የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ዋና ጸሐፊ አንቶንዮ ጉተሬዝ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተውን የኮቪድ-19 (ኮሮና ቫይረስ) ወረርሽኝ ተከትለው የሚሠራጩ የተዛቡ መረጃዎች አስመልክቶ የተናገሩት፡፡ የተመድ የባህል ዘርፍ ተጠሪው ዩኔስኮ የተዛቡ መረጃዎችን፣ ስህተትና የፈጠራ ወሬዎችን አስመልክቶ የገመገመበትና አቅጣጫ የሚያስቀምጥ ፖሊሲዎችን በማዘጋጀት የዩኔስኮ አባላት፣ የኢንተርኔት የኮሚዩኒኬሽን ኩባንያዎች፣ ዜና ማሠራጫዎች፣ ጋዜጠኞች፣ ሲቪል ማኅበራትና ሌሎች ባለድርሻዎች እንዲቃኙት ጥናቱን አውጥቷል፡፡