Saturday, February 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊለተፈናቃይ አባወራዎች የታሰበው የስድስት ሚሊዮን ብር ዕርዳታ

ለተፈናቃይ አባወራዎች የታሰበው የስድስት ሚሊዮን ብር ዕርዳታ

ቀን:

አረጋውያን ለተለያዩ የኅብረተሰብ የጤና አደጋዎች ተጋላጭ ናቸው፡፡ ድህነቱም አደጋው በይበልጥ እንዲባባስ ያደርገዋል፡፡ እንደ እነዚህ ዓይነቱ አደጋዎችን ለመከላከል የሚቻለው ደግሞ ጉዳዩ በይበልጥ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ሲንቀሳቀሱ ብቻ ነው፡፡

ከዚህም ግንዛቤ በመነሳት ኸልፕ ኤጅ ኢንተርናሽናልና የኢትዮጵያ አረጋውያንና ጡረተኞች ብሔራዊ ማኅበር የሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች በአርዓያነት እንደሚታይ ይወሳል፡፡

ኸልፕ ኤጅ ለ680 ተፈናቃይ አባወራዎች ስድስት ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል ዝግጅት ማጠናቀቁን  ይገልጻል፡፡

የኸልፕ ኤጅ ኢንተርናሽናል ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሲሳይ ሥዩም እንደገለጹት የተባበሩት መንግሥት ድርጅት አካል ከሆነው ኦርጋናይዜሽን ፎር ከኦርዲኒሼን ሂውማኒቴሪያን አፌርስ (ኦኮሂአ) እና ከጀርመን መንግሥት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ዕርዳታ የሚደረግላቸው በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን በሚገኙ በዋጪ፣ ጉቺና ደሀሰ ወረዳዎች ውስጥ በተቋቋሙት 15 መጠለያ ጣቢያዎች ለሚኖሩ አባወራ ተፈናቃዮቹ ነው፡፡

አባወራዎቹ ከቀድሞ ቀዬአቸው ሊፈናቀሉ የቻሉት ቀደም ሲል በተከሰተው የእርስ በርስ ግጭትና አምባጓሮ ምክንያት መሆኑን ዋና ሥራ አስኪያጁ አመልክተዋል፡፡

ከሚቀጥለው ሳምንት መጀመርያ ቀናት አንስቶ ለተጠቃሚዎች የሚታደሉት ዕርዳታዎችም የንጽሕና መጠበቂያ አልኮል፣ ሳኒታይዘር፣ የወባ መከላከያ አጎበር፣ የቤት ቁሳቁስ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

ከዚህም ሌላ የመጠጥ ውኃ ማስፋፊያ፣ የመፀዳጃ ቤትና የንጽሕና አጠባበቅ ሥራ እንደሚከናወኑላቸው ዋናው ሥራ አስኪያጅ አመልክተው፣ ለዚህም ሥራ ማከናወኛ ከተመደበው ገንዘብ ውስጥ ሦስት ሚሊዮን ብር ድጋፍ የተገኘው ከኦኮሂአ ሲሆን፣ የቀረው ደግሞ የተለገሰው ከጀርመን መንግሥት መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡

ከዚህም ሌላ ከቤት ለማይወጡና የምግብ ችግር ላለባቸው 1,000 አረጋውያን  ለአንድ ዓመት የሚሆን አልሚ ምግቦችን የማቅረብ ሥራ ይከናወናል፡፡ ከጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞችም ጋር በመተባበር በጤና በተለይም በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ ቤት ለቤት የግንዛቤ ማስጨበጥ ትምህርት እንደሚሰጥ ለዚህም ዕውን መሆን ከ300 በላይ የሚሆኑ የቤት ለቤት ሠራተኞችን አረጋውያንን በመንከባከብ ሥራ ላይ ያተኮረ ሥልጠና ሰጥቶ ማንቀሳቀሱን አስረድተዋል፡፡

የኢትዮጵያ አረጋውያንና ጡረተኞች ብሔራዊ ማኅበር በ650,000 ብር የምግብ ዘይት፣ ዱቄት፣ የንጽሕና መጠበቂያ ሳሙና፣ ሳኒታይዘርና አልኮል ገዝቶ በሁለት ከተሞችና በዘጠኝ ክልሎች ለሚገኙ ምንም ገቢ ለሌላቸው 760 አረጋውያን አከፋፍሏል፡፡

የማኅበሩ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ክፍሌ እንደገለጹት፣ ማኅበሩ ከሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ገዝቶ ዕርዳታ ካደረገላቸው አረጋውያን መካከል 72ቱ በአዲስ አበባ ከተማ በአሥሩም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ናቸው፡፡

ከዚህም ሌላ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 450,000 ችግረኛ ዜጎችን ለመርዳት የሚያስችለውን ምዝገባ እያካሄዱ መሆኑን፣ በአሥሩም ክፍለ ከተሞች እየተካሄደ ያለው ይኸው ምዝገባ ከቤት የማይወጡና ምንም ነገር የሌላቸውን አረጋውያን ያካትታል ተብሎ እንደሚጠብቁ አስረድተዋል፡፡

በመላ ኢትዮጵያ ከ6.8 ሚሊዮን በላይ አረጋውያን እንደሚገኙ ከእነዚህም መካከል ከ400,000 በላይ የሚሆኑት አዲስ አበባ ውስጥ እንደሚኖሩ ከምክትል ፕሬዚዳንቱ ማብራሪያ ለመረዳት ተችሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ከህወሓት የሰላም ስምምነት ኮሚቴ አባላት ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ተገናኙ

የፌዴራል መንግሥትና የህወሓት የሰላም ስምምነት ኮሚቴ አባላት ከጠቅላይ ሚኒስትር...

ማስተካከያ

በሪፖርተር ጋዜጣ ረቡዕ ጥር 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ዕትም...

[ክቡር ሚኒስትሩ በወቅታዊ ፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የቀረበላቸውን ምክረ ሐሳብ እያደመጡ ነው]

ችግሩ ምን እንደሆነ በትክልል ለይተነዋል ግን ግን ምን? በይፋ መናገር አልነበረብንም። ለምን? ችግሩን...

የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ውጤትና እንደምታው

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) የትምህርትን...