Friday, December 8, 2023

በኮሮና ምክንያት ቤት ውስጥ በሚኖር ቆይታ የሚፈጠሩ ጥቃቶችን ፍርድ ቤቶች በአስቸኳይ እንዲያዩ መመርያ ተሰጠ

- Advertisement -spot_img

በብዛት የተነበቡ

በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ 19) ወረርሽኝ ምክንያት በቤት ውስጥ እንዲቆዩ በተደረጉ የኅብረተሰብ ክፍሎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን፣ ፍርድ ቤቶች ከሚያዩዋቸው ጥቂት አስቸኳይ ጉዳዮች አንዱ አድርገው እንዲሠሩ መመርያ ተሰጠ፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ በትዊተር ገጻቸው ላይ እንዳስታወቁት፣ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ፍርድ ቤቶች መደበኛ ሥራቸውን አቁመዋል፡፡ ዳኞች በቤታቸው ሆነው እየሠሩ ቢሆንም፣ የተወሰኑ ወይም ጥቂት ጉዳዮች  ግን በችሎት እየታዩ ነው፡፡ በመሆኑም በወረርሽኙ ምክንያት በቤት ውስጥ እንዲቆዩ በተደረጉ የኅብረተሰብ ክፍሎች ላይ ጥቃቶች መፈጸማቸው በፖሊስ ተመርምሮ ሲቀርብ፣ ፍርድ ቤቶች ለማየት ዝግጁ መሆናቸውን አሳውቀዋል፡፡

የሦስቱም ፌዴራል ፍርድ ቤቶች ቃል አቀባይና የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ተስፋዬ ነዋይ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በዚህ የወረርሽኝ ጊዜ ዜጎች በቤት ውስጥ ሲቆዩ ጊዜ ጥቃቶች ሊፈጸሙባቸው ይችላሉ፡፡ ጥቃቶቹ  በቤተሰብ መካከል፣ በባልና ሚስት ወይም በሌላ ሊሆን ይችላል ብለዋል፡፡

ምንም እንኳን በኢትዮጵያ በጥናት የተረጋገጠ መረጃ ባይኖርም፣ ጥናት በተደረገባቸው እንደ ቻይና፣ እንግሊዝ፣ አሜሪካና ፈረንሣይ የመሳሰሉ አገሮች የቤት ውስጥ ጥቃት (Domestic Violence) በሦስት እጥፍ ጨምሯል፡፡ ጥቃቱ አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት እንደሚያደርስ መረጋገጡንም አቶ ተስፋዬ አስረድተዋል፡፡

ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ መንግሥታትና ፖሊሲ አውጪዎች ስለቤት ውስጥ ጥቃቶች ሊያደርጉ የሚችሉትን እ.ኤ.አ. ማርች 19 ቀን 2020 የዓለም ጤና ድርጅት ያወጣውን ሪፖርት ታሳቢ በማድረግ፣ የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶችም ዝግጁ ሆነው መጠበቅ ስላለባቸው በሥራ ላይ ያሉ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የቤት ውስጥ ጥቃቶችን ለማስተናገድ ዝግጁ መሆናቸውን አቶ ተስፋዬ አክለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ትኩስ ጽሑፎች

ተዛማጅ ጽሑፎች

- Advertisement -
- Advertisement -