Thursday, March 30, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትበኮሮና ቅድመ መከላከል የስፖርት ተቋማት ሚና

በኮሮና ቅድመ መከላከል የስፖርት ተቋማት ሚና

ቀን:

ኃያላኑን አገሮች ጨምሮ የዓለም ሳይንቲስቶች ከሁሉም በፊት ትኩረታቸውን  በአንድ ነገር ካደረጉ ወራት እየተቆጠሩ ነው፡፡ በቻይና ውኃን ግዛት በፈረንጆቹ አዲስ ዓመት መባቻ ለተከሰተውና በምህፃረ ቃሉ ኮቪዲ 19 የሚል መጠሪያ ላገኘው ኮሮና ቫይረስ፡፡ እስካሁን ባለው ወረርሽኙ ሊገታው የቻለ ምድራዊ ኃይል አልተገኘለትም፣ ኮሮና በማይታመን ፍጥነት ዓለምን እያዳረሰ የሰው ልጆችን ሕይወት እያጠቃ ይገኛል፡፡

ወረርሽኙ ዘር፣ ቀለም፣ ትንሽና ትልቅ ሳይለይ ሁሉንም ከማጥቃቱ ጎን ለጎን ስፖርቱን ጨምሮ በተለያዩ የንግድ ተቋማት ላይ ይህ ቀረሽ የማይባል ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ቀውስ እያስከተለ ነው፡፡ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ‹‹ይካሄዳል አይካሄድም›› በሚል ለአገሮች ከፍተኛ ሥጋት ሆኖ የሰነበተው ቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ በተጠናቀቀው ሳምንት መጀመሪያ ወደ ሚቀጥለው ዓመት እንዲሸጋገር ምክንያት የነበረውም ይኼው ኮሮና ቫይረስ መሆኑ የወረርሽኙን አደገኛነት ልብ ይሏል፡፡

ወቅቱ በኮሮና ቫይረስ በከፍተኛ ሁኔታ የተጠቁ አገሮች ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ጥረት እያደረጉ የሚገኙበት፣ የወረርሽኙ ምልክት ካልሆነ ሞት ያላስከተለባቸው አገሮች ደግሞ በሌላ ወገን የአደጋውን መጠን ለመቀነስ ቅድመ ዝግጅት ላይ ትኩረት ሰጥተው የሚንቀሳቀሱበት ነው፡፡

በኮሮና ቅድመ መከላከል የስፖርት ተቋማት ሚና

 

ለዚሁ ሲባል በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ዩኒቨርሲቲዎችን ጨምሮ ትምህርት ቤቶች፣ የስፖርት ማዘውተሪያዎችና ሰዎች ይሰበሰብባቸዋል ተብሎ የሚገመቱ ሁሉ ለጊዜውም ቢሆን ዝግ እንዲሆኑ፣ ጎን ለጎን ደግሞ ችግሩ አሁን ከሚስተዋለው ተባብሶ እንዳይቀጥል ራሱን የቻለ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ የቅድመ መከላከል ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ከእነዚህ ሥራዎች ውስጥ የስፖርቱን ተቋማት ከሚመሩት አካላት ጀምሮ በየደረጃው የሚገኙ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እየተበረከተ የሚገኘው የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ይጠቀሳል፡፡

በዚህ ረገድ ስፖርቱን ከሚመሩ ተቋማት ቅድሚያውን የወሰዱት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንና የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መጋቢት 17 ቀን 2012 ዓ.ም. በወሰነው መሠረት፣ ለኮሮና ቫይረስ ቅድመ መከላከልና ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል የሁለት ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉ ታውቋል፡፡ የብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ በግሏ እንደዚሁ ለሁለቱ ዓበይት ጉዳዮች 400,000 ብር ለግሳለች፡፡

ፌዴሬሽኑ ይህን የገንዘብ ልገሳና ድጋፍ ሲያደርግ በሥነ ሥርዓቱ የተገኙት የጤና ሚኒስትር ሊዲያ ታደሰ (ዶ/ር) እና በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሮማን ገብረሥላሴ በየበኩላቸው፣ ሌሎች የስፖርት ተቋማትም አቅማቸው በፈቀደ መጠን ለእንዲህ ዓይነቱ ቅዱስና ወገኖችን ለመታደግ የሚያስችል ተግባር መረባረብ እንደሚጠበቅባቸው ማሳሰባቸው ተሰምቷል፡፡

መንግሥት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት የወገኖችን አፋጣኝ ርብርብ በሚጠይቅበት በዚህ ወቅት፣ ‹‹ፌዴሬሽኑ ከጎናችን በመሆን እንደ ተቋም አንድ ሚሊዮን ብር እንዲሁም የተቋሙ መሪ ኮማንደር ደራርቱ በግሏ ሁለት መቶ ሺሕ ብር ድጋፍ ላደረጉት አብሮነት እጅግ አድርጌ አመሠግናለሁ፣ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በማንኛውም ሁኔታ ከመንግሥት ጎን በመሆን ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ እንደሚገኝ ግልጽ ነው፤›› በማለት የጤና ሚኒስትሯ ለተቋሙ ያላቸውን አክብሮት መግለጻቸው መረጃው አመልክቷል፡፡

በተመሳሳይም የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት ኃላፊዋ ወ/ሮ ሮማን በበኩላቸው፣ ‹‹የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምሳሌያዊ ተግባር በጣም አበረታች ነው፣ ኮማንደር አራርቱ ቱሉ የማስተባበሪያ ምክር ቤቱ አባል ከመሆናቸወም በላይ የክብር አምባሳደር መሆናቸው ይታወቃል፡፡ በእሳቸው የሚመራው አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከሌሎች ስፖርት ፌዴሬሽኖች፣ ማኅበራትና ሌሎችም ተቋማት ግንባር ቀደም በመሆን እንደ ተቋም አንድ ሚሊዮን ብር ኮማንደር ደራርቱ ደግሞ በግሏ ሁለት መቶ ሺህ ብር ለፈጸሙት አኩሪ ተግባር ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነው፣›› ማለታቸው ታውቋል፡፡

ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ በበኩሏ፣ ‹‹ልግስናው ሁሉም አገር ወዳድ ዜጋ በዚህ ወቅት በጋራ እንዲረባረብና በተለይም ወረርሽኙን እንድንመክት ነው፤›› ብላ  ሌሎችም ተቋማት የበኩላቸውን እንደሚወጡ ያላትን እምነት መናገሯ ታውቋል፡፡

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበርና ደጋፊዎችም በተመሳሳይ ለኮሮና ቫይረስ ቅድመ መከላከል የሚያስፈልጉ ግማሽ ሚሊዮን ብር ግምት ያላቸውን ቁሳቁሶችን ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢ/ር) በዛው ሳምንት አስረክበዋል፡፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም ለኮሮና ቫይረስ ቅድመ መከላከል የግማሽ ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉ ታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[የምክር ቤቱ አባል ላቀረቡት ጥያቄ በተሰጣቸው ምላሽ አቤቱታቸውን ለክቡር ሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር ትክክል ነው? ምነው? ምክር ቤቱም ሆነ...

የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ትኩሳት

ቅዳሜ መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በጉራጌ ዞን ወልቂጤ...

አይ የእኛ ነገር!

የዛሬው ጉዞ ከጀሞ ወደ ፒያሳ ነው፡፡ መንገዱ ለሥራ በሚጣደፉ፣...

የዓለም ኢኮኖሚ መናጋት ለወቅታዊው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ችግር ምክንያት ነው?

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ባለፈው ማክሰኞ መጋቢት 16...