Friday, March 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልበሰኔ አጋማሽ የሚከሰተው ቀለበታዊ የፀሐይ ግርዶሽ

በሰኔ አጋማሽ የሚከሰተው ቀለበታዊ የፀሐይ ግርዶሽ

ቀን:

በሰሜናዊ ንፍቀ ክበብ ፀሐይ ከምድር ወገብ በጣም ከምትርቅበት ሁለት ቀናት አንዱ ጁን 21 ቀን 2020 (ሰኔ 14 ቀን 2012) ሲውል የዓመቱ ፀሐይ ረዥም ሰዓት የሚታይበት ቀን ይሆናል፡፡ ይህም በሰሜናዊ ንፍቀ ክበብ ባሉ አገሮች የበጋ ወቅት መጀመርያ ነው፡፡

ለምሳሌ ስዊድን ስቶክሆልም የሰኔ የመጀመርያ ሳምንት የቀኑ ብርሃን 18 ሰዓታት በላይ የሚዘልቅበት ሲሆን ይህንኑ የፀሐይ ክስተትሰመር ሶልስቲስ” በኛ አጠራር “ዕቱተ ዮን” (ፀሐይ ከምድር ወገብ የምትርቅበት በጋ) ይሉታል፡፡ በስዊድንም ሆነ በተለያዩ አገሮች እንደየባህላቸው ያከብሩታል፡፡

በስዊድን ከገና በዓል ቀጥሎ በከፍተኛ ደረጃ የሚከበረው ይኸው የበጋ መቀበያ ሲሆን ሚድሰመር ይሉታል፡፡ ወቅቱ ምድሪቱ በአበባ የምትጌጥበት፣ ዛፎች ለምልመው የሚታዩበት በመሆኑ ኅብረተሰቡ በልዩ ስሜት በተለያዩ ሥፍራዎች ያከብረዋል፡፡  ዘንድሮ ኮቪድ-19 ካላወከ በስተቀር በዓሉን እንደሁሌው ብቻ ሳይሆን ዘንድሮ በዕለቱ ይከሰታል ተብሎ ከሚጠበቀው ቀለበታዊ የፀሐይ ግርዶሽ ጋር የሚያከብሩት ይሆናል፡፡

ቀለበታዊው ግርዶሽ የሚታየው ሰኔ 14 ቀን ጨረቃ በፀሐይና በምድር መካከል ስትሆንና  ፀሐይ ሙሉ በሙሉ ተጋርዳ ብርሃን መስጠት ሳትችል በሚፈጠር ክስተት ነው፡፡ በሁለቱ መካከል ተጣጥማ በምትታይበት ወቅት በፀሐይ ዙርያ ሆና ቀለበታዊ ቅርፅ ታሳያለች፡፡

በሰኔ አጋማሽ የሚከሰተው ቀለበታዊ የፀሐይ ግርዶሽ

 

ኢንዲያ ታይምስ እንደዘገበው፣ የፀሐይ ግርዶሹአፍሪካ ክፍሎች ኢትዮጵያን፣ ማዕከላዊ አፍሪካን እና ኮንጎ ጨምሮ ይታያል ፡፡ በተጨማሪም በሰሜን ፓኪስታን እና ቻይናን ጨምሮ በአብዛኛዎቹ ሰሜን ሕንድ ውስጥ ይከሰታል፡፡

የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሰኔ 14 ቀን 2012 .ም. በኢትዮጵያ ቀለበታዊ የፀሐይ ግርዶሽ እንደሚከሰት ለመገናኛ ብዙኃን አስታውቋል፡፡ ከምዕራብ እስከ ሰሜን ምሥራቅ ኢትዮጵያ የሚታየውና የቀለበት ቅርፅ እንደሚኖረው የተገለጸው የፀሐይ ግርዶሽ ከጠዋቱ 1245 እስከ እኩለ ቀን (633) እንደሚቆይና ከረፋዱ 340 ደግሞ 38 ሴኮንዶች ጨለማ እንደሚሆን ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሰሎሞን በላይ (ዶክተር) ለአብመድ ገልጸዋል፡፡

 በተለይም በከፊል ጎጃም፣ ጎንደርና ወሎ የሚከሰት ሲሆን ከሌሎች ካባቢዎች ጨለማ ይሆናል፡፡  ከሌሎች ቦታዎች በተለየ መልኩ በላሊበላ ከተማ ድቅድቅ ያለ ጨለማ እንደሚሆን ተገልጿል፡፡ እንደዘገባው፣ ቀለበታዊው ግርዶሽ ከኮንጎ ተነስቶ ሱዳን፣ የመን፣ ኦማን፣ ፓኪስታንና ህንድ እንደሚከሰት፣ቻይና እና ኢትዮጵያ ተከስቶ ፓስፊክ ውቅያኖስ አካባቢ እንደሚያበቃም ይጠበቃል፡፡

በዋና ዳይሬክተሩ አገላለጽ፣ በኢትዮጵያ ለየት ያለ ክስተት እንደሚኖር ዓለም አቀፍ ተመራማሪዎችና ቱሪስቶች ቀደም ብለው ያውቁ ስለነበር ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት ዕቅድ ይዘው ነበር፡፡ ኢትዮጵያም በከፍተኛ ደረጃ መልካም ገጽታዋን የምታስተዋውቅበት አጋጣሚ ስለሆነ ለዚህ ተግባር ብሔራዊ ኮሚቴ ተቋቁሞ ነበር፡፡ ምንም እንኳን ዓለም አቀፍ ተመራማሪዎችና ጎብኝዎች በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ባይመጡም ኢንስቲትዩቱ ከፌዴራልና ከአማራ ክልል መንግሥት እንዲሁም ከኮማንድ ፖስት ጋር በመነጋገር በላሊበላ ከተማ ሊከበር እንደሚችል ዋና ዳይሬክተሩ ማመላከታቸውን አብመድ ዘግቧል፡፡

ከረጅም ዓመታት በኋላ የሚከሰተውን ታሪካዊ ክስተት ሕዝብ ሳይደናገጥ በዕድለኛነት ስሜት በነፃነት፣ በንቃትና በጥንቃቄ ሊከታተለው እንደሚገባም መክረዋል፡፡

ዘገባው አያይዞም ዋና ዳይሬክተሩ ተማሪዎች፣ ተመራማሪዎች፣ ማኅበረሰቡ ክስተቱ ሊያመልጣቸው እንደማይገባ፣ በሚከሰትበት ጊዜ ያለ አጋዥ መሣሪያ በባዶ ዓይን ማየት እንደማይገባም መክረዋል፡፡ ክስተቱ በተፈጥሮ ላይ ምንም ተፅዕኖ እንደማይኖረውና ምናልባት የአየር ንብረት ለውጥ ሊኖር እንደሚችልም አመላክተዋል፡፡

በኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም በ16ኛው፣ በ17ኛውና በ18ኛው ምዕት ዓመት ፀሐይ ሙሉ በሙሉ ተጋርዳ እንደነበር ተመዝግቧል፡፡ 

በጎርጎርዮሳዊው የዘመን ቀመር መሠረት በሰሜናዊ ንፍቀ ክበብ የበጋ (ሐጋይ) ወቅት ጁን 21 (ሰኔ 14) ሲገባ ከምድር ወገብ በሚገኙ አገሮች ይፋዊ ባይሆንም የክረምት ወቅት ይጀምርበታል፡፡ በኢትዮጵያ ባሕረ ሐሳብ መሠረት ግን ክረምት በይፋ የሚገባው ወቅቱን ከፀደይ የሚረከበው ሰኔ 26 ቀን ነው፡፡

ሶልስቲስ የሚከሰተው መሬት በፀሐይ ዙሪያ 23.4 ዲግሪ ስታዘነብል/ስታጋድል በመሆኑ የሰሜንና የደቡብ ንፍቀ ክበቦች በዓመት የሚያገኙት የፀሐይ ብርሃን እኩል አይሆንም፡፡

በሰሜን ንፍቀ ክበብ ከመጋቢት እስከ መስከረም የፀሐይ ብርሃን የሚያዘነብል ሲሆን፣ መፀውና በጋ ይውሉበታል፡፡ ከመስከረም እስከ መጋቢት ደግሞ ፀሐይ ትርቅባቸውና ፀደይና ክረምት ይውሉበታል፡፡ በደቡባዊ ንፍቀ ክበብ የሚውሉት ወቅቶች በተቃራኒው ይሆናል፡፡ በባሕረ ሐሳባችን እንደተጻፈው ‹‹በኛ ክረምት ሲሆን በእነሱ በጋ፣ በኛ መፀው ሲሆን በእነሱ ፀደይ፤›› እንዲል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኩባንያ አስተዳደር ለኢትዮጵያ ባንኮች ውጤታማነት

የጠቅላላ ጉባኤ፣ የጥቆማና ምርጫ ኮሚቴ፣ የተቆጣጣሪ ቦርድ፣ የዳይሬክተሮች ቦርድና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...