳኛ የሚሆኑ መድኃኒቶችን ለማግኘት እየተረባረበ ባለበት ወቅት፣ የጤና ሚኒስቴርና የኤኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በመቀናጀት ከባህላዊ መድኃኒት የተቀመመና የኮሮና ቫይረስን የመከላከል አቅም የሚጨምር ማከሚያ መድኃኒት ማግኘታቸውን አስታወቁ፡፡

ቫይረሱ በዓለም መስፋፋቱ ከተነገረበት ጊዜ አንስቶ ምርምር ሲደረግበት እንደቆየ፣ የባህል ሕክምና ባለሙያዎች በአገር ውስጥና በውጭ አገር ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተመራማሪዎች ጋር በመጣመር አበረታች ውጤት የታየበት መድኃኒት መገኘቱ ተገልጿል፡፡ ‹‹ቫይረሱን ለማከም የተሠራው መድኃኒት መሠረታዊ የምርምር ሒደት በማለፍ ተደጋጋሚ የቤተ ሙከራ ሞዴሊንግ ሒደቶችን በስኬት አልፏል፤›› በማለትም ተገልጿል፡፡

‹‹ምርምሩ የኮሮና ቫይረስ በዓለም ላይ መከሰቱ ከተሰማ ጊዜ ጀምሮ ከተለያዩ በአገር ውስጥና በውጭ ከሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ሲካሄድ የቆየ ሲሆን፣ ተደጋጋሚ የምርምር ሒደት አልፎ ወደ ምርትና ቀጣይ የእንስሳት ፍተሻና ክሊኒካል ፍተሻ ሥራዎች እንዲሸጋገር ተደርጓል፤›› ሲል የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያወጣው መግለጫ ያትታል፡፡

ክሊኒካል ፍተሻ በሰዎች ላይ የሚደረግ እንደሆነ የአሜሪካ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን ያስረዳል፡፡ በኢትዮጵያ ተገኘ የተባለው መድኃኒት የመከላከል አቅምን የሚጨምር፣ መርዛማነት የሌለውና አዋጭነቱ የተረጋገጠ ነው ሲልም መግለጫው አክሏል፡፡

በአሜሪካ የመድኃኒትና የምግብ ባለሥልጣን መመርያ መሠረት አንድ መድኃኒት ከምርምር አንስቶ እስከ ጥቅም ላይ መዋል ሊከተላቸው የሚገቡ አምስት ደረጃዎችን ማለፍ እንዳለበት ይጠቁማል፡፡ የመጀመርያው ማግኘትና ማልማት ሲሆን፣ ሁለተኛው ቅድመ ክሊኒካል ሙከራ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ተገኘ የተባለው መድኃኒትም እነዚህን ደረጃዎች እንዳለፈና ወደ ሦስተኛ ደረጃ ማለትም የክሊኒካል ወይም የሰዎች ላይ ሙከራ እንደተዛወረ ተገልጿል፡፡

ከክሊኒካል ሙከራው በመቀጠል ግምገማና ከዚያም በኋላ የሚኖሩ የደኅንነት ሁኔታዎችን መቆጣጠር ናቸው፡፡

በእነዚህ ደረጃዎች ውስጥ በርካታ ዝርዝር ጉዳዮች የሚካተቱ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ መድኃኒት ግኝት እነዚህን ሒደቶች በምን ያህል ትኩረት እንዳከናወናቸው የተነገረ ነገር የለም፡፡ በተጨማሪም የተመራማሪዎቹን ማንነት፣ ምርምሩ የወሰደውን ጊዜ፣ የገንዘብ መጠን፣ የመድኃኒቱን ግብዓቶች፣ የመድኃኒቱን የአዕምሯዊ ንብረት ጥበቃ ጉዳይና የመሳሰሉ ተያያዥ ጥያቄዎችን በተመለከተ ምላሽ ለማግኘት ሪፖርተር በሁለቱም ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ያደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡

የመድኃኒቱን ግኝት በተመለከተ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይም እንዲገኙ የተደረጉት የተመረጡ የመንግሥት የመገናኛ ብዙኃን ብቻ ነበሩ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ማስተካከያ

በሪፖርተር ጋዜጣ ረቡዕ ጥር 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ዕትም...

[ክቡር ሚኒስትሩ በወቅታዊ ፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የቀረበላቸውን ምክረ ሐሳብ እያደመጡ ነው]

ችግሩ ምን እንደሆነ በትክልል ለይተነዋል ግን ግን ምን? በይፋ መናገር አልነበረብንም። ለምን? ችግሩን...

የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ውጤትና እንደምታው

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) የትምህርትን...

ንግድ ባንክ ከቪዛና ማስተር ካርድ ጋር ተደራድሮ ያስጀመረው የገንዘብ ማስተላለፊያ ቴክኖሎጂና ፋይዳው

ከውጭ ወደ አገር በሕጋዊ መንገድ የሚላክ ገንዘብ (ሬሚታንስ) መጠን...