Wednesday, May 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ፍሬከናፍር“ለሁላችሁ ልነግራችሁና ልትረዱት የምፈልገው ይህ ቀን ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ ያዲስ ታሪክ ዘመን መክፈቻ...

“ለሁላችሁ ልነግራችሁና ልትረዱት የምፈልገው ይህ ቀን ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ ያዲስ ታሪክ ዘመን መክፈቻ መሆኑን ነው”

ቀን:

ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ፣ ከሰባ ዘጠኝ ዓመታት በፊት ኢትዮጵያ በፋሺስት ጣሊያን ላይ ድል መቀዳጀቷን ተከትሎ በዳግማዊ ምኒልክ ቤተ መንግሥት አገራዊውን ሰንደቅ ዓላማ ካውለበለቡ በኋላ ካሰሙት ዲስኩር የተወሰደ፡፡ ከወራሪው የፋሺስት ጣሊያን ሠራዊት ጋር ለአምስት ዓመት የዘለቀው ጦርነት መቋጫ በሆነው ሚያዝያ 27 ቀን 1933 ዓ.ም.፣ ከስደት ወደ አገራቸው የተመለሱት አፄ ኃይለ ሥላሴ በዕለቱ ባሰሙት ዲስኩር፣ ዕለቱ ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ዘርግታ እልል እያለች ምስጋናዋን የምታቀርብበት፣ ደስታዋን ለልጆችዋ የምትገልፅበት ቀን ነው ካሉ በኋላ፣ የኢትዮጵያ ልጆች ከባዕድ የመከራ ቀንበርና ከዘላለም ባርነት ነፃ የወጡበት ቀንና እኛም አምስት ዓመት ሙሉ ተለይተነው ከነበረው ከምንወደውና ከምንናፍቀው ሕዝባችን ጋር ለመቀላቀል የበቃንበት ቀን ስለሆነ ይህ ቀን የተከበረና የተቀደሰ ነው… በዚህም በአዲስ ዘመን ሁላችን መፈጸም ያለብን አዲ ሥራ ይጀመራል ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የማዳበሪያ አቅርቦትና ውጣ ውረዱ

በቅፅል ስሙ “The Father of Chemical Warfare” እየተባለ የሚጠራው...

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የትርፍ ምጣኔውን ከ70 በመቶ በላይ አሳደገ

ከሁለቱ መንግሥታዊ ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ...