Wednesday, March 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየሊጉን ቀጣይ ዕጣ ለመወሰን ጥናትና መጠይቆች በመፍትሔነት ተይዘዋል

የሊጉን ቀጣይ ዕጣ ለመወሰን ጥናትና መጠይቆች በመፍትሔነት ተይዘዋል

ቀን:

የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከሰቱ ከታወቀ ጀምሮ በጥቂት አገሮች ካልሆነ በስተቀር የእግር ኳስ ውድድሮች ተቋርጠዋል፡፡ እስካሁን የተቋረጡ ውድድሮችን ለማስጀመርም ሆነ ለማቋረጥ እንዲሁም የተጀመሩትን ለማጠናቀቅ የሚቻልበት አማራጭ ለማወቅ ከባድ ሆኗል፡፡ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮፌዴሬሽን (ካፍ) ለአባል አገሮች ባስተላለፈው መልዕክት፣ በኮረና ቫይረስ ምክንያት የተቋረጠው ሊግ ለመጀመርም ሆነ ለማቋረጥ አገሮች ከሊጋቸው ነባራዊ ሁኔታ በመነሳት ውሳኔያቸውን እንዲያሳውቁት ጠይቋል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ውሳኔውን ለካፍ ከማሳወቁ በፊት ጉዳዩን ገለልተኛ በሆነ አካል እያስጠና ከመሆኑ ጎን ለጎን ባለድርሻ ለሚባሉ አካላት ማለትም ለክለብ አሠልጣኞች፣ ለአመራሮችና ለመገናኛ ብዙኃን መጠይቆችን ልኮ ለጥናቱ አጋዥ ሊሆን የሚችል ግብዓት በማሰባሰብ ላይ ይገኛል፡፡

ብሔራዊ ፈዴሬሽኑ የጥናቱን ግኝትና መጠይቁን መነሻ በማድረግ የሊጉን ቀጣይ ዕጣ ምን ይሁን የሚለውን እንደሚወስን አስታውቋል፡፡ መንግሥት በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ያወጀው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አኳያ ውሳኔው ለፌዴሬሽኑ ፈታኝ ሊሆን እንደሚችል የሚናገሩ አልጠፉም፡፡

“ውሳኔው ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ነው” በሚሉት የፌዴሬሽኑ ጽሕፈት ቤት ተጠባባቂ ኃላፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን አገላለጽ፣ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የሊጉን ቀጣይነት ከሚወስነው ጥናት በተጨማሪ ለዘርፉ ተዋንያን መጠይቅ ማዘጋጀት ያስፈለገው፡፡ እስካሁንም ከጥናቱ ጀምሮ ወደ ባለድርሻ የተላኩት መጠይቆች ተጠናቀው ለፌዴሬሽኑ ከደረሱ በኋላ የማጠቃለያ ትንተና የሚሰጥበት ይሆናል፡፡ ይሁንና በዚህ ደረጃ ያለውን ጉዳይ መሠረት የሌላቸው መረጃዎች ፌዴሬሽኑ የማያውቃቸው ስለመሆናቸው ጭምር አቶ ባህሩ ተናግረዋል፡፡

ካፍ አባል አገሮች የሊጎቻቸውን ቀጣይ ዕጣ እንዴት ሊወስኑ እንዳሰቡ አብራርተው እንዲያሳውቁት የሰጠው ቀነ ገደብ ማክሰኞ ሚያዝያ 27 ቀን 2012 ዓ.ም. አብቅቷል፡፡ ፌዴሬሽኑ በሚቀርብለት ጥናትና መጠይቅ መሠረት ትንተና መስጠት እንደሚቀረው እየገለጸ በሚገኝበት በዚህ ወቅት፣ አንዳንዶች ፕሪሚየር ሊጉን ጨምሮ በተዋረድ የሚገኙ ሊጎች ዕጣ ፈንታ እንዴት መሆን እንዳለበት የሚተነትኑ አልጠፉም፡፡

ሁሉም ሊጎች እስከተቋረጡበት ድረስ ክለቦቹ ባላቸው የነጥብ ደረጃ የዘንድሮ ውድድር ፍጻሜውን እንዲያገኝ፣ በዚሁ መሠረት ፕሪሚየር ሊጉን በአንድ ነጥብ የሚመራው ፋሲል ከተማ በቀጣይ ዓመት በአፍሪካ የክለቦች ሻምፒዮንስ ሊግ ኢትዮጵያን እንዲወክል፣ በአንድ ነጥብ ዝቅ ብሎ የሚገኘው መቐለ 70 እንደርታ ደግሞ ለአፍሪካ ክለቦች ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተሳትፎ ይኖረዋል፡፡ በተመሳሳይ ከፕሪሚየር ሊጉ ወደ ብሔራዊ ሊጉ የሚወርዱትና ወደ ፕሪሚየር ሊጉ የሚያድጉት ክለቦችም ባላቸው ነጥብ ውጤታቸው እንዲወሰን እየተነገረ ይገኛል፡፡

እያንዳንዱ ክለብ 30 ጨዋታ በሚያደርግበት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር፣ መሪው ፋሲል ከተማ 52 ነጥብ ሲኖረው፣ ተከታዩ መቐለ 70 እንደርታ 51 ነጥብ እንዲሁም ቅዱስ ጊዮርጊስ ደግሞ 50 ነጥብ ይዘው ነው በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ጨዋታው የተቋረጠው፡፡ በዚህ ስሌት ከፕሪሚየር ሊጉ ወደ ብሔራዊ ሊጉ የመውረድ ዕጣ የሚኖራቸው ደግሞ ጅማ አባ ጅፋር፣ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲና ሐድያ ሆሳዕና ይሆናሉ ማለት ነው፡፡

ስሌቱን ከጥቂቶች በስተቀር ብዙዎቹ የማያስኬድ ስለመሆኑ ያስረዳሉ፡፡ በስሌቱ መሠረት በሦስት ምድብ ተከፍሎ እየተከናወነ ከሚገኘው ብሔራዊ ሊጉ ወደ ፕሪሚየር ሊጉ የሚያድጉት የየምድባቸው መሪ የሆኑት ለገጣፎ ከተማ፣ ነቀምት ከተማና አርባ ምንጭ ከተማ ይሆናሉ፡፡

ሊጉን በባለቤትነት የሚያስተዳድረው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እያደረገ ከሚገኘው ዳሰሳ መረዳት የሚቻለው፣ ለሁሉም ነገር ከጥናቱና ከመጠይቁ በመነሳት ወደ መፍትሔው መሄድ መፈለጉ ነው፡፡     

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...

አወዛጋቢነቱ የቀጠለው የአዲስ አበባ የጤፍ ገበያ

ሰሞኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጤፍ የተከሰተውን የዋጋ ንረት...