Monday, December 5, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናአቶ በረከት ስምኦን የተከሰሱበት የሙስና ወንጀል ተቀይሮ በወንጀል ሕጉ ጥፋተኛ ተባሉ

  አቶ በረከት ስምኦን የተከሰሱበት የሙስና ወንጀል ተቀይሮ በወንጀል ሕጉ ጥፋተኛ ተባሉ

  ቀን:

  ከጥረት ኮርፖሬት ኩባንያዎች በተለይም ከዳሸን ቢራ አክሲዮን ማኅበር ድርሻ ሽያጭ ጋር በተያያዘ በከፍተኛ የሙስና ወንጀል ክሶች ተከሰው ሲከራከሩ የከረሙት የቀድሞ የኢሕአዴግ ከፍተኛ ባለሥልጣን የነበሩት አቶ በረከት ስምዖን፣ የተከሰሱበት የሙስና ወንጀል አንቀጽ ወደ መደበኛ ወንጀል ሕግ አንቀጽ ተቀይሮ ጥፋተኛ ተባሉ፡፡

  የጥረት ኮርፖሬት ቦርድ ኃላፊ የነበሩት አቶ ታደሰ ካሳም የተወሰኑ ክሶች ወደ መደበኛ ወንጀል ሕግ ተቀይሮላቸው ጥፋተኛ የተባሉ ሲሆን፣ በአንድ ክስ ግን የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 ተላልፈዋል በማለት ጥፋተኛ ተብለዋል፡፡ የዲቨንትስ ኩባንያ ባለድርሻ አቶ ዳንኤል ግዛው ግን ከተመሠረተባቸው ክስ በነፃ ተሰናብተዋል፡፡

  ተከሳሾቹ ከዳሸን ቢራ አክሲዮን ኩባንያ ሽያጭ ለጥረት ኮርፖሬት ገቢ መደረግ የነበረበትን 83 ሚሊዮን ዶላር ለዳሸን ቢራ አክሲዮን ማኅበር ቀሪ እንዲሆን አድርገዋል፣ እንዲሁም የዳሸንን ከፍተኛ አክሲዮን የገዛው ዱየት የሚባለው የእንግሊዝ ኩባንያ ገቢ ማድረግ የነበረበትን 53 ሺሕ ዶላር ገቢ ሳያደርግ መቅረቱን በሚመለከት የቀረበውን ክስ፣ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውድቅ አድርጎታል፡፡ ለጥናት 635 ሺሕ ዶላር እንዲከፈል ማድረጋቸውን በሚመለከት ተገቢ አለመሆኑን በሚመለከት በቀረበባቸው ክስ ጥፋተኛ ተብለዋል፡፡ ጥናት ሳይደረግ የዳሸን ቢራን አክሲዮን ለእንግሊዙ ዱየት ኩባንያ 50.1 በመቶ ድርሻ መስጠታቸው ተገቢ አይደለም በማለት፣ ዓቃቤ ሕግ ያቀረበው መከራከሪያ ተቀባይነት በማግኘቱ ጥፋተኛ ተብለዋል፡፡

  ዳሸን ቢራ ፋብሪካ የተሸጠበት ዋጋ ትክክል እንዳልሆነና ከሜታ ቢራ ፋብሪካ ጋር በተደረገ የንፅፅር ዋጋ፣ ከ22 ሚሊዮን ዶላር በላይ ጥረት ኮርፖሬት እንዲያጣ ስለማድረጋቸው የቀረበውን ክስ ፍርድ ቤቱ ውድቅ አድርጎታል፡፡

  በሦስቱም ተከሳሾች ላይ ዓቃቤ ሕግ ያቀረበው ክስ አቶ ዳንኤል ለባለቤታቸው 16 ሚሊዮን ብር የዲቨንቱስን ድርሻ የከፈሉት ከጥረት ኮርፖሬት መሆኑን በሚመለከት ቢሆንም፣ ማረጋገጫ ሊቀርብ ባለመቻሉ ሁሉም በነፃ ተሰናብተዋል፡፡

  ሌላው የሙስና ወንጀሎች ድንጋጌን ተላልፈዋል ተብለው ጥፋተኛ የተባሉት አቶ ታደሰ ሲሆኑ፣ አቶ ዳንኤል ለተበደሩት የጥረት ኮርፖሬት ጋራንቲ ሲሰጥ እሳቸው ኃላፊ በመሆናቸው መመለስ አለመመለሱን መመልከት ሲገባቸው፣ ዝም ብለው መስጠታቸው ተገቢ አይደለም በማለት ጥፋተኛ ብሏቸዋል፡፡

  የአማራ ክልል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ሕግ የመሠረተውን ክስ ሲመረምርና ሲያከራክር የከረመው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰጠው የጥፋተኝነት ውሳኔ ላይ የቅጣት ማቅለያ እንዲያቀርቡ የተጠየቁት አቶ በረከትና አቶ ታደሰ፣ እስካሁን ታግሰው የቆዩት ፍርድ ቤቱ ክሱንና ማስረጃውን አይቶ በሚሰጠው ውሳኔ ነፃ እንደሚሆኑ ስለነበር የሚያቀርቡት የቅጣት ማቅለያ አይኖርም ማለታቸውን ጠበቃቸው ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

  ነገር ግን ዓቃቤ ሕግ በዕለቱ የቅጣት ማክበጃ ማቅረብ ባለመቻሉ፣ ለሚያዝያ 28 ቀን 2012 ዓ.ም. ስለተቀጠረ እነሱም ሊያቀርቡ ይችላሉ የሚል እምነት እንዳላቸው ጠበቃዋ ተናግረዋል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  ዳግም ነፍስ የዘራው የተማሪዎች ማርች ባንድ

  የሙያው ፍቅር ያደረባቸው ገና በልጅነታቸው ነው፡፡ በ1970ዎቹ መጀመርያ፣ ለቀለም...

  በስንደዶና ሰበዝ የተቃኘው ጥበብ

  በአንዋር አባቢ ተወልዳ ያደገችው መሀል አዲስ አበባ አራት ኪሎ ነው፡፡...

  አዲስ ጥረት የሚጠይቀው  ኤችአይቪ  ኤድስን  የመግታት  ንቅናቄ

  ‹‹ኤችአይቪ በመላው ዓለም  በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚያጠቃ ዋነኛ የሕዝብ...

  የኅትመት ብርሃን ያየው ‹‹የቃቄ ወርድዎት›› ቴአትር

  ከአራት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር መድረክ ላይ ይታይ...