Friday, March 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ለፀረ ኮሮና ዘመቻ 55.4 ሚሊዮን ብር አሰባሰበ

ማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ለፀረ ኮሮና ዘመቻ 55.4 ሚሊዮን ብር አሰባሰበ

ቀን:

የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር መንግሥት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የሚያደርገውን ጥረት ለማገዝ የሚውል 55.4 ሚሊዮን ብር፣ ከተለያዩ የማዕድንና የነዳጅ ኩባንያዎች አሰባሰበ፡፡

ከዘርፉ የሥራ ባህሪ አኳያ ቫይረሱ አስከፊ ጉዳት እንዳያደርስ አስቀድሞ ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወነ እንደሆነ፣ የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ይህን ጥረት በበላይነት የሚያስተባብር የማዕድንና ነዳጅ ዘርፍ የኮሮና ቫይረስ መከላከልና መቆጣጠር ግብረ ኃይል ተቋቁሞ፣ ሥራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

ግብረ ኃይሉ ያስተላለፈውን ጥሪ በመቀበል በማዕድንና ነዳጅ ሥራዎች የተሰማሩ ኩባንያዎች፣ በሁለት ዙር በአጠቃላይ 55.4 ሚሊዮን ብር ድጋፍ እንዳደረጉ ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

በመጀመርያው ዙር የማዕድንና ነዳጅ ኩባንያዎች 52 ሚሊዮን ብር በገንዘብና በዓይነት ገቢ ማድረጋቸውን፣ በሁለተኛው የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ስድስት ኩባንያዎች 3.4 ሚሊዮን ብር በጥሬ ገንዘብ ወደ ባንክ ገቢ እንዳደረጉ ተገልጿል፡፡

ኒውሞንት ቬንቸርስ 50,000 ዶላር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተው የኮሮና መከላከል ትረስት ፈንድ የባንክ ሒሳብ ገቢ ሲያደርግ፣ የተባበሩት ፔትሮሊየም 500,000 ብር፣ ያራ ዳሎል 520,000 ብር፣ ጂፒቢ ሪሶርስስ 540,000 ብር፣ ኑቢያን ጎልድ ኤክሰፕሎሬሽን 50,000 ብር፣ ጄአር ፔትሮሊየም 129,600 ብር ገቢ እንዳደረጉ ተገልጿል፡፡

የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር በሁለተኛው ዙር መዋጮውን ገቢ ላደረጉ ኩባንያዎች፣ የዕውቅና ሰርተፊኬት ሐሙስ ግንቦት 7 ቀን ሰጥቷል፡፡ የብሔራዊ የድጋፍ አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ምሥጋኑ አረጋ፣ የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር) እና ሚኒስትር ዴኤታ ኮኦንግ ቱትላም (ዶ/ር) የዕውቅና ሰርተፊኬቱን ለኩባንያ ተወካዮች ሰጥተዋል፡፡ በሥነ ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት አቶ ምሥጋኑ፣ የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር አርአያነት ያለው ተግባር በማከናወን ላይ ነው ብለዋል፡፡ የኮሮና ወረርሽኝ የሰው ሕይወት እየጎዳ በአገር ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረ እንደሆነ የገለጹት አቶ ምሥጋኑ፣ መንግሥት ላስተላለፈው ጥሪ ፈጣን ምላሽ ለሰጡ የማዕድንና ነዳጅ ኩባንያዎች ምሥጋና አቅርበዋል፡፡

‹‹ይህን ፈታኝ ወቅት እንደ አገር ተባብረን፣ ብሔራዊ አንድነታችንን አጠናክረን ተሳስበን ማለፍ አለብን፡፡ በሽታውን በቁጥጥር ሥር አድርገን ወደ ተለመደው ሕይወታችን እስክንመለስ ድጋፋችሁ ይቀጥል፤›› ያሉት አቶ ምሥጋኑ፣ የማዕድን ኤክስፖርት እንዳይቀዛቀዝ ኩባንያዎች ጥረት እንዲያደርጉ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር) ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ የማዕድን ኩባንያዎች ሁለት ዓይነት አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡ ‹‹አንዱ ለብሔራዊ ኮሚቴው ድጋፍ እያደረጉ ነው፡፡ ሁለተኛ የውጭ ምንዛሪ በማስገባት ለኢኮኖሚው የበኩላቸውን አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ ይገኛሉ፤›› ብለዋል፡፡

በማዕድን ልማት ዘርፍ ሰፊ የኢንቨስትመንት ዕድል ቢኖርም የአገር ውስጥ ባለሀብቶች እስካሁን ያላቸው ተሳትፎ ውስን መሆኑን የገለጹት ሳሙኤል (ዶ/ር)፣ ተፈጥሮ የለገሰችውን የማዕድን ሀብት በማልማት እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...