በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ካትሪን ሶዚ (ዶ/ር) ካደረጉት ንግግር የተወሰደ፡፡ አስተባባሪዋ እንደሚሉት የኮሮና ቫይረስን ሥርጭት ከመግታት በተጨማሪ፣ አስፈላጊ ግብዓቶችን ለማሰባሰብ የሚደረገውን ጥረት ማሳደግ ያስፈልጋል፡፡ ጥረቶችን በማቀናጀትና በማስተባበር ለወረርሽኙ በቂ ምላሽ መስጠት የግድ ነው ብለዋል፡፡ የጋራ ኃላፊነትና ዓለም አቀፋዊ የትግል አንድነት ኮሮና ቫይረስን ድል ለመንሳት ቁልፍ መሆኑን አስተባባሪዋ አስገንዝበዋል፡፡