Tuesday, February 27, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ፖሊስ ባንክ ለመዝረፍና በሕገወጥ ድርጊቶች ተሰማርተው አገኘኋቸው ያላቸውን ማሰሩን አስታወቀ

ተዛማጅ ፅሁፎች

በሰባት ቀናት ውስጥ ከ246 በላይ ንግድ ቤቶች ተዘግተዋል

ሕግ በመጣስና ደንብ በመተላለፍ 8,422 አሽከርካሪዎች ተቀጡ

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የሰዎችን እንቅስቃሴ በማጥናት የተለያዩ ትናንሽ ቅሚያዎችና የዘረፋ ሙከራዎች ቢኖሩም፣ ሰሞኑን ግን በውድቅት ሌሊት ባንክ ለመዝረፍ ተሰማርተው የነበሩና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመተላለፍ በሕገወጥ ተግባራት ላይ ተሰማርተው የተገኙ በርካታ ሰዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ምንም እንኳን የወንጀል ድርጊቶች ካለፈው ዓመት አንፃር ሲነፃፀሩ 17 በመቶ የቀነሱ ቢሆንም፣ አልፎ አልፎ የንጥቂያና ከባድ ዝርፊያ የማድረግ ሙከራዎች መኖራቸውን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፈንታ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ባለፈው ሳምንት ውስጥ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ውስጥ የሚገኘውን የኅብረት ባንክ ሊዘርፉ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡ ዝርፊያውን ያቀነባበረው የባንኩ የጥበቃ ባልደረባ መሆኑን፣ ከጓደኛው ጋር በሥራ ላይ ላይ እያሉ አብሮት የነበረው የሥራ ባልደረባውን በማሰርና በመሣሪያ በማስፈራራት፣ ከውጭ የቀጠራቸውን ግብረ አበሮቹን በር ከፍቶ ማስገባቱን ኃላፊው አስረድተዋል፡፡

ገንዘብ ያለበትን ካዝና ለመስበር ሲታገሉ፣ ታስሮ የነበረው ጥበቃ አምልጦ በመውጣት ፖሊሶች ጠርቶ እጅ ከፍንጅ እንዳስያዛቸው አክለዋል፡፡ በሌሎችም አካባቢዎች የማታለል ወንጀሎች እየተፈጸሙ ቢሆንም፣ በአሁኑ ጊዜ በተፈጠረው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ወጣቶች ወንጀለኞችን እያጋለጡ መሆኑን ኮማንደር ፋሲካ ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተቀመጡ ድንጋጌዎች በመተላለፍ ከ246 በላይ ሆቴሎችና የመጠጥ ግሮሰሪዎች፣ አረቄ ቤቶችና ጠጅ ቤቶች መዘጋታቸውን አስረድተዋል፡፡ በ110 የጫትና የሺሻ ቤቶች፣ የአራት የቪዲዮ ቤቶችና በሌሎች ሥፍራዎች አዋጁን በመቃረን አንድ ላይ ተሰብስበው ሲጠጡ፣ ሲቅሙና ሺሻ ሲያጨሱ የተገኙ በርካታ ሰዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ተመክረው ቢለቀቁም፣ የቤቶቹ ባለቤቶች ግን ፍርድ ቤት እየቀረቡና እየተቀጡ መሆኑን ኮማንደር ፋሲካ ገልጸዋል፡፡

አዋጁን በመተላለፍ ትርፍ ሰው የጫኑ፣ ያለ ታሪፍ ያስከፈሉና ደንብ ተላልፈው የተገኙ 8,422 አሽከርካሪዎች መቀጣታቸውንም አክለዋል፡፡ ኅብረተሰቡ ግን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ እያደረገ ያለውን ትብብር በአዎንታዊ ጎኑ አውስተዋል፡፡

ባለፈው ሳምንት በኮሮና ቫይረስ ተይዘው የተገኙ ሰዎች በፖሊስ ጣቢያ ታስረው የነበሩ ናቸው ስለመባሉ ተጠይቀው፣ አንዳችም የፖሊስ ባልደረባ በቫይረሱ አለመያዙን እንጂ ስለተባለው ነገር የሚያውቁት ነገር እንደሌለም ኮማንደሩ ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች