Sunday, June 4, 2023
- Advertisment -
- Advertisment -

የአገራችን የፀረ ሙስና ትግል ያጋጠሙት ተግዳሮቶችና ሊወሰዱ የሚገባቸው የመፍትሔ ዕርምጃዎች (ክፍል አንድ)

በሐረጎት አብርሃ

ሙስና (Corruption) የሚለው ቃል በግልጽ መቼ ጥቅም ላይ እንደዋለና መቼ እንደ ወንጀል መቆጠር እንደጀመረ ግልጽ የሆነ፣ በጥናት የተደገፈና ወጥ የሆነ ዓለም አቀፍ ስምምነት የለም፡፡ አገሮች እንደ ራሳቸው ነባራዊ ሁኔታ የሚተረጉሙበትና የሚረዱበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው ስምምነት ሙስና የሁሉም አገሮች ዋነኛ ችግር እንደሆነ ይኼም ለብዙ ዘመናትና ዓመታት ማስቆጠሩ ነው፡፡ ሙስና በግልጽ መቼ እንደተጀመረ የሚያሳይ ጥናት ባይኖርም ግን በኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉዳይ ላይ ጥናት ያደረጉ ብዙ ምሁራን እንደሚሉት ሙስና ከ16ኛ እና 17ኛ ክፍለ ዘመን በተለይም በአውሮፓ ከነበረው የኢንዱስትሪ አብዮት ማግሥት ጀምሮ ከእጅ ወደ አፍ የነበረውን የግብርና ኢኮኖሚን ትተው ወደ ኢንዱስትሪ ሲሸጋገሩ የምርት አቅርቦት መጨመር፣ ዘመናዊ የሥርጭት ሥርዓት መፈጠር፣ የሚጠቀሙትን ቴክኖሎጂ መራቀቅ እንዲሁም በሒደት የሥራ ፍሰትና ውስብስብነት መጨመር ለሙስና መከሰት ትልቅ ዕድል መፍጠሩና በጊዜ ሒደት ትልቅ አጀንዳ እየሆነ መምጣቱን ይገልጻሉ፡፡ በሒደትም ትልልቅ የኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽኖች/ካምፓኒዎች ወደ ሙስና ቅሌት (Scandal) እንደገቡ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በሃይማኖትና በሳይኮሎጂ ዘርፍ ያሉ ምሁራን ደግሞ ሙስና የሚለው ቃል መቼና የት እንደጀመረ ከሃይማኖትና ሳይኮሎጂ አንፃር የራሳቸው መላ ምት ወይም ትንታኔ የሚያስቀምጡበት ሁኔታ አለ፡፡ ዞሮ ዞሮ ሙስና ዓለማዊ ይሁን ሃይማኖታዊ መነሻ ይኑረው ለዴሞክራሲና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት እንዲሁም ለአጠቃላይ የኅብረተሰብ ዕድገትና ደኅንነት ጠንቅ ወይም ዋነኛ ችግሮች ተብለው ከሚጠቀሱ ችግሮች አንዱ መሆኑን በሁሉም ዘርፍ ያሉት ምሁራን የሚስማሙበት ሀቅ ነው፡፡ ሙስና የማይነካው አገር የለም፡፡ የዓለም ኅብረተሰብ ይኼን ችግር ለመቅረፍ በጋራ ቃልኪዳን ገብቶ የተለያየ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡ 

ሙስና በአገራችን ያደረሰው ጉዳትና ተፅዕኖ በቀላሉ የሚነሳ ጉዳይ አይደለም፡፡ ብዙ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ አስከትሏል፡፡ በቅርብ ዓመታት ወደ ግንባታ ገብተው የነበሩ ሰፋፊ ፕሮጀክቶች በአጭሩ እንዲቀጩ ዕድል ፈጥሯል፡፡ ሥራ አጥነት እንዲስፋፋ፣ የመንግሥት የአገልግሎት አሰጣጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተዳከመ እንዲሄድ ከማድረጉ በተጨማሪ የአገሪቷን አንጡራ ሀብት በሕገ ወጥ መልክ ወደ ውጭ እንዲሸሽ ትልቅ ዕድል ፈጥሯል፡፡ ከፍ ሲልም በ2010 ዓ.ም. በአገራችን  የመንግሥት ለውጥ እንዲፈጠር  የሙስና ሚና ቀላል ነበር ብሎ መውሰድ አይቻልም፡፡

በተለያየ ደረጃ የነበሩ መንግሥታት ወይም የመንግሥት አመራሮች ሙስና ጠላቴ ነው ብለው ቢፈርጁትም በተግባር ግን ሙስናን ማሸነፍ አልቻሉም፡፡ እንዲያውም እነሱ የሙስና ሰለባ ሆነዋል፡፡ በቀጣይም እንደ አገር አሁን ያለውን ለውጥ እንደ መልካም አጋጣሚ ወስደን ያለፈውን የፀረ ሙስና ሥርዓትና አደረጃጀት በአግባቡ ጉድለቶቹን ፈተሽን፣ የማስተካከያ ዕርምጃ ወስደን ጠንካራ የፀረ ሙስና ተቋምና ሙስናን የምንጠየፍበትና የምንታገልበት ሥርዓት መፍጠር ካልቻልን የተረጋጋ አገር፣ መንግሥትና ኅብረተሰብ ለመፍጠር ያለን ዕድል በጣም ጠባብ ነው፡፡ ለዚህ ነው በ21ኛው ክፍለ ዘመን በሙስና የተዘፈቁ መንግሥታት በሥልጣን የሚቆዩበት ጊዜ አጭር የሚሆነው፡፡

ይኼ የሆነበት ምክንያትም ካለፈው ስህተት ለመማር ያላቸው ፍላጎትና ጥረት አነስተኛ ከመሆኑ በተጨማሪ ኅብረተሰቡ ሙሰኞችን ለመሸከም የሚያስችል ጫንቃ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠበበና የዜጋው ንቃተ ህሊና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ ነው፡፡ ከለውጥ በኋላ መንግሥት ሙስና መፈጸም ቀይ መስመር ነው ብሎ ፈርጀዋል፡፡ በእኔ እምነት መፈረጁ በራሱ ጥሩ ቢሆንም ያለፈውን ስህተት አርመንና ተምረንበት ለነገ ሳንል ከልብ አምነንበት ወደ ተግባር ካልቀየርነው መንግሥትን ብቻ ሳይሆን አገራችንም እስከ ወዲያኛው እንደሚበላት ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ከአሁን በኋላ ሙስና በአገራችን ያደረሰው ጉዳት እንደ ገና እንዲደገም የሚፈልግ የኅብረተሰብ ክፍል አለ ብዬ አላምንም፡፡

