Monday, March 27, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትኦሊምፒክ ኮሚቴ ለብሔራዊ ፌዴሬሽኖች የገንዘብ ድጋፍ ሊያደርግ ነው

ኦሊምፒክ ኮሚቴ ለብሔራዊ ፌዴሬሽኖች የገንዘብ ድጋፍ ሊያደርግ ነው

ቀን:

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ለብሔራዊ ፌዴሬሽኖች የገንዘብ ድጋፍ ሊያደርግላቸው መሆኑ ታወቀ፡፡ ድጋፉ ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች በሚያቀርቡት ምክረ ሐሳብ ላይ የተመሠረተ እንደሚሆንም ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው አስታውቋል፡፡

የሁሉም ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ውቅር የሆነው የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በተለይ ለሪፖርተር እንደገለጸው፣ ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ተቋማቶቻቸው የሚገኙበትን ሁኔታ የሚያሳይ ምክረ ሐሳብ እንዲያቀርቡ፣ ምክረ ሐሳቡን መነሻ አድርጎ የገንዘብ ድጎማ እንዲሰጣቸው ሥራ አመራር ቦርዱ ወስኗል፡፡ በዚሁ መሠረት ብዙዎቹ ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች የተጠየቁትን ምክረ ሐሳብ ሲያቀርቡ፣ ያላቀረቡም እንዳሉ የብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው ዋና ጸሐፊ አቶ ዳዊት አስፋው ተናግረዋል፡፡

ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴው ለእያንዳንዱ ፌዴሬሽን ምን ያህል የገንዘብ ድጎማ እንደሚሰጥ ይታወቃል ወይ? ለሚለው አቶ ዳዊት፣ ‹‹ሁሉ ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ምክረ ሐሳባቸውን አጠቃለው ካቀረቡ በኋላ ያንን መሠረት በማድረግ ነው የገንዘብ መጠኑ የሚወሰነው፡፡ ቀደም ሲል እንደተናገርኩት የተወሰኑ ፌዴሬሽኖች ምክረ ሐሳባቸውን አላቀረቡም፡፡ እንዲያቀርቡ ጥሪ ተደርጎላቸዋል፣ ድጋፉም እንደሚቀርበው ምክረ ሐሳብ ይወሰናል፤›› ብለዋል፡፡

‹‹ሁሉም እንደሚያውቀው በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የቶኪዮ ኦሊምፒክ ጨምሮ በርካታ ስፖርታዊ ክንውኖች ተራዝመዋል፡፡ ችግሩ ባይከሰት ኖሮ ኢትዮጵያ በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ ለዓመታት ከምትታወቅበት አትሌቲክስ በተጨማሪ ለመጀመርያ ጊዜ በወርልድ ቴኳንዶ እንዲሁም በብስክሌትና የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ዋናን ተደራሽ ለማድረግ በሚሰጠው ኮታ መሰረት በአንድ ወንድና በአንድ ሴት ዕድሉን አግኝታ ነበር፤›› የሚሉት አቶ ዳዊት ኦሊምፒክ ኮሚቴ የገንዘብ አቅም የሌላቸው ስፖርቶችና ስፖርተኞች ወቅታዊ ብቃታቸው እንዳይወርድ ዕገዛ ማድረግ እንደሚጠበቅበት ይናገራሉ፡፡

በኢትዮጵያ የተለያዩ ስፖርቶች ለማሳደግና ለማስፋፋት የተቋቋሙ ከ26 በላይ ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች እንደሚገኙ ይታመናል፡፡ ይሁንና ተቋማቱ ዓለም አቀፉ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከተከሰተ ጀምሮ ከማናቸውም ዓይነት ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ተቆጥበዋል፡፡ በኅብረተሰቡ ዘንድ በስፋት የሚዘወተሩት ስፖርቶች ከሚመሩ ፌዴሬሽኖች በቀር ብዙዎቹ በወረርሽኙ ምክንያት ከቢሮ ይልቅ ቤት ውስጥ መዋል ከጀመሩ መሰነባበታቸው ይታወቃል፡፡

ሕጋዊ ሰውነት አግኝተው በአገሪቱ በመንቀሳቀስ ላይ ከሚገኙ ብሔራዊ ፈዴሬሽኖች የኢትዮጵያ አትሌቲክስና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ካልሆኑ ሌሎቹ በአጠቃላይ ከመንግሥት ቋት በሚለቀቅላቸው አነስተኛ በጀት የሚንቀሳቀሱ ናቸው፡፡

መንግሥት ከሚመደብላቸው በጀት ይልቅ ከስፖርት ኮሚሽንና ከኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ የተሻለ የገንዘብ ድጎማ እንደሚደረግላቸው የሚናገሩት ብሔራዊ ፌዴሬሽኖቹ፣ ስፖርት በቂ ፋይናንስ ታክሎበት ካልሆነ በስተቀር ብሔራዊ በሚለው ስያሜ ብቻ ትርጉም ያለው እንቅስቃሴና ውጤት ማስመዝገብ እንደማይችል ጭምር ያምናሉ፡፡

የፌዴሬሽኖቹ አመራሮችም የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ለወትሮ በዓመት አንድ ጊዜ እንደ አስፈላጊነቱ ይሰጥ የነበረው የሙያ ማሻሻያ ኦሊምፒክ ሶሊዳሪቲ በወረርሽኙ ምክንያት ስለመቋረጡ ጭምር ይናገራሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...