Wednesday, March 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊሰምቶ እንዳልሰማ የመሆን አባዜ

ሰምቶ እንዳልሰማ የመሆን አባዜ

ቀን:

በተመስገን ተጋፋው

በዓለም ኃያላን አገሮችን ጭምር ያንበረከከውና ለኢትዮጵያ ሥጋት የሆነው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ፣ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት የሚከበረውን ትንሳዔ (ፋሲካ) በዓል የነበረውን የአብሮነት ድባብ አጥፍቶት ውሏል፡፡

ሆኖም የቫይረሱን ሥርጭት ለመቀነስ ሲባል የተሰጡ ግንዛቤ ማስጨበጫዎች በተለይ በገበያ ሥፍራዎች ሲተገበሩ አልተስተዋለም፡፡ በአንዳንድ ቦታዎች ላይ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ርቀትን ከመፍጠር ይልቅ ማኅበራዊ ትስስርን በማስቀደም ከዚህ ቀደም ሲከበሩ እንደነበሩ ክብረ በዓሎች ሁሉ በጋራ ሆኖ የዕርድ ሥርዓትን (ቅርጫን) ሲያከናውኑ ታይቷል፡፡ ከዛም አልፎ ‹‹መሞታችን አይቀር እስኪ በልተን እንሙት›› የሚል ማምለጫ በመፍጠር ርቀታቸውን ሳይጠብቁ የበሽታውን አስከፊነት በመተው አድርጉ ያልተባሉትን ነገር ሲያደርጉ የዋሉም ነበሩ፡፡

ጥሬ ሥጋ ለኮሮና ቫይረስ ሥርጭት ምክንያት ሊሆን ይችላል ተብለው ከተቀመጡ መካከል አንዱ በመሆኑ፣ ጥሬ ሥጋንና ሌሎች ያልበሰሉ ምግቦችን ኅብረተሰቡ እንዳይመገብ የሕክምና ባለሙያዎች ቢያሳስቡም፣ ሰምቶ አልሰሜዎች ጥቂት አለመሆናቸውን የበዓል ቀን በሉካንዳ ቤቶች ተሰብስበው ጥሬውን ሲያሻምዱ የነበሩትን ያስተዋለ ይመሰክራል፡፡ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች እንደ ወግ ባህሉ የቅርጫ ክፍፍል ሥርዓት ሲከናወን ጥሬ ሥጋ የመቅመስ ልማድ መኖሩ ከብዙዎቹ አይጠፌ ነው፡፡ በኮሮና ቫይረስ ሥጋት ምክንያት ጥሬ ሥጋ ለምኔ ብሎ ከመመገብ ራሳቸውን የቆጠቡ በርካቶች ቢሆኑም፣ ‹‹ኧረ ምን አባቱ ከላይ አረቄ ደፋ ሲደረግ ምንም አያመጣም›› በማለት እንደ ልብ ቢላቸውን እያፋጩ ሲመገቡ ታዝበናል፡፡

የአመጋገብ ሥርዓቱ ሰብሰብ ብለው አንዱ ለሌላው እያጎረሰ መሆኑ ይበልጥ አሥጊ ያደርገዋል፡፡ የነበረውን ሁኔታ ቆሞ ለታዘበውም በሽታው ለበዓል ከአገር የወጣ አስመስሎታል፡፡

በሳሪስ፣ በሃና ማርያምና በአቦ አካባቢ ላይ የሚገኙ ሆቴሎችም ላይ ጥሬ ሥጋ የኮሮና ቫይረስ መተላለፊያ መንገድ መሆኑ እስኪጠፋቸው ድረስ ቁጭ ብለው ሲመገቡ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

የኮሮና ቫይረስ መተላለፊያ መንገዶችን በመዘንጋት በሆቴሎች ላይ ርቀታቸውን ሳይጠብቁ ቁጭ ብለው በመዝናናት በዓሉን ያሳለፉ ግለሰቦችም ነበሩ፡፡

የወረርሽኙን ሥርጭት ለመግታት መንግሥት አዋጅ አውጥቶ፣ አዋጁን ተግባራዊ ለማድረግ እየተሠራ ቢሆንም፣ አልፎ አልፎ ግን ችግሮች ይታያሉ፡፡ በሆቴሎችም ላይ ከመሸ በኋላ መጠጥ ተደብቆ ሲሸጡ ተስተውሏል፡፡

ቫይረሱ በኢትዮጵያ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ እየተሠራ ቢሆንም፣ በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ ግን የመደንገጥ ሁኔታ እንኳን እንደማይታይ ይስተዋላል፡፡ ይህም ችግር ለቫይረሱ መስፋፋት ምክንያት ከመሆኑ በፊት ማኅበረሰቡ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባው የሕክምና ባለሙያዎችና ያነጋገርናቸው ግለሰቦች መክረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...

አወዛጋቢነቱ የቀጠለው የአዲስ አበባ የጤፍ ገበያ

ሰሞኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጤፍ የተከሰተውን የዋጋ ንረት...