Tuesday, December 5, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናባይቶና የምርጫውን መራዘም እንደሚቃወም አስታወቀ

ባይቶና የምርጫውን መራዘም እንደሚቃወም አስታወቀ

ቀን:

ብሔራዊ ባይቶ ዓባይ ትግራይ (የታላቋ ትግራይ ብሔራዊ ኮንግረስ) – (ባይቶና) ዘንድሮ ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው ጠቅላላ ምርጫ፣ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን በመቃወም ምርጫው በጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ ጥሪ አቀረበ፡፡

ፓርቲው የተመሠረተበትን አንደኛ ዓመት አስመልክቶ በወቅታዊ ጉዳዮችና  ስላሳለፈው የአንድ ዓመት የፖለቲካ ጉዞ ባወጣው  መግለጫ፣ በተለይ የምርጫውን መራዘም በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቃወም አስታውቋል፡፡

ባይቶና ባለፈው አንድ ዓመት በተለይ በትግራይ ሕዝብ ላይ ተጋረጠ ያለውን ‹‹የደኅንነት አደጋ›› ለመመከትና ሕዝቡን ከዚህ አንፃር ለማንቃት ከፍተኛ ሥራ መሥራቱን ለሪፖርተር የገለጹት የፓርቲው የውጭ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ክብሮም በርሔ፣ በዚህም የተሳካ ሥራ ማከናወን መቻሉን አስረድተዋል፡፡

ዘንድሮ ሊካሄድ ዕቅድ ተይዞለት የነበረውን ጠቅላላ ምርጫ አስመልክቶ፣ ‹‹በእርግጥ ኮሮና ያስከተለው ችግር ከባድ ነው፡፡ ነገር ግን ችግር አለ ማለት ሌላ ችግር ትጨምራለህ ማለት አይደለም፡፡ ምርጫውን ማራዘም ሕገ መንግሥታዊ ቀውስ ያስከትላል፤›› ሲሉ የፓርቲውን ተቃውሞ አሰምተዋል፡፡

ይህንን ሕገ መንግሥታዊ ቀውስ ለማስወገድ፣ ‹‹ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ በአገራችን ያለው ሁኔታ በሌሎች አገሮች እንደምንመለከተው ባለመሆኑ፣ ምርጫውን ከፍተኛ ጥንቃቄ በተሞላበት ሁኔታ ማካሄድ ይቻል ነበር፤›› ብለዋል፡፡

ምርጫውን በጊዜው አለማካሄድ በርካታ ችግሮች እንደሚያስከትል የገለጹት አቶ ክብሮም፣ ‹‹በዋናነት ግን ምርጫው በጊዜው ካልተካሄደ መንግሥት አልባ መሆንን ያስከትላል፡፡ መንግሥት አልባ መሆን ደግሞ ሁሉንም ዓይነት ጣጣ ሊያመጣ ይችላል፤›› ሲሉ፣ ምርጫው በጊዜው ባለመካሄዱ ሊደርስ ይችላል ያሉትን ችግር ገልጸዋል፡፡

በኮሮና ወረርሽኝ ሳቢያ የምርጫው መካሄድ ‹‹ለድርድር መቅረብ አልነበረበትም፤›› ያሉት አቶ ክብሮም፣ ባለፈው ሳምንት ከምርጫው መራዘም ጋር ተያይዞ በመንግሥት የቀረቡት አማራጭ የመፍትሔ ሐሳቦችንም፣ ‹‹ምርጫውን ለማራዘም የተደረደሩ ሐሳቦች ናቸው፤›› ሲሉ አጣጥለዋቸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...