በመሆኑም አሁን በሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት ሙስና በአገራችን ያስከተለውን አደጋና ሥጋት ከግምት አስገብቶ ከ1993 ጀምሮ እስካሁን ያለውን የፀረ ሙስና ትግል ሒደቱ፣ አደረጃጀቱና አጠቃላይ ሥርዓቱ በውል በመገምግም ማስተካከያ ዕርምጃ መወሰድ ያለበት ጊዜው አሁን ነው ብዬ አስባለሁኝ፡፡ ከመጪው ዓመት ጀምሮ የምንተገብራቸው አዳዲስ ዕቅዶችና ፕሮጀክቶች ከሙስና የፀዱ፣ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ቀልጣፋ እንዲሆን፣ የፍትሕ ተቋሞቻችን ከእሮሮ፣ አድልዎ በአጠቃላይ ከሙስና  ነፃ ሆነው እንዲሠሩ ማድረግ መቻል አለብን፡፡ መንግሥት ለዚህ ጉዳይ ትኩረት በመስጠት የአገሪቱ የፀረ ሙስና ትግል በሁለት እግሩ እንዲቆም የግድ የሚልበት ሁኔታ ላይ እንገኛለን፡፡ በአገራችን የሚደረጉ የፀረ ሙስና ትግሎች ትክክለኛ ቁመና ላይ መሆኑን ከሚረጋገጥበት መንገዶች አንዱና ዋነኛው መለኪያ  ጠንካራ፣ ነፃና በሕዝብ ተቀባይነት ያለው የፀረ ሙስና ተቋማት አደረጃጀት መፍጠር ነው፡፡ በጸሐፊው እምነት አሁን ያለው የአገራችን የፀረ ሙስና አደረጃጀት የተበታተነ፣ ጠንካራና ነፃነት ኖሮት ሙስናን ለመታገል የሚያስችል ቁመና ያለው ነው ብሎ አያስብም፡፡

ጽሑፉ በዓለማችን ያለው የፀረ ሙስና  ተቋማት አደረጃጀቶች ልምዶች ምን ይመስላሉ፣ አገራችን በዚህ ረገድ ያለችበት ሁኔታና ሊወሰዱ የሚገባቸው ልምዶች፣ አሁን በተጨባጭ ያሉ ተግዳሮቶቹና በቀጣይ ሊወሰዱ የሚገባቸው መፍትሔዎቹ የሚዳስስ ነው፡፡ በመንግሥት ተቋም እንደ መሥራቴ የማነሳው ሐሳብ ቅር የሚለው አካል/ግለሰብ ሊኖር እንደሚችል ብገምትም እዚህ ላነሳው የምፈልገው መሠረታዊ ሀቅ ግን ቢዚህ ርዕስ የማነሳቸው መሠረታዊ ዕሳቤዎች ፖለቲካዊ ውግንና ያለማሳየት፣ አንድን አካል ለመተቸት ወይም ለማሞገስ ካለኝ ፖለቲካዊ ዕሳቤ የመነጨ ሳይሆን በፀረ ሙስና ዙሪያ እንደሠራ ሰው፣ በአገሬ አጥብቄ እንዲኖር ከምፈልገው ትክክለኛ የፀረ ሙስና ትግል እንዲሁም መንግሥት በሚወስዳቸው የለውጥ ማሻሻያ ውስጥ የፀረ ሙስና ትግሉ ትልቅ ትኩረት እንዲያገኝ ካለኝ ፍላጎት፣ ቀናነትና ዕሳቤ መሆኑን ልብ ሊባል ይገባል፡፡ የፀረ ሙስና ትግሉ በጠንካራ አለት ላይ እንዲገነባ የመንግሥታት ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት እጅግ ወሳኝ ነውና ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ የተከበሩ አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ እንዲሁም ክብርት የሰላም ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በዚህ ጽሑፍ ለማንሳት የሞከርኳቸውን መሠረታዊና ወሳኝ ጉዳዮች አንብበው ሐሳቤን እንደሚጋሩኝና በፀረ ሙስና ትግሉ ያሉትን ክፍተቶችም ሥር ነቀል በሆነ ሁኔታ በመፍታት የአመራር ኃላፊነታቸው በብቃት እንዲሚወጡ ትልቅ ተሰፋና እምነት ስላለኝ ጭምር ነው፡፡ ዕድሉ ከተገኘም ለሦስቱ አመራሮች በአካል ቀርቤ ሐሳቤን ለማስረዳት ዝግጁ ነኝ፡፡

ለአንባብያን ግንዛቤ እንዲመች የጽሑፍ አደረጃጀት በመጀመርያ የአገራችን የፀረ ሙስና ትግሉ ታሪካዊ ዳራ በአጭሩ ከዳሰሰ በኋላ በቅደም ተከተል የዓለም አቀፍና የአገራችን የፀረ ሙስና ተቋማት አደረጃጀት ምን እንደሚመስል፣ አሁን ያሉ ዋና ዋና ተግዳሮቶች እንዲሁም በቀጣይ መንግሥታችን ሊወስዳቸው የሚገባቸው መፍትሔዎች ምን መሆን እንዳለባቸው በሚያሳይ መልክ የተደራጀ ሲሆን ጽሑፉን በሁለት ተከታታይ ዕትም ለማቅረብ እሞክራለሁኝ፡፡ 

የአገራችን የፀረ ሙስና ትግል ታሪካዊ ዳራ

ሙስና የሚለው ቃል በአገራችን በግልጽ ሕጋዊ ትርጉም ያገኘው በ1993 ዓ.ም. የወጣው የፀረ ሙስና ሕግ ቢሆንም በ1949 በወጣው የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ላይ እንደ ትቦ መቀበልና መስጠት የመሳሰሉ የሚከለክሉ የተወሰኑ የሙስና ድርጊቶች በሕግ ተደንግጎ ነበር፡፡ በአፄ ኃይለ ሥላሴ ጊዜ ሙስና በግልጽ እንዲታገል የተደራጀ ተቋም ወይም ሥርዓት ባይኖርም በተገኘው አጋጣሚ ግን በወንጀለኛ መቅጫ ሕጉ የተዳሰሱ ተግባራት ላይ የሚፈጸም ወንጀል ግን ለመቅጣት የሚደረግ ጥረት እንደነበረ ይታወቃል፡፡ በአጠቃላይ ሙስና የሚለው ቃል በኅብረተሰቡ የነበረው ግንዛቤና ትርጉም በጣም አነስተኛ ነው፡፡ በደርግ ጊዜም ሙስና ወይም ሌላ ወንጀል የፈጸሙ ባለሥልጣናት ወይም ግለሰቦች ናቸው ብሎ በትክክል ለይቶ ለመሄድ የሚያስቸግር ጊዜ የነበረ ቢሆንም ሙስናን የሚቆጣጠር ልዩ ኮሚቴና ፍርድ ቤት አቋቁሞ የሚሠራበት ሁኔታ እንደነበረ ግን ማስታወስ ተገቢ ነው፡፡ በደርግና በአፄ ኃይለ ሥላሴ የነበረው የፀረ ሙስና ትግል ጎልቶ እንዳይወጣ ያደረገው በአገሪቱ ሲነሱ የነበሩ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ የፍትሕ ጥያቄዎች ዘርፈ ብዙ የነበሩ በመሆኑ በእነዚህ ጥያቄዎች ውስጥ የሙስና ሚና ይኼን ያህል ነበር ብሎ ለማስቀመጥ አስቸጋሪ ነው፡፡ በወቅቱ አንዳንድ የሙስና ድርጊቶች መኖራቸው የማይካድ ሀቅ ቢሆንም እንደ አሁን አገራችን አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንድትገባ ሙስና የነበረው አስተዋጽኦ ሲታይ ግን በእኔ እምነት በጣም አነስተኛ ነው ብዬ እወስደዋለሁኝ፡፡

በአገሪቱ የነበሩት ችግሮች በአብዛኛው ከዴሞክራሲና ሰብዓዊ መብት ጥያቄ የተያያዙ እንጂ የሀብት መቀራመት ሊያስከትል የሚችል ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ እንዲሁም ሙስና የልማትና የፖለቲካ ጥያቄዎች እንዳይመለሱ ትልቅ እንቅፋት ሆኖ የወጣበት ሁኔታ አልነበረም ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡ በአንፃሩ በሁለቱ መንግሥታት የነበረው ሥርዓት በባህሪው ዴሞክራሲያዊ ስላልነበረ ለሙስና የመጋለጥ ዕድሉ ጠባብ ነበር ብሎ በአንድ ዕይታ ብቻ መውሰድ የተሳሳተ ቢሆንም የአገሪቷ ኢኮኖሚ በጦርነት በመድቀቁ፣ የነበረው ሀብት በእጅጉ በመንግሥት እጅ ብቻ በየነበረ በመሆኑ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ መስተጋብሩ በጣም ውስን የነበረ በመሆኑ ለሙስና የመጋለጥ ዕድሉ እንዲቀንስ አድርጎታል፡፡ በመሆኑም በወቅቱ ሙስናን የሚታገል የፀረ ሙስና ተቋም በተደራጀ መልኩ መቋቋም ነበረበት ብሎ መውቀስ እውነትን መንፈግና ነባራዊ ሀቅን አለመረዳት ይሆናል፡፡ 

የደርግ መንግሥት መውደቅን ተከትሎ የኢሕአዴግ መራሹ መንግሥት ወደ ሥልጣን እንደወጣ በአብዛኛው ተጠምዶ የነበረው ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ሪፍርሞች ማካሄድ ነበር፡፡ ከ1983 እስከ 1993 በነበረው ጊዜ የነፃ ገበያ ሥርዓት ለመገንባትና የገበያ ትስስር ለመፍጠር ጥረት የተደረገበት፣ ይኼን የገበያ ትስስርና የነፃ ገበያ ሥርዓት ሊፈጥረው የሚችል የሙስና አደጋ ከወዲሁ መከላከል ያስፈልጋል ብሎ በማመኑ የተለያዩ ማሻሻያዎች ዕርምጃዎች ወስዷል፡፡ በተለይም የመንግሥት መዋቅር ግልጽነትና ተጠያቂነት በሚያረጋግጥ መልኩ ለመዘርጋት፣ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ከአድልዎና ከሙስና በፀዳ መልኩ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል የሥነ ምግባር ማሻሻያ ንዑስ ፕሮግራም በመቅረጽ የፀረ ሙስና ትግሉን ለመጀመር የሚያስችሉ መሠረቶች ለማስቀመጥ ጥረዋል፡፡ ከአሥር ዓመት በላይ ጥናት በማድረግ፣ በወቅቱ በፀረ ሙስና ትግሉ ስኬታማ የነበሩትን ሆንግ ኮንግና ሲንጋፖር ልምድ በመውሰድ በአገር ደረጃ የፀረ ሙስና ትግሉን የሚመራ የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን በ1993 ማቋቋም ችሏል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በክልሎች የፀረ ሙስና ተቋማት እንዲቋቋሙ ተደርገዋል፡፡ ለዚህ መቋቋም መነሻው የሆነው መንግሥት ከሚያስተዳድረው የሕዝብ ሀብት በተጨማሪ በግል ዘርፉም ጠንካራ ባለሀብቶች እየተፈጠሩ በመሄዳቸው የመንግሥት መዋቅር ለሙስና ያለው ተጋላጭነት መቀነስ አለብኝ ብሎ የወሰደው ዕርምጃ ነው፡፡

የፀረ ሙስና ተቋማት ያመጡት ውጤት ሌላ ጉዳይ ሆኖ በታሪክ አጋጣሚ የኢሕአዴግ መንግሥት የፀረ ሙስና ተቋም ያስፈልገኛል ብሎ ለማቋቋም የሄደበት ርቀት፣ ተቋሙ በፀረ ሙስና ትግሉ ውጤታማ የሆኑት አገሮች ልምድ በመውሰድ የተሟላ ሥልጣን ያለው (የመከላከል፣ የመመርመርና የመክሰስ) ለማቋቋም የወሰደው ፖለቲካዊ አቋም በአዎንታ ሊወሰድ የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ በወቅቱ ይኼን ዕርምጃ መውሰዱ በቀጣይ ለነበሩ የፀረ ሙስና ትግሎች ትልቅ መሠረት ሆኖ አገልግሏል፡፡

