Wednesday, March 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልየፋሲካው መልዕክት

የፋሲካው መልዕክት

ቀን:

የዘንድሮውን የእግዚእ ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳዔ በዓል ምክንያት በማድረግ የሃይማኖት አባቶች በዋዜማው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ በከፊል እንዲህ ቀርቧል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ወርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ

በእርሱ ያመኑ ሕሙማንን ያድን ዘንድ የታመመው፣ የሞተውና ሞትን ድል አድርጎ የተነሳው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለብርሃነ ትንሳዔው በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!!

የክርስቲያኖች መሠረተ ሃይማኖት ወልደ እግዚአብሔር የሆነው አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለእኛና ስለድኅነታችን ሲል በለበሰው ሥጋ ታመመ፣ ሞተ፣ ተቀበረ፣ በሦስተኛውም ቀን ሞትን ድል አድርጎ፣ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ ተነሳ የሚለው ነው፡፡ … በመሆኑም በሕማሙ ሕመማችንን፣ በሞቱ ሞታችንን፣ በመቃብሩ ሙስና መቃብርን አስወግዶ በትንሳዔው ትንሳዔያችንን አብስሮናል፣ በዚህ የጌታችን ቤዛነት ዕዳችን ሁሉ ከላያችን ላይ ስለተነሳልን በትንሳዔው ላመን ሁሉ የድኅነት ሽልማታችን እሱም ፍጹም መዳናችን ለጌታ ቀን ተዘጋጅቶልን በፊታችን ይጠብቀናል፡፡ በዚያን ጊዜ በእርሱ ሕመም ሕመማችን ጠፍቶ፣ በእርሱ ሞት ሞታችን ተሸንፎ፣ በእርሱ መቃብር መቃብራችን ባዶ ሆኖ በክብር እንነሳለን፡፡ በዚያን ጊዜ እኛም እንደ እሱ የማይታመም፣ የማይሞትና መቃብር የማይነካው አካል ተጎናጽፈን ከእርሱ ጋር ፍጻሜ በሌለው ሕይወት በመንግሥቱ እንኖራለን፡፡

… በየጊዜው በልዩ ልዩ በሽታ እንታመማለን፣ እንሰቃያለን፣ በመከራም እናልፋለን፣ ነገር ግን ይህ ሁሉ በእኛ ላይ እንዲሆን የእግዚአብሔር ፈቃድና ፍላጎት ነው ወይ? ካልን የመጽሐፍ ቅዱስ መልስ አይደለም የሚል ነው፡፡ ሕሙማንን ለማዳን የታመመው አምላክ ሕሙማን በልዩ ልዩ በሽታዎች እንዲጠቁ ይፈቅዳል ማለት የማይቻል ነው፡፡ ይሁን እንጂ ከእግዚአብሔር ቁጥጥር ውጪ የሆነ በሽታ የለምና በሃይማኖታችን፣ በጸሎታችን እሱ በሰጠን አዕምሮ ተጠቅመን እንድንከላከል ብቻ ሳይሆን በምንችለው ሁሉ እንድንመክተው እግዚአብሔር ይፈልጋል፡፡

ሁላችንም ከጌታችን አስተምህሮ እንደምንረዳው በእግዚአብሔር የተሰጡ ሕጎች በሙሉ ዓላማቸው ሰውን ለማዳን ብቻ ነው፡፡ ስቅለቱም፣ ሞቱም፣ ትንሳዔውም የተደረገው ለሰው ነው፡፡ ሰንበትም የተፈጠረችው ለሰው እንጂ ሰው ለሰንበት አልተፈጠረም፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ጾሙ፣ ጸሎቱ፣ ሱባዔው የተፈጠረው ለሰው ነው፡፡

ሰው ከሌለ ጸሎቱም፣ ጾሙም፣ ሱባዔውም፣ ሃይማኖቱም ሳይቀር ሌላው ሁሉ የለም፣ ምክንያቱም ይህ ሁሉ የተፈጠረው ለሰው ነውና ሰው ከሌለ ለማን ተብሎ ይደረጋል፡፡ እግዚአብሔር መጀመርያውኑ ሲፈጥረን በዚህ ዓለም እንደፈቃዱ ልንኖር እንጂ በአሰቃቂ በሽታ ተሰቃይተን ተዋርደንና የሚቀብረን አጥተን እንደ ቅጠል ረግፈን ልንቀር አይደለም፡፡

