Monday, February 26, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናግብፅ ከአንድ ወር በፊት ውድቅ ያደረገችውን የሦስትዮሽ ድርድር ተቀበለች

ግብፅ ከአንድ ወር በፊት ውድቅ ያደረገችውን የሦስትዮሽ ድርድር ተቀበለች

ቀን:

ግብፅ መልሳ ከድርድሩ በመውጣት ኢትዮጵያ ላይ ጣት መቀሰሯ እንደማይቀር ባለሙያዎች አሳሰቡ

በህዳሴ ግድቡ የውኃ አሞላል ላይ የሦስትዮሽ ወይይት እንዲደረግ ኢትዮጵያ ከአንድ ወር በፊት ያቀረበችውን ጥያቄ ውድቅ ያደረገችው ግብፅ፣ የሦስትዮሽ ድርድሩን ለመቀጠል መስማማቷን ሐሙስ ግንቦት 14 ቀን 2012 ዓ.ም. አስታወቀች።

ግብፅ ወደ ሦስትዮሽ ድርድሩ ለመመለስ የወሰነችው ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (/)፣ የውጭ ጉዳይና የውኃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሮችን፣ እንዲሁም የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር በተገኙበት ከሱዳን አቻቸው ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ጋር በጉዳዩ ላይ የቪዲዮ ኮንፈረንስ ካደረጉ በኋላ ነው።

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ግብፅ ... ሜይ 1 ቀን 2020 ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ባቀረበችው አቤቱታ፣ ኢትዮጵያ በህዳሴ ግድቡ የውኃ አሞላልና አለቃቀቅ ላይ በሦስቱ አገሮች መካከል ስምምነት ሳይደረስ በመጪው ሐምሌ ወር የመጀመሪያውን ምዕራፍ የውኃ ሙሌት ለማካሄድ በተናጠል መወሰኗን፣ እንደማትታገሰውና ይህም በአካባቢው ፀጥታና ደኅንነት