በአጠቃላይ ከ1983 ጀምሮ ኮሚሽኑ እሰከ ሚቋቋምበት ጊዜ ከነበረው እስከ 1993 ዓ.ም. ያለው የአገራችን የፀረ ሙስና ትግል በአብዛኛው ለቀጣይ የፀረ ሙስና ትግል እርሾ የሚሆኑ ተቋማዊ አደረጃጀቶችና አሠራሮች ለመጣል ጥረትና ዝግጅት የተደረገበት እንጂ በስፋትና በተደራጀ ሁኔታ ሙስናን ለመከላከል የተሄደበት ርቀት አነስተኛ ነው፡፡ ሕዝቡ በፀረ ሙስና ትግሉ የነበረው ሚናና ተሳትፎ እጅግ አነስተኛ ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡ ለዚህ ማነስ ዋነኛ ምክንያት ሊሆን የሚችለው በወቅቱ የነበረው ኢኮኖሚያዊ አቅም ሙስናን በስፋት የሚጋብዝ ነው ብሎ መውሰድ አስቸጋሪ ነው፡፡ ወደ መጨረሻ አካባቢ ግን ሙስና ወይም ሌብነት እየተስፋፋ ነው የሚል ድምፅ ከኅብረተሰቡ እየጨመረ የመጣበት ጊዜ የነበረ በመሆኑ የፀረ ሙስና ተቋማት ወደ ማቋቋም ሥራ ተገብተዋል፡፡

    1993 ዓ.ም. እስከ 2005 ዓ.ም. ያለው የፀረ ሙስና ትግል    

የኢሕአዴግ መንግሥት ከ1993 እስከ 2007 ባለው ዜ በይፋ የፀረ ሙስና ትግሉን የሚመራና የሚያስተባር የፀረ ሙስና ተቋም በማቋቋም ሙስናን ለመታገል የሚያስችል ጅምር እንቅስቃሴ አ በፌዴራል ብቻ ሳይሆን በክልል ጭምር የፀረ ሙስና ተቋማት የተቋቋሙበት፣ በተለይም የፌዴራል ነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የተላ ነነትና በጀት ኖሮት እንዲደራጅ በሙስና ወንጀል የሚያስቀጡ ተግባራት በግልግ የተደነገጉበትሙስና እንዲታገሉ የተቋማት የበላይ ላፊዎች የሚያማክሩ የነ ምግባር መከታተያ ክፍሎች የተደራጁበት ዝቡ ሙስና የሚለውን ቃል ትክክለኛ ግንዛቤና ይታ እንዲኖረው ሰፊ ትምህርት የተሰጠበት ዜ ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡

ለመጀመርያ ጊዜ የሀብት ምዝገባ ሥርዓት ተግባራዊ ለማድረግ ጥረት የተደረገበት፣ ሙስና ለመከላከል በፊት ለፊትና በሚዲያ የተሰጡ ትምህርቶች፣ በሜጋ ፕሮጀክቶች የተደረጉ ጥናቶችና የሙስና መከላከል ሥራዎች፣ በአዲስ አበባና በፌዴራል ተቋማት በተለይም በመሬት፣ ግብርና ታክስ፣ ግዥና ሽያጭ፣ ኮንስትራክሽን ላይ የተፈጸሙ የሙስና ወንጀል ለማስመለስ የተደረጉ ጥረቶች አጠቃላይ ኅብረተሰቡ በፀረ ሙስና ትግሉ ለማሳተፍ የተደረገው ጥረት የፀረ ሙስና ትግሉ ጥሩ ጅማሮ ላይ የነበረበት ጊዜ ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡ ኮሚሽኑ በእነዚህ ጊዜያት ያደረጋቸው እንቅስቃሴዎች ኅብረተሰቡ ዓይን ውስጥ የገቡ ነበሩ፡፡ በፀረ ሙስና ትግል የመንግሥታት ቁርጠኝነት ወሳኝ በመሆኑ በወቅቱ የነበረው ድጋፍ በጣም ወሳኝ የሚባልና ተቋሙ ተሰሚነት እንዲኖረው ያገዘው ይመስለኛል፡፡ በክልሎች በተመሳሳይ ሁኔታ የፀረ ሙስና ተቋማት ተቋቁመው ከፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ጋር ተናበውና ተግባብተው ለመሥራት የሚችሉበት ዕድል ነው የነበረው፡፡

በተለይም ሙስናን ለመዋጋት የሚያስችሉ ሦስቱ የመዋጊያ ሥልቶች ማለትም የመከላከል፣ የመመርመርና የመክሰስ ሥራዎች ተበታትነው ከሚሠሩ ይልቅ በአንድ ተቋም ተጣምረው እንዲሠሩ መፍቀዱ አሁን የሚታየውን አለመናበብ በእጅጉ ያስቀረ ነበረ፡፡ በዚህ ወቅት የነበረው ትግል ከአንድ አንድ ፖለቲከኞች ይደርስ የነበረ ጫና፣ ኮሚሽኑ በተወሰነ መልኩ የነበረበት የተደራሽነት ውስንነት ካልሆነ በስተቀር በመሠረታዊነት የፀረ ሙስና ትግሉንና ተቋሙ የሚሸረሽር ችግር ነበር ብዬ ለመውሰድ እቸገራለሁኝ፡፡ ይኼ ማለት ግን ኮሚሽኑ ትግል እያደረገ በነበረበት ወቅት ሙስና እየጨመረ አልነበረም የሚል መደምደሚያ ኖሮኝ አይደለም፡፡ ኢኮኖሚው እያደገ ሲሄድ ሙስና እየጨመረ እንደሚሄድ የሚታወቅ ጉዳይ ነው፡፡

በአጠቃላይ በዚህ ወቅት የነበረው የፀረ ሙስና ትግል መሠረት የያዘ፣ ሕዝቡ በተቋሙ ላይ እምነት መጣል የጀመረበት፣ ለአፍሪካ አገሮች የልምድ ማዕከል ሆኖ ወደፊት እየመጣ የነበረ ተቋም ነው፡፡ በአጭሩ በዚህ ወቅት የነበረው የፀረ ሙስና ትግል እየተጠናከረ ወደ ውጤታማነት ያመራ የነበረ የፀረ ሙስና ትግል ነው ብዬ ባስቀምጠው ማጋነን አይሆንም፡፡

