Monday, March 20, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊንግድ ባንክ የኮንዶሚኒየም ቤት ክፍያና ወለድ ማሰብ እንዲያቆምላቸው ነዋሪዎች ሊጠይቁ ነው

ንግድ ባንክ የኮንዶሚኒየም ቤት ክፍያና ወለድ ማሰብ እንዲያቆምላቸው ነዋሪዎች ሊጠይቁ ነው

ቀን:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገንብቶ ላለፉት 12 ዙሮች የጋራ መኖሪያ ቤቶች (ኮንዶሚኒየም) የደረሷቸው ነዋሪዎች፣ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሥጋት ምክንያት የሥራ እንቅስቃሴያቸው መገታቱን በማስታወቅ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በየወሩ የሚፈጽሙትን መደበኛ ክፍያና የሚታሰብባቸውን ወለድ ለጊዜው ባለበት እንዲቆምላቸው ሊጠይቁ መዘጋጀታቸው ተጠቆመ፡፡

በተለይ የ20/80 ኮንዶሚኒየም ባለቤቶች ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው መሆናቸውን በማስታወስ፣ ዓለምን እያመሰ በሚገኘው ወረርሽኝ ምክንያት ሳይወዱ በግድ በቤት እንዲቀመጡ በመገደዳቸው ከልጆቻቸውና ከራሳቸው ቀለብ ያለፈ ገቢ ስለሌላቸው አቤቱታ ለማቅረብ ተዘጋጅተዋል፡፡

 ወረርሽኙ ተገቶ እነሱም ሠርተው መክፈል እስከሚችሉ ድረስ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንዲከፍሉ የተተመነባቸውን ክፍያና የሚታሰብባቸውን ወለድ በማቆም እንዲተባበራቸው ለመጠየቅ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕድለኞች አብዛኞቹ አከራይተውና ተከራይተው የሚኖሩ በመሆናቸውና የተከራዩ ነዋሪዎች ሥራ አቁመው በመቀመጣቸው፣ ኪራዩን በነበረው ስምምነት መሠረት ሊከፍሏቸው እንደማይችሉና እነሱም ሳይወዱ በግድ ኪራይ መቀነስ ስላለባቸው፣ ባንኩ ይኼንን በማስተዋል እንዲተባበራቸው ሊጠይቁ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በመንግሥትና በባለሙያዎች የሚሰጡትን መመርያዎች ተግባራዊ በማድረግ ሕዝብ ከተባበረና ራሱን ከጠበቀ ወረርሽኙን በአጭር ጊዜ ድል በማድረግ ዓለም የተለመደ እንቅስቃሴዋን እንደምትቀጥል በመመኘት፣ እነሱም ያለባቸውን ቀሪ ሒሳብ ካቆሙበት በመቀጠል ግዴታቸውን እንደሚወጡ እየገለጹ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም የንግድ ባንክ አመራሮችና መንግሥት ሁኔታውን ተመልክተው ሐሳባቸውን በመደገፍ ከጎናቸው እንደሚቆሙ በመተማመን፣ ጥያቄውን ረቡዕ ሚያዝያ 7 ቀን 2012 ዓ.ም. ሊያቀርቡ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕድለኞች ሊያቀርቡ ነው ስለተባለው ጥያቄና ንግድ ባንክ ከጋራ መኖሪያ ቤቶች ክፍያና ከሌሎች ብድሮች ጋር በተያያዘ ያሰበው ነገር ካለ ማብራሪያ እንዲሰጡ ለሕዝብ ግንኙነት ሥራ አስኪያጁ አቶ የአብሥራ ከበደን ሪፖርተር ላቀረበላቸው ጥያቄ ‹‹ባንኩ በራሱ ያሰበው ነገር አለ፣ ከኃላፊዎች ጋር ተወያይቼ ምላሽ ልስጣችሁ፤›› ካሉ በኋላ፣ በድጋሚ ሊገኙ ባለመቻላቸው ተጨማሪ ማብራሪያ ማካተት አልተቻለም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ዜጎች የተፈተኑበት የኑሮ ውድነት

በኢትዮጵያ በየጊዜው እየተባባሰ የመጣው የኑሮ ውድነት የበርካታ ዜጎችን አቅም...

በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች የሚደረጉ ድጋፎች ዘላቂነት እንዲኖራቸው ተጠየቀ

በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች የሚደረጉ ድጋፎች ዘላቂነት እንዲኖራቸውና በተቀናጀ መልኩ...

ወደ ኋላ የቀረው የሠራተኞች ደኅንነት አጠባበቅ

በአበበ ፍቅር ለሠራተኞች የሚሰጠው የደኅንነት ትኩረት አናሳ በመሆኑ በርካታ ዜጎች...