Sunday, July 14, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየክለቦች ቅሬታ አቀራረብ ደንብና መመሪያ አለመከተሉን የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ገለጸ

የክለቦች ቅሬታ አቀራረብ ደንብና መመሪያ አለመከተሉን የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ገለጸ

ቀን:

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፈዴሬሽንና የፕሪሚር ሊጉ አክሲዮን ማኅበር አመራሮች በሚያሳልፏቸው ውሳኔዎች ቅር የሚሰኙ ክለቦች፣ ቅሬታቸውን የሚያቀርቡበት መንገድና አካሄድ መመርያና ደንብን አለመከተሉን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡ ክለቦች ቅሬታቸውን የሚያቀርቡት ለሦስተኛ ወገን (መገናኛ ብዙኃን) በመሆኑ ለተቋሙ አስተዳደራዊ  ውሳኔ አሰጣጥና አካሄድ ላይ አስቸጋሪ እንደሆነበት የሚናገሩ አሉ፡፡

በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨምሮ የ2012 ዓ.ም. ውድድሮች ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የሚያስተዳድራቸው ከፍተኛና ብሔራዊ ሊግ፣ እንዲሁም በተዋረድ የሚገኙ የአንደኛና ሁለተኛ ዲቪዚዮን የጨዋታ መርሐ ግብሮች ውጤት ሙሉ በሙሉ እንዲሰረዙ ተደርጓል፡፡

የፕሪሚየር ሊጉን በሚመለከት ውሳኔው የሚመለከተው የ2012 ውድድር ዓመት ከመጀመሩ አስቀድሞ የተቋቋመው ሊጉን የሚያስተዳድረው የአክሲዮን ማኅበር ሲሆን፣ ከከፍተኛው ሊግ እስከ አንደኛና ሁለተኛ ዲቪዚዮን ያለውን በሚመለከት ደግሞ ውሳኔው የተላለፈው በብሔራዊ ፌዴሬሽኑ እንደሆነ የጽሕፈት ቤቱ ጊዜያዊ ኃላፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን ያስረዳሉ፡፡

በዚሁ ውሳኔ መሠረት የተሰረዘው የውድድር ዓመቱን ውጤት ተከትሎ ከሁሉም አቅጣጫ የብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የአሠራር ጉድለትና ክፍተት ተደርጎ እየተነገረ መሆኑን የሚናገሩት አቶ ባህሩ፣ አንዳንዶቹ ቅሬታዎችና ክሶች ቢያንስ ክለቦች በተዋረድ እንዲተዳደሩባቸውና ራሳቸው ያጸደቋቸው መመርያና ደንቦችን ተከትለው የሚቀርቡ አይደሉም ይላሉ፡፡ የከፍተኛውም ይሁን የብሔራዊ ሊጉ ክለቦች በኮቪድ 19ኝም ሆነ በሌላ በደል ደርሶባቸው ሊሆን ይችላል፡፡ መሆን ያለበት የበደሉን ዓይነትና ምንነት ጠቅሶ በፌዴሬሽኑ ለሚመለከተው ዲፓርትመንት ማቅረብ ሲገባ የሚያቀርቡት ለሦስተኛ ወገን (መገናኛ ብዙኃን) ነው፡፡ እንዲህ ያለው አሠራርና አካሄድ ደግሞ ለተቋሙ የፍትሕ ሥርዓት አመቺ አይደለም፤” በማለት ክለቦቹ እየሄዱበት ያለው መንገድ ይተቻሉ፡፡

ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ፍጹም እንዳልሆነ እንደሚናገሩት አቶ ባህሩ አገላለጽ፣ አንድ ክለብ በፌዴሬሽኑም ሆነ በሌላ አካል በደል ሲደርስበት ቅሬታውን ለማንና እንዴት ማቅረብና መክሰስ እንዳለበት ሁሉም በጋራ ባጸደቁት መመርያ ደንብ በግልጽ ተቀምጧል፡፡ ይሁንና ከሰሞኑ ከ2012 ዓ.ም. ውድድር መሰረዝ ጋር ተያይዞ የሚነገሩትን ጨምሮ አንድም ክለብ መመርያና ደንብ ተከትሎ ቅሬታ የሚያቀርብ የለም ያሉት ኃላፊው ይህ አካሄዱ ለራሳቸው ለክለቦቹ ውጤታማነትም ሆነ ለብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የፍትሕ ሥርዓት አስቸጋሪ ነው በማለት ክለቦች ቢያንስ ለሚመሩበት መመርያና ደንብ ሊገዙ እንደሚገባ ያስረዳሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሚዲያው በሕዝብ የህሊና ችሎት ከተዳኘ በቂ ነው!

መሰንበቻውን ድንገት ሳይታሰብ ያለ ማስጠንቀቂያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ...

የባህር በር ጉዳይ

በታምሩ ወንድም አገኘሁ ድሮ ድሮ ገና ልጅ ሆኜ ፊደል እንደቆጠርኩ...

አገሩ ፖለቲካዊ ስክነትና መደማማጥ ያስፈልገዋል

በንጉሥ ወዳጀነው    ኢትዮጵያ የሁላችንም የጋራ ቤት ነች፡፡ ‹‹ጥያቄዬ ተመለሰልኝ››፣...

የመንግሥት የሰብዓዊ መብት ተቋም ለምን የመንግሥት ሚዲያን ማስተማር አቃተው

በገነት ዓለሙ የአገራችን የ2016 የበጀት ዓመት መሰናበቻና የአዲሱ የ2017 በጀት...