     ከ2005 ዓ.ም. ጀምሮ እስካሁን ያለው ሁኔታ

ከ1993 እስከ 2005 የነበረውን የፀረ ሙስና ትግል ባለበት ግለት መሄድ ባለመቻሉ ከ2005 በኋላ አጠቃላይ የፀረ ሙስና ትግሉን ወደኋላ የሚወሰዱ  ሁኔታዎች ታይተዋል፡፡ በመጀመርያ ደረጃ በአገሪቷ የነበረውን የገዥ ፓርቲ ውስጣዊ ፖለቲካዊ አንድነት መሸርሸር በፀረ ሙስና ትግሉም የራሱ ተፅዕኖ ፈጥሯል፡፡ በሒደትም በተወሰኑ ክልሎች የተፈጠረውን የሰላም መደፍረስና አጠቃላይ የአገሪቷ ፖለቲካዊ ሁኔታ መቀየሩ የፀረ ሙስና ትግሉ ከድጡ ወደ ማጡ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ የኮሚሽኑ የመከላከል፣ የመመርምርና የመክሰስ ሥራዎች ላይ ጫና ፈጥሯል፡፡ ቀጣይነት ያለውና ተስፋ ሰጪ የነበረውን የፀረ ሙስና ትግል በጊዜ ሒደት እየደበዘዘ መጥቷል፡፡ ከፌዴራልና ከክልል መንግሥታት ለፀረ ሙስና ተቋማት ሲሰጥ የነበረው ፖለቲካዊ ዕገዛና ድጋፍ ቀንሷል፡፡

በሒደትም ኮሚሽኑ በሜጋ ፕሮጀክቶች ላይ ሲከሰቱ የነበሩ የሙስና አዝማሚያዎችና በወቅቱ ለሙስና ያላቸው ተጋላጭነት ያሰጠናቸው ጥናቶችና የመፍትሔ ሐሳቦች ተግባራዊ ማድረግ አልቻለም፡፡ በተለይም በስኳርና ማዳበርያ ፋብሪካ፣ የውኃና መብራት ማመንጫ ፕሮጀክቶች ላይ የተፈጠረው ሁኔታ ሁላችን የምንረዳው ሲሆን ከእዚያ አለፍ ብሎ እስካሁን በአንዳንድ ፕሮጀክቶች ላይ እየተስተዋሉ ያሉ ፖለቲካዊ ጭቅጭቆች ምንጫቸው በወቅቱ የነበረው የፀረ ሙስና ትግል መዳከምና ከመንግሥት ሲሰጥ የነበረው ፖለቲካዊ ድጋፍ መቀነስ ድምር ውጤቶች ናቸው ብዬ እወስዳለሁኝ፡፡

በሒደትም የአገሪቱ ፖለቲካዊ አለመረጋጋት እየተባባሰ ሲሄድ በ2007 መጨረሻ ወራት አካባቢ በወቅቱ በነበረው መንግሥት ውሳኔ መሠረት ለፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ተሰጥተው የነበሩትን የመመርመርና የመክሰስ ሥራዎች እንዲነጠቁ ተደርገዋል፡፡ ነፃና ገለልተኛ የሆነውን ፀረ ሙስና ተቋም እንዲዳከም ተደርጎ ለገዥው ፓርቲው ቀጥታ ተጠሪ ለሆኑት ለዓቃቤ ሕግና ፖሊስ ተቋማት ነው የሰጡት፡፡ በወቅቱ ይኼን በግብታዊነት የሚወሰድ ውሳኔ ለአገር የማይጠቅም፣ የፀረ ሙስና ተቋማት ችግር ካለባቸው በጥናት ተደግፎ ክርክር ተደርጎበት መፍትሔ መስጠት እንጂ ያለምንም ጥናት በፖለቲካዊ ውሳኔ ብቻ ላይ ተመሥርቶ ውሳኔ ማሳለፍ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ልምዶች ከግምት ውስጥ ያላስገባ የችኮላ ውሳኔ እንዳይሆን በጥሞና  እንዲታይ ፓርላማ ተገኝተው ለህሊናቸው ከተከራከሩት ጥቂት ባለሙያዎች አንዱ ነኝ፡፡ መንግሥት ፖለቲካዊ ጥቅም በማስቀደም የባለሙያዎች ምክር ጆሮ ዳባ ልበስ በማለቱና በውሳኔው በመፅናቱ፤ በአንድ ተቋም ሲሠሩ የነበሩ ሥራዎች ወደ ሦስት ተቋማት እንዲበተኑ አድርጓል፡፡ የፀረ ሙስና ትግሉ ወደኋላ እንዲመለስ አድርጓል፡፡ መንግሥት በወቅቱ ነፃና ገለልተኛ የሆነ የፀረ ሙስና ተቋም አፍርሶ ለራሱ ለሚመቸው አደረጃጀት ሥራው መስጠቱ ትክክል እንዳልሆነ ሕዝቡ ቅሬታው አሁንም በተለያዩ መድረኮች እያነሳ ይገኛል፡፡ ይባስ ብሎ ተቋሙ ከነበረበት ሕንፃ እንዲወጣ መደረጉ ሲያሳድዳቸው የነበሩ ሌቦችና ሙሰኖች መሳቂያና ቁጭታቸው መወጣጫ አድርጎታል፡፡

በዚህ ምክንያት በአሁኑ ሰዓት ያለው የምርመራናና ክስ አደረጃጀት በነባራዊ ሁኔታ ይሁን ካለው ዓለም አቀፍ ልምድ አንፃር ሲታይ ሕዝቡ እምነት የሚጥልበት፣ ከመንግሥት ጣልቃ ገብነት ነፃ የሆነና የተቀናጀ የፀረ ሙስና ትግል በየደረጃው የሚካሄድበት ነው ብሎ ለመውሰድ ያስቸግራል፡፡ ነባራዊ ሀቁንና ዓለም አቀፍ ልምዶች ዓይተን ይኼ ጉዳይ ትክክል አይደለም ብለን በማስረጃ አስደግፈን በምንከራከርበት ወቅት ይኼ ትክክል አይደለም፣ ተቋሙ የራሱ ሥልጣን ለማሳበጥ ፈልጎ ነው ብለው የሚያፌዙና የፀረ ሙስና ትግሉ የበለጠ ለማዳከም ፍላጎት ያላቸው ባለሥልጣናት ቁጥር ቀላል አይደሉም፡፡ በቀጥታ ይሁን በተዘዋዋሪ ኮሚሽኑ እንዲዳከምና ተመልሶ እንዳይመጣ የሚሠሩ ኃይሎች አይጠፉም፡፡

በመሆኑም አሁን ያለው የፀረ ሙስና ተቋማት አደረጃጀት ትክክለኛና አገራችን ወደፊት ልታሳካቸው ያሰበቻቸው ዘርፈ ብዙ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ድሎች የሚደግፍ ነው ወይስ አይደለም? እየተደረጉ ያሉ የፀረ ሙስና ትግሎች ከሙሰኞችና ከፖለቲከኞች ጣልቃ ገብነት ምን ያህል የፀዳ ነው? ይኼን መሸከም የሚያስችል ነፃና ጠንካራ ተቋማዊ አደረጃጀት አለን ወይስ የለንም? ብሎ በጥልቀት መገምገም ያስፈልጋል፡፡ በእኔ እምነት አሁን ያለው የፀረ ሙስና ተቋማት አደረጃጀት ለውጥ ያስፈልገዋል ብዬ ከሚከራከሩ ባለሙያ አንዱ ነኝ፡፡ ሐሳቤን በማስረጃ ለማስደገፍና አንባብያን የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማድረግ በአሁን ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ የፀረ ሙስና ተቋማት አደረጃጀት ሞዴል ምን እንደሚመስሉ፣ ለአገራችን የትኛው ሞዴል ተስማሚ እንደሆነ አሁን ካለው አደረጃጀት ጋር አነፃፅረን ክፍተቱን በአግባቡ ማስቀመጥ ተገቢ ይሆናል ፡፡

በፀረ ሙስና ትግል ውጤታማ የሆኑ ገሮች ልምዶችና የሚከተሏቸው ሞዴሎች

በዓለም ላይ ያሉ አገሮች ሙስናን ለመታገል የተለያዩ ሞዴሎችን ተከትለው ተቋሞቻቸውን ያደራጃሉ፡፡ ከእነዚህም ሞዴሎች ውስጥ ጎላ ብለው የሚታወቁት ሦስት ናቸው፡፡ እነዚህም መካለከል ሞዴል ብቻ ትኩረት አድርገው የሚሠሩ፣ የመከላከልና የሕግ ማስከበር ሥራ በአንድ ላይ አጣምረው የሚሠሩ እንዲሁም የሕግ ማስከበር ብቻ የሚሠሩ ተብለው ይከፈላሉ፡፡ የትኛው ሞዴል ከየትኛው አገር ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት እንደሚቆራኝ እስኪ ዘርዘር አደርገን እንመልከታቸው፣

ሙስና መከላከል ሞዴል ብቻ የሚከተሉ (Corruption Prevention Model)

ይህ ዓይነት ሞዴል የሚጠቀሙ አገሮች ከሦስቱ የፀረ ሙስና መዋጊያ ሥልቶች ውስጥ የመከላከል ሥራ ብቻ ይዘው የሚሄዱ ሲሆኑ በአብዛኛው ጠንካራ የሕግ ማስከበር ሥርዓት ቀደም ብለው የፈጠሩ፣ ሙስናን የሚጠየፍ ጠንካራ የሆነ የኅብረተሰብ ባህል ያላቸው፣ የእርስ በርስ ቁጥጥር ሥርዓት በመፍጠር የተዋጣላቸው አገሮች የሚከተሉት ሞዴል ነው፡፡ ይህን ዓይነት ሞዴል መሠረት አድርገው የፀረ ሙስና ተቋም አደረጃጀት የፈጠሩ አገሮች በአብዛኛው መንግሥት ሊከተለው የሚገባውን የፀረ ሙስና ፖሊሲን ለማማከር (Advisory Role)፣ የመንግሥት ባለ ሥልጣናት ሀብት ለሕዝብ ግልጽ ለማድረግና ለመቆጣጠር፣ የፀረ ሙስና ሰርቨይ ለማካሄድ፣ የመንግሥት አጭርና ረዥም የፀረ ሙስና ዕቅድ (Anti Corruption Strategy) ለማዘጋጀት ሚና እንዲኖራቸው ለማድረግ የሚደራጁ የፀረ ሙስና አካላት ናቸው፡፡ የሙስና ወንጀሎች  ለመመርመርና ለመክሰስ የሚያስችል ሥልጣን አልተሰጣቸውም፡፡ ይህን ሥልጣን የተሰጣቸው በየአገሮቹ ውስጥ የሚገኙ የፖሊስና የዓቃቤ ሕግ ተቋማት ናቸው፡፡ ይህን ዓይነት ሞዴል የሚከተሉ አገሮች በአብዛኛው የፀረ ሙስና ኮሚሽን (ኤጀንሲ)፣ የሚል ስም ከመጠቀም ይልቅ የሥነ ምግባር ኮሚቴ፣ ሙስናን የሚከላከል ኮሚቴ ወዘተ. (Ethics committee, Corruption prevention committee, etc) የሚል ዓይነት ስም የሚጠቀሙ ናቸው፡፡ ፈረንሣይ (Central Service for Prevention of corruption)፣ አሜሪካ (Office of Government for Ethics)፣ ብራዚል (Office of Control General)፣ አልጄሪያ (National Agency for the Prevention Combating of Corruption)፣ ሰርቢያ (Anti Corruption Agency)፣ ስሎቫኒያ (Commission for Prevention of Corruption)፣ ሜቄዶንያ (State Commission for Prevention of Corruption)፣ ይህን ዓይነት ሞዴል ከሚከተሉ አገሮች ውስጥ በምሳሌ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ የመከላከል ሥራ ብቻ አትኩረው እንዲሠሩ የተሰጣቸው ኃላፊነት አንደኛ ጠንካራ፣ ከማንኛውም ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት ነፃና ሙያዊ ኃላፊነተቻውን የማያጓድሉ የፖሊስና የዓቃቤ ሕግ ተቋማት አለን ብለው ሲያምኑ ወይም ሲኖራቸው ብቻ ነው፡፡ የፖሊስና ዓቃቤ ሕግ ነፃነትና አቅም የሌላቸው ራሳቸው በሙስና የተጠለፉ ከሆኑ ግን ይኼን ሞዴል በብዛት አይመርጡትም፡፡

    የሙስና መከላከልና የግ ማስከበር ራን አጣምረው የሚጠቀሙ ገሮች ሞዴል (Multi Purpose Anti Corruption Model or The Universal Model)

ይህን ዓይነት ሞዴል የሚከተሉት አግሮች በዋናነት ሦስት የፀረ ሙስና መታገያ ሥልት ይዘው የሚሄዱ ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ የሦስት ጦር ውጊያ ሥልት ይሉታል፡፡ ይኼ ማለት ሙስና በብቃት ለመዋጋት አንደኛ ሕዝብ በሙስና ላይ እንዲዘምት የማስተማርና ማስተባበር፣ ሁለተኛ የሕግና የአሠራር ማሻሻያዎች በመውሰድ የመከላከል ሥራ መሥራት ሲሆን፣ ሦስተኛ ደግሞ በሙስና ላይ የተሳተፉ አካላት ተጠያቂ ማድረግ (በመርመር) ነው፡፡ ይህን ሞዴል የሚከተሉ አገሮች እነዚህ ሦስቱን ተግባራት ለአንድ ተቋም በመስጠት ውጤታማና የተቀናጀ የፀረ ሙስና ትግሉ እንዲኖር ያግዛል የሚል እምነት አላቸው፡፡ በእንዲህ ዓይነት አደረጃጀት በአንድ ተቋም የተከማቸ ሥልጣን እንዳይፈጠር የመከታተያ (Check and Balance) ሥርዓት እንዲኖር በተወሰነ መልኩ የክስ ሥራ ለፀረ ሙስና አደረጃጀቱ ነፃነት ተሰጥቶት እንዲሠራ/እንዲደራጅ የሚደረግበት አግባብ አለ፡፡ እዚህ ላይ ሊሰመር የሚገባው ጉዳይ ግን ይህን ዓይነት ሞዴል የሚከተሉ አገሮች ቢያንስ የፀረ ሙስና ተቋማት የምርመራ ሥራ በሥራቸው እንዲደራጅ የሚያደርጉበት ሁኔታ አለ፡፡ 

ይህን ይነት የፀረ ሙስና ሞዴል የሚከተሉት አገሮች በዋናነት የሚታወቁት ለረዥም ጊዜ በሙስና ተዘፍቀው የነበሩ/ያሉ፣ የመንግት ተቋማት ግ አከባሪ አካላት (Law Enforcement Institutions) ጭምር በሙስና የሚጠረጠሩበትና ሙስና ሰለባ የሆኑበት፣ መንግት በእነዚህ ተቋማት ራ ላይ ጣልቃ የሚገባበት ሁኔታ ሲኖር በተነፃፃሪ በኢኮኖሚ ድገት ወደ ኋላ የቀሩ፣ የዳበረ የዴሞክራሲ የሌላቸውና ዝቅተኛ የመንግት የCheck and Balance ርዓት የነበራቸው/ያላቸው አገሮች ናቸው፡፡ 

ይህን ይነት የፀረ ሙስና አደረጃት በዋናነት ከ19ኛው ክፍለ ዘመን ከቅኝ ግዛት ነፃ መውጣት በኋላ በአፍሪካ፣ በስያ፣ በላቲን አሜሪካ እንዲሁም በአውሮፓ በተወሰኑ አገሮች ተቀባይነት ያገኘና እንደ ምሳሌ የሚወሰድ የፀረ ሙስና አደረጃጀት ሞዴል ነው፡፡ ይህን አደረጃት የሚከተሉ አገሮች በዋናነት የሚታወቁት ከአስፈሚው አካል ጣልቃ ገብነት ነፃ የሆነ ተቋም እንዲደረጁ የማድረግ፣ አፈላጊ ልጣን፣ ሀብት/ በጀትና ጠንካራ የግ ማቀፍ እንዲኖራቸው ያደርጋሉ፡፡ ነፃ እና ጠንካራ የሆነ የፀረ ሙስና አደረጃጀት እንዲኖር ማድረግ መንግታት ሙስና ለመታገል ያላቸው ቁርጠኝነት ማሳያ ተደርጎ በዝቡ የሚወሰድበት ሁኔታ አለ፡፡ ገራችንም ለሙስና በጣም ተጋላጭ በመሆ ለ14 ዓመታት ያህል ይህን ሞዴል የሚከተሉ አገሮች ጭምር ልምድ በመውሰድ ሰፊ ጥናት ስታደርግ ቆይታ በ1993 ይህን ሞዴል ተግባራዊ ለማድረግ ችላ ነበር፡፡ ሆኖም ግን ከ2007 መጨረሻ አካባቢ ጀምሮ አጥጋቢ ባልሆነ ምክንያትና በተወሰደ የተሳሳተ ግንዛቤ የነበረውን የፀረ ሙስና አደረጃት የተልዕኮ ለውጥ እንዲኖረው ተደርጓል፡፡

በአሁን ሰዓት ከክስ በመመለስ ያለውን ሁለ ገብ ሞዴል የሚከተሉ አገሮች ሆንግ ኮንግና ቻይና (Independent Commission Against Corruption)፣ ሲንጋፖር (Corrupt Practice Investigation Office)፣ ሉቲኒያ (Special Investigation Service)፣ ላቲቪያ (Corruption Prevention and Combating Office)፣ ፖላንድ(Central Anti Corruption Bearo)፣ ኢንዶኒዥያ (Corruption Eradication Commission)፣ ኡጋንዳ (Anti Corruption Commission፣ ቦትስዋና (Directorate on Corruption and Economic Crime)፣ አውስትራሊያ፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ታይላንድ፣ አርጀንቲናና ኢካዶርን በምሳሌነት መጥቀስ ይቻላል፡፡ በተለይም በአፍሪካ ቦትስዋና የፈጠረችው የፀረ ሙስና ተቋም ለሌሎች አርዓያ የሚሆን ተቋም ሲሆን በአፍሪካ ሙስና በመታገል የተሻለች አገር ሆና ተቀምጣለች፡፡

ግን የማስከበር ራን ብቻ ሞዴል የሚከተሉ (Law Enforcement Model)