እውነት ነው እግዚአብሔር ይህንን አሰቃቂ የኮሮና በሽታ በከሃሊነቱ አንድ ቀን  ያስወግደዋል፣ ግን እኛስ በሰጠን አዕምሮና ባለሙያዎቻችን በሚነግሩን (በሚሰጡን) ምክር ተጠቅመን የአቅማችንን ያህል መከላከል የለብንም ወይ? ነው ጥያቄው፡፡ አዎ መከላከል አለብን፡፡ እንዲያውም እግዚአብሔር ዕውቀቱን በፈቀደላቸው የጥበብ  ባለሙያዎች ልጆቻችን ችግሩንና መፍትሔውን እየነገረን እያለ እግዚአብሔር ያውቃል እያልን ቸል የምንል ከሆነ ጌታችን እንደነገረን እግዚአብሔርን መፈታተን ነው የሚሆነው፡፡ ይህም ኃጢአትም ነው፡፡

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ምድራዊ ወኪል በሆነው በቅዱስ ሲኖዶስ አማካይነት ምዕመናን በቤታቸው ሆነው በመጸለይ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን እንዲከላከሉ ያስተላለፈው ውሳኔ እንዲሁ ዝም ብሎ አይደለም፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ ይህንን ራስን የመጠበቅና የመከላከል ውሳኔ ያስተላለፈው፡-

  1. እግዚአብሔር አንድ ሰው እንኳ በጥንቃቄ ጉድለት እንዲጎዳ የማይፈቅድ መሆኑን ስለሚያውቅ፣
  2. አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በቤት ሆኖ መጸለይና መጾም ሱባዔንም መፈጸም የተፈቀደ ብቻ ሳይሆን እንዲያውም እንደዚህ ያለ ችግር ሲያግጥም ‹‹ወደ እልፍኝህ ግባ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ›› የሚል የጌታችን ትዕዛዝና ትምህርት መኖሩን ስለሚያውቅ፣
  3. ምዕመናንም ሆኑ ካህናት እስካሉ ድረስ እግዚአብሔር ምሕረቱን በላከልን ጊዜ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አንድ ላይ ሆነን መጸለይ፣ ማመስገንና ማስቀደስ፣ ማምለክና መቁረብ እንደሚቻል በመንዘብ ነው፣
  4. ምዕመናን ከሌሉ ሁሉንም እናጣለን ከሚል አባታዊ ርኅራኄና አርቆ አስተዋይነት በመነሳት፣ እንደዚሁም በተሰጠን ሥልጣን ይህንን ነገር ለሕዝባችን ባናስታውቅ በእግዚአብሔርም በሥነ ምግባርም ከባድ ወቀሳና ተጠያቂነት እንደሚያስከትልብን በመረዳት ነው፡፡

ስለዚህ አሁንም ቢሆን ከቅዱስ ሲኖዶስ በተላለፈውና ለወደፊትም እንደ አስፈላጊነቱ በሚተላለፈው ሲኖዶሳዊ ብይን መሠረት በየቤታችሁ ሆናችሁ ከልብ ወደ እግዚአብሔር በመጸለይ በሽታውን እንድትከላከሉ፣ ለተቸገሩ ወገኖችም ባላችሁ አቅም ሁሉ እንድትረዱና እንድታግዙ በእግዚአብሔር ስም አደራችንን እናስተላልፋለን፡፡

ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነ የሱስ

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹ክርስቶስ ሁሉ ነው፡ በሁሉም ነው›› ይላል። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዛሬ በአዲስ ሁኔታ በበዓለ ትንሳዔ በእኛ ይኖራል። እኛም ከእርሱ ጋር የእግዚአብሔር ልጆች ነን ሰለሆነም ዛሬ ወደ እርሱ የምንመለስበት ቀን ነው።

የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳዔ ከማክበር የበለጠ ቀን የለም። ሆኖም የዘንድሮው በዓላችን ዘንና በጨለማ የተከበበ ቢመስለንም በተስፋ የተሞላ ሆነን እናከብረዋለን። ምክንያቱም ጌታችን የሥጋውን ድካም ሞትን ድል በማድረግ በመንፈሳዊነት እንዳሸነፈ እኛም የሥጋን ድካም በመንፈሳዊነት እንደምናሸንፍ አውቀን በዚህ ወቅት የዓለም ደዌ ሆኖ የመጣውን የኮሮና ቫይረስ እርሱ በትንሳዔ እንዲሽርልንና እንዲያጠፋልን የጀመርነውን የጸሎትና የንስሐ ልመና አምላካችን ሆይ እንደቸርነትህ ብዛት ማረን፣ ይቅር በለን በማለት አጠናክረን ልንቀጥል ያስፈልጋል።

ከዚህ ጋር ልባችንን ሙሉ በሙሉ ልናስገዛለት ይገባናል። ምክንያቱም ክርስቶስ በልባችን ውስጥ ሲኖር እነሆ በክብር ተስፋው እንኖራለን። አሁን ከፀ በታች ያለው መልካም ነገር ሁሉ ከንቱ መሆኑን አይተናል። ከዚህ በኋላ የሚቀረን እግዚአብሔርን ፈርቶ ማክበር እና ለእርሱ መታዘዝ ነው።

ብዙዎቻችን ዓመቱን ስንጀምር ብዙ ነገሮችን አቅደን ይሆናል። በትምህርት፣ በሥራ፣ በንግድ፣ በጉዞ፣ ሌሎችም ሆኖም ግን በዚህ ደዌ እንቅፋት ገጥሞናል፡፡ ቢሆንም ቅዱስ ጳውሎስ ወደኋላ ሊጎትቱ የሚችሉ እንቅፋቶች በገጠሙት ጊዜ ምንም ነገሮች ቢከሰቱ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለይኝ የሚችል ምንም ነገር የለም በማለት ፀንቶ እንደቆመ እኛም እስከመጨረሻው በጋራ ፀን በመቆም ንነቱንና ፈውሱን በልመናና በንስሐ ተግተን ረቱን ልንጠብቅ ያስፈልጋል።

ማንኛውም ሰው ቢሆን ይወቱን እንደማይረባ ነገር ቆጥሮ በማይሆን አቅጣጫ መምራት የለበትም። ትርጉም የሚሰጠውን ይወት ለመኖርና የሙሉ ደስታ ይወትነ መልስን ለማግኘት በየዕለቱ የሚነገረንን እና የምንባለውን መስማትንና የሚያዋጣውን መፈፀም ያስፈልገናል።

የፈጠረን አምላክ የማይለወጥና ቅዱስ ነው፡፡ ይወት ያለው ፍጥረት በሙሉ ያለ እርሱ መኖር እንደማይችል ሁሉ ለተጨነቀው አዕምሮአችን ሰላምና እርጋታን የሚስጠን እርሱ ነው።

የምናደርገው እንቅስቃሴያችን ለጊዜው ከመንቀሳቀስ ቢታገድም በማንኛውም መንገድ ለነፍሳችን የሚተላለፈውን የእግዚአብሔር መልዕክት ማዳመጥ መቻል አለብን ብቻችንን አይደለም ያለነው፡፡

የከበበንን አስፈሪ ነገር ስናየው ያለእርሱ ምንም መሆናችንን ያስረዳናል፡፡ ሰው አሁን ከምንጊዜውም በበለጠ አምላኩን የሚፈለግበት ጊዜ ነው። ሁሉም ወደርሱ ተንበርክኮ በድለንሃልና ይቅርበልን የሚልበት እንጂ በራሱ ብቻ የሚሮጥበት ምንም ነገር የለውም፡፡ ማንም ከዚህ መቅሰፍት ካለጌታ መሻገር አይልምና።

አሁን የመጣብን መከራ ከእግዚአብሔር አቅምና ችሎታ በላይ ስላልሆነ በእርሱ ጥላ ሥር መሆን ያስፈልገናል። እርሱ በዙሪያችን እንደሚገኝ ስናውቅ ሐና ደስታ ይሞላናል፡፡ ትንቢተ ዕንባቆም 3 17-18 ላይ እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፣ ‹‹እኔ በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል እርሱ መድኃኒቴም ስለሆነ ሐሴት አደርጋለሁ፤›› ይላል።

