Thursday, June 8, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልዒድ አልፈጥር

ዒድ አልፈጥር

ቀን:

የዘንድሮው ረመዳን ከወትሮው ለየት ያለ ነገር ያጋጠመበት ነገር ቢኖር የሚጠቀሰው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በዓለም መንሰራፋቱ ነው፡፡ አማኞች በቤታቸው እንዲወሰኑ ጾም ጸሎታቸውን በመስጊድም ሆነ በአደባባይ እንዳያደርጉ የታቀቡበት ነበር፡፡

መጾም በሕዝበ ሙስሊሙ ዘንድ ከእስላማዊ አስተምህሮ ከአምስቱ ምሰሶዎች አንዱ ነው፡፡ ሌሎቹ እምነት፣ ጸሎት፣ ዘካ (ችሮታ) እና ወደ መካ በሕይወት ዘመን ቢያንስ ለአንድ ጊዜ መጓዝን የያዙ ናቸው፡፡

በተፈጠረው ወረርሽኝ ምክንያት ወደ መካ መጓዝና መሳለም ተሰናክሏል፡፡ ሚያዝያ አጋማሽ ላይ የተጀመረው የዘንድሮው የረመዳን ጾም ግንቦት 15/16 አብቅቷል፡፡ በዓሉ በተለያዩ አገሮች በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ እየተከበረ ነው፡፡ የዒድ ትርጉም ‹‹በዓል››፣ ሙባረክ ደግሞ ‹‹የተባረከ›› ማለት ሲሆን በመልካም ምኞት መግለጫነት ዒድ ሙባረክ አገልግሎት ይውላል፡፡

በሕዝበ ሙስሊሙ የረመዳን ወር በዓመተ ሒጅራ ካሉት ወሮች መካከል ዘጠነኛው ሲሆን የተቀደሰ ወር የሚያሰኘው ሙሉውን የጾም ወር መሆኑ ነው፡፡ ቀጣዩ 10 ወር ሸዋል በሚብትበት ዕለት የዒድ አልፈጥር በዓል ይውላል። ይህ በጨረቃ 354 ቀን ዑደት ላይ የተመሠረተው ዓመተ ሒጅራ፣ ዘንድሮ ጾሙንረመዳን 30 ቀን 1441 ዓመተ ሒጅራ” (ግንቦት 15 ቀን 2012) ላይ አብቅቶ በማግሥቱሸዋል 1 ቀን” (ግንቦት 16 ቀን) ዒዱ በዓለም ዙርያ በተከታዮቹ ዘንድ ተከብሯል፡፡

‹‹ቁርዓን የዚህች ዓለም ሕይወት መመሪያ ነው፡፡፡ ቀጥተኛና ግልጽ የሆነ መጽሐፍ ነው፡፡ ቁርዓን ለያዘውና ለተገበረው ቀናኢ መንገድ ነው፡፡ ቅዱሱ መጽሐፍ የሚለውን ተከትሎ የተፈቀደውን (ሀላሉን) ላደረገ፣ የተከለከለውን (ሀራሙን) ለራቀ ብርሃን ነው፡፡ በእውነትና በውሸት መካከል ያለውን የሚለየው ቁርዓን ነው፡፡ ቁርዓን ጥብቅ ቃል ነው›› ልዩ የረመዳን መገለጫዎች በሚል በአንድ እስላማዊ ድረ ገጽ ላይ ከሠፈረ ጽሑፍ ተቀንጭቦ የተወሰደ ነው፡፡

የእስላም መሠረት የሆነው ቁዱስ ቁርዓን የወረደው በረመዳን ወር ነው፡፡ በጨረቃ ቀን አቆጣጠር ዘጠነኛ ወር ላይ የሚውለው የረመዳን ወር፣ በሃይማኖቱ ተከታዮች ዘንድ የወራት ሁሉ ቁንጮ ተደርጎ ይታሰባል፡፡ ከእስላም ማዕዘናት አንዱ የሆነው ፆም የሚተገበረውም በዚሁ በረመዳን ወር ነው፡፡ በዚህ ቅዱስ ወር የጀነት (የገነት) በሮች ይከፈታሉ ሰይጣንም ይታሠራል፡፡ መልካምነት ጎልቶ የሚሠፍንበት፣ የፈጣሪ ምሕረት የሚበዛበት ወር ነው፡፡ ረመዳን ክፉ ማሰብና መጣላት ቀርቶ የተጣሉ ይቅር የሚባባሉበት መልካም ወር ነው፡፡

በኢትዮጵያ ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን የዒድ ሰላትን በየቤቱ መስገድ በመስገድ አክብሮታል፡፡ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እድሪስ 1441ኛውን ዒድ አል ፈጥር በማስመልከት በዋዜማው ባስተላለፉት መልዕክት፣ ሕዝበ ሙስሊሙ የዘንድሮውን ኢድ ሲያከብር የኮሮና ቫይረስ የተከሰተበት  ወቅት  በመሆኑ በሽታው እንዳይሠራጭ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበታል ብለዋል።

በዓሉ ሲከበርም የተቸገሩትን በመርዳት፣ በመተጋገዝና በመተዛዘን እንዲሁም አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ መሆን እንደሚኖርበትም ሳያስገነዝቡ አላለፉም፡፡

በሌላ በኩልም የጤና ሚኒስትር ሊያ ታደሰ (ዶ/ር) ባስተላለፉት መልዕክት፣ ሕዝበ ሙስሊሙ ዒድ አልፈጥርን ሲያከብር ለኮሮና ቫይረሰ ተጋላጭ እንዳይሆን መጠንቀቅ እንዳለበት አሳሰበዋል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት ሕዝበ ሙስሊሙ በተናጠልና በቤት ውስጥ ሲሰግዱ መቆየታቸውን አስታውሰው፣ ይህንኑ ጥንቃቄ በዒድ አከባበር ወቅትም መጠናከር እንዳለበት፣ በክብረ በዓል ወቅት እንቅስቃሴዎች ስለሚበዙ በማንኛውም ጊዜ የፊት መሸፈኛን በማድረግና የእጅ ንጽህናን መጠበቅ እንደሚገባም ሳያስገነዝቡ አላለፉም፡፡             

በክብረ በዓሉ ወቅት የሚበሉ ምግቦችን ማብሰል እንደሚገባና እርድም በከፍተኛ ጥንቃቄ  መፈጸም እንዳለበትም አሳስበዋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ከቀጣዩ ዓመት በጀት ውስጥ 281 ቢሊዮን ብሩ የበጀት ጉደለት ነው ተባለ

ለቀጣዩ በጀት ዓመት ከቀረበው 801.65 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ በጀት...

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ከተለመደው አሠራር ወጣ ያለውን ‹‹የወደፊት ግብይት›› ሥርዓት በይፋ አስጀመረ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ከተለመደው የማገበያየት ተግባሩ ወጣ ያለና በኢትዮጵያ...

የባንክ ማቋቋሚያ መሥፈርት እንደሚጠነክር ሚኒስትሩ ተናገሩ

 ባንኮች ስለውህደት እንዲያስቡም መክረዋል በኢትዮጵያ ውስጥ ባንክ ለማቋቋም የሚያስፈልገው መሥፈርት...