ይህን ይነት ሞዴል የሚከተሉ አገሮች ሙስናን ለመታገል የሚያስችላቸው በዋናነት በምርመራና ክስ ላይ ያተኮሩ ሲሆኑ ይህን ራ ለመራት በተለመደው የግ ማስበር ርዓት ማለትም በፖስና ዓቃቤ ግ ተቋማት እንዲሩ ማድረግ ነው፡፡ በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ አንዳንድ አገሮች ልዩ ዲፓርትመንት (Special Department) በማቋቋም የሚታገሉበት ሁኔታ አለ፡፡ ይህን ይነት ሞዴል ውጤታማነቱ እንየ አገር ሁኔታ ይለያል፡፡ ለምሳሌ በታዳጊ አገሮች ያሉት የፖሊስና የቃቤ ግ ተቋማት ነፃና ጠንካራ ከአሚ አካል ጣልቃ ገብነት የፀዱ ባለመሆናቸው ውጤታማ አይደሉም፡፡ እንዲያውም እንዲህ ይነት አደረጃጀት ‹‹እንያማህ ብላ በለው፣ እንዳይበላ ግፋው›› እንደሚባለው ይነት አባባል መንግት ሙስና መታገል አይፈልግም የሚለውን ሜት ለማስወገድ የሚደራጁ እንጂ መንግት ከልቡ ሙሰናን ለመዋጋት ፍላጎት ስላለው አይደለም የሚያቋቁመው ተብሎ በስፋት የሚተችበት ሁኔታ አለ፡፡ ደጉ አገሮች በገነቡት ጠንካራ የሞክራሲ ባህል፣ የግልነት ርዓት እንዲሁም በደት ባገኙት ልምድ ታግዘው ሙስናን ጨምሮ በተወሰነ ወንጀል ላይ ትኩረት ሰጥተው የሚሩበትና ውጤታማ የሆኑበት ሁኔታ አለ፡፡ ለምሳሌ እንግሊዝን ለአብነት ማንሳት ይቻላል፡፡

ሆኖም ግን ይህን ሞዴል የሚከተሉ አገሮች ሙስና መከላከል ራ ከግ ማስከበር ራው (ምርመራና ክስ) ጋር አጣምረው ለማይሩ በተለይም ታዳጊ በሆኑ አገሮች የተቀናጀ የፀረ ሙስና ትግል በማድረግ በኩል ችግር ያለባቸውና ዝብ በማነሳሳቱ ላይ አነስተኛ ትኩረት ስለሚሰጡ ውጤታማ አይደሉም፡፡ ለምሳሌ ደቡብ አፍሪካን ማንሳት ይቻላል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ ይህ አማራጭ ውጤታማ የሚሆነው ጠንካራ የግ ማስከበር ርዓት በደት የገነቡ፣ የነቃ ብረተሰብ የገነቡና ያደጉ አገሮች ላይ በስፋት ጥቅም ላይ የሚውል እንጂ እንደኛ አገር በጣም ሰፊ የግ ማስከበር ርዓት ክፍት ያለበት፣ የነቃና የተደራጀ ብረተሰብ በተሟላ ሁኔታ ባልተፈጠረበት ሁኔታ የሙስና መከላከል ራውን በአንድ ላይ አጣምሮ ለመሄድ የሚያስችል ርዓት ባለመሆኑ ይህ ሞዴል በአፍሪካ ተመራጭነቱ በጣም ያነሰ ነው፡፡ ይህን ተግባራዊ ያደረጉ አገሮችም ብዙም ለውጥ አላመጡም፡፡ ስፔንሩማንያ ክሮሽያ ኖር እንግሊዝ ደቡብ አፍሪካ ቤልጂየም ይህን ሞዴል በመከተል በምሳሌ የሚነሱ አገሮች ናቸው::

በዓለም አቀፍ ደረጃ ከላይ የተነሱ ሞዴሎች በብዛት ተግባራዊ የተደረጉ ቢሆንም ከእነዚህ ለየት ያለ ሞዴል የሚከተሉ አገሮች መኖራቸው አልቀረም፡፡ ለምሳሌ ደቡብ ኮሪያና ጋና የፀረ ሙስና ኮሚሽንና ሰብዓዊ መብትን በአንድ ላይ አቀላቅለው አደራጅተዋል፡፡ ሩዋንዳ የፀረ ሙስና፣ የሕዝብ ዕንባ ጠባቂና ዋና ኦዲተር ሥራዎች በአንድ ላይ አቀላቅላ ያደራጀችና ጠንካራ ፀረ ሙስና ተቋም በመገንባት ሒደት  ላይ የምትገኝ አገር ናት፡፡ ለእንደዚህ ዓይነት ለየት ያለ አደረጃጀት ለማደራጀት የሚሰጡት ምክንያት ደግሞ ውስን የሆነውን የሕዝብ ሀብት በአግባቡ ለመጠቀም ነው ይላሉ፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ ሙስናን የመከላከል ሞዴልና የሕግ ማስከበር ሥርዓት ሁለቱም ተግባራዊ በሚያደርጉበት ጊዜ ‹‹Multi Agency Model›› የሚከተሉ አገሮች ናቸው ይባላል፡፡ በአንድ አገር ከሁለት በላይ የፀረ ሙስና ተቋማት ማደራጀት በተለይም በታዳጊ አገሮች የሀብት ብክነት የሚያስከትል፣ ለሥልጣን ፉክክር የሚጋብዝ፣ መንግሥት ወጥ የሆነ የአመራር ሥርዓት ለመስጠት የሚቸገርበት፣ በተቋማቱ መሀል ቅንጅታዊ አሠራር ክፍተት እንዲፈጠር ዕድል የሚፈጥርና ከመንግሥት ጣልቃ ገብነት ነፃ የሆነ አንድ ጠንካራ የፀረ ሙስና ተቋም እንዳይኖር ያደርጋል በሚል በብዛት የሚተችበት ሁኔታም አለ፡፡ እንዲያውም ባላደጉ አገሮች ይህን ሞዴል መከተል እንደ “Passive Model” ወይም በአሁን ሰዓት ተቀባይነቱ እምብዛም ያልሆነ ሞዴል ተብሎ የሚወሰድበት ሁኔታ አለ፡፡

በአጠቃላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያሉ ሞዴሎች እነዚህ ሲሆኑ ከእነዚህ ውስጥ በፀረ ሙስና ትግሉ ውጤታማ የሆኑት አገሮች የትኞች እንደሆኑ፣ ለአገራችን ተመራጭ ሊሆን የሚገባ ሞዴል የትኛው እንደሆነ፣ አሁን ያለው ሞዴል ያሉትን ክፍተቶችና በፀረ ሙስና ትግሉ የፈጠራቸው ተፅዕኖዎች እንዲሁም ሊወሰዱ የሚገባቸው የመፍትሔ ዕርምጃዎች በሁለተኛው ክፍል እንመለስበታለን፡፡ እስከዚያ ቸር ወሬ ያሰማን፡፡

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር !

ከአዘጋጁ፡- ጸሐፊው በፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የሥነ ምግባር አውታሮች ማስተባበርያ ዳይሬክተር ሲሆኑ፣ ጽሑፉ የእሳቸውን አመለካከት ብቻ የሚገልጽ መሆኑን እየገለጽን በኢሜይል አድራሻቸው [email protected]  ማግኘት ይቻላል፡፡    

spot_imgspot_img
- Advertisment -

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

Related Articles