ጌታችን የደረሰበትን መከራና ስቃይ ስናስብና የክርስቶስን ትንሳ ስናብር እኛም ባሳለፍነው አርባ ጾም ዓለም ከክርስቶስ ጋር ያሳለፈውን መከራና ስቃይ ስናስተውል በእርሱ ደግሞ ድልና መድኃኒት መኖሩን በማመን ነው። በጎልጎታ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር እንደሌለ ያሳየን ራሱን በሞት እስከመስጠት የወደደን ዛሬም ልጆቼ አይዟችሁ ይለናል።

ቄስ ዮናስ ይገዙ ዲብሳ፣ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ፕሬዚዳንት

የክርስቶስ ትንሳዔ ከጥንት በእግዚአብሔር ዘንድ የነበረው ዘለዓለማዊው መለኮታዊ ፈቃድ የተከናወነበት፣ የሰው ልጆች ያለተስፋ በጨለማና በሞት ጥላ ሥር ከነበሩበት ሕይወት አርነት ወጥተው፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንዲሁ በተገለጠው የዕርቅ ፀጋ ከእግዚአብሔርና ከእርስ በርሳቸው ጋር የታረቁበት፣ የሞትና የክፋትይላትም በክርስቶስ ሞትና ትንሳዔ ድል የሆኑበት፣ ለሰው የማይቻል ነገር ግን ለእግዚአብሔር ብቻ የተቻለው አስደናቂ የድነት ፀጋ የተገለጠበት መለኮታዊ አሠራር ነው፡፡

እግዚአብሔር ጠብን በዕርቅ ጥላቻን በፍቅር፣ ሞትን በሕይወት፣ ልዩነትን በአንድነት የተበቀለበት ጊዜ ቢኖር ኢየሱስ ክርሰቶስ በመሰቀል ላይ በተሰቀለበትና ሞትን ድል ነሰቶ መቃብርን ፈንቅሎ በተነሳበት ወቅት እንደሆነ ክርስቲያኖች እናምናለን፡፡ እንመሰክራለንም፡፡ ጥላቻ ሰላማዊ ንግግርን የሚከለክል፣ የፍቅርና የመደማመጥን ዕድል የሚነፍግ፣ የሰውን ህሊናና ልብ ሰርቆ የከንቱና የጎጂ አስተሳሰብ ባሪያ የሚያደርግ የሰላምና የአንድነት ፀር ነው፡፡

… ስለዚህ የጥላቻ፣ የንቀት፣ የትዕቢት ንግግርና ድርጊት የከበረውንና እግዚአብሔር ንጹህ አድርጎ የፈጠረውን ህሊና አሳልፎ ለክፋት ምርኮኛ ያደርጋል፡፡ አሁን ባለንበት በዘመነው ዓለም ጥላቻን ባላካተተ ምክንያታዊ አስተሳሰብ ላይ በተመሠረተ ተግባቦት አብሮ ለመኖር ጥረት እየተደረገ ባለበት ሁኔታ ተቃራኒ አካሄድን መከተል ምንም ጠቀሜታ ስለሌለው በተለይም አማኞች ልዩነትን በእርቅ አሸንፎ ከልዩነት አንድነትን የፈጠረውን የጌታችንን መስዋዕታዊ ቤዛነት በመከተል የአንድነት ሐዋሪያት ለመሆን መትጋት ይገባናል፡፡

በአሁኑ ወቅት አኅጉራችንና አገራችንን ጨምሮ ዓለምን በሞላ፣ በእጅጉ እያሠጋ ያለው ኮቪድ 19 በሚል ስያሜ የሚታወቀው የኮሮና ቫይረስ ከሦስት ወራት በፊት በምድረ ቻይና ተከስቶ፣ርጭቱ በአስደንጋጭና አሳሳቢ ፍጥነት በመላውለም መዳረሱ ይታወቃል፡፡ በበርካታ የዓለም አገሮች እየተዛመተ በርካታ ሰዎችን ለዕልፈተ ሕይወት እየዳረገም ይገኛል፡፡ የቫይረሱርጭት አድማሱን እያሰፋ ጥቃት እያደረሰና በአገራችንም የችግሩ ሰለባ እየሆኑ የሚገኙት ወገኖች ቁጥር እያሻቀበ እንደሆን በየዕለቱ ከሚሰጠው መንግሥታዊ መግለጫዎች ማረጋገጥ ይቻላል፡፡

በመሆኑም በአሁኑ ወቅት ሁሉም ዜጋ ራሱን መጠበቅ፣ ለወገኑ መጠንቀቅ፤ ከመንግሥት፣ ከባለሙያዎችና ከሃይማኖት መሪዎች የሚሰጠውን ምክር ተቀብሎ ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ ቫይረሱ እንዳይዛመት ሁሉም በየቤቱ በመሆን ወደ አምላኩ በጾምና በፀሎት በመቅረብ ምሕረትን ሳይታክቱ በትህትና መለመን ትልቁ መፍትሔ እንደሆነ ማመንና ይህንኑ መተግበር ተገቢ ነው፡፡ ለጊዜው የተገኘው መፍትሔና በባለሙያዎች የሚመከረው ርቀትን መጠበቅ፣ እጅን ቶሎ ቶሎ በሳሙና መታጠብ፣ አለመተቃቀፍ፣ ከንኪኪ መታቀብ፣ ሰዎች በዛ ብለው በሚገኙበት ሥፍራ አለመገኘት፣ አለመጨባበጥና አስቸጋሪ ካልሆነ በስተቀር ከቤት አለመውጣት ብቻ ነው፡፡

… ከዚህ ከወረርሽኙ ክስተት የተነሳ የዘንድሮውን የፋሲካ በዓል የምናከብረው ከሌላው ጊዜ በተለየውድ ውስጥ ሆነን እንደሆነ ይታወቃል፡፡ እንደሚታወቀው የወረርሽኙንርጭት ለመግታት ይቻል ዘንድ፣ ለተወሰነ ጊዜ ቤተ ክርስቲያንን ጨምሮ ባልተለመዱ ልምምዶች ውስጥ ለማለፍ አስገድዷል፡፡ በተለይም ለቫይረሱርጭት ዕድል ከሚሰጡ ሁኔታዎች መታቀብ የግድ በመሆኑ አስፈላጊ የሆኑ የክልከላ ዕርምጃዎች መደንገጋቸው እንደ ቤተ ክርስቲያን ላሉት አካላት አስደንጋጭና ለመቀበልም የሚያስቸግር መስሎ ሊታይ እንደሚችል እንገምታለን፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ የክልከላ ሥርዓቶች ለእኛው ለራሳችን፣ ለሕዝባችንና እንደ አገርም አገር ሆነን እንድንቀጥል ለማድረግ የተጣለ ክልከላ ስለሆነ የሚከብድ ቢመስልም፣ የውጤቱ ተጠቃሚዎች መሆናችሁን በማመን ጨክናችሁ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ማለፍ እንድትችሉ በታላቅ ትህትናና የእረኝነት መንፈስ እንለምናችኋለን፡፡

ይህ ሁኔታ ዝቅተኛ ኑሮ ባላቸው የኅብረተሰባችን ክፍል ላይ በየዕለት ዕለት ኑሮ ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ቀላል እንደማይሆን ግልጽ ነው፡፡ በመሆኑም እንደ እምነታችንና ባህላችን በዚህ አስቸጋሪ ወቅት፣ ለእርስ በርስ ተግባራዊ ርህራሄን በማሳየት፣ ያለንን ከሌላቸው ጋር በመካፈል፣ በልግስና በመተጋገዝ፣ አንድም ቤተሰብ ወይም ግለሰብ እንዳይጎዳ፣ ከምንበላው፣ ከምንጠጣው፣ ከምንለብሰውና እግዚአብሔር በቸርነቱ ከሰጠን ሁሉ ለሌሎች በማጋራት ተያይዘን በአሸናፊነት ለመዝለቅ መበርታት ይጠበቅብናል፡፡

በተለይም እኛ ክርስቲያኖች ጎረቤታችንን ወይም ችግር ያለባቸውን ማገልገል ጥሪአችን እንደሆነና ለክርስቶስ ያለንን ፍቅር የምንገልጽበት አንዱ መንገድ እንደሆነም እናምናለን፡፡ ስለዚህም በጥሪያችሁ ልክ ለመኖር ትበቁ ዘንድ ፀጋ ይብዛላችሁ፡፡

spot_img
Previous article
Next article
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...

አወዛጋቢነቱ የቀጠለው የአዲስ አበባ የጤፍ ገበያ

ሰሞኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጤፍ የተከሰተውን የዋጋ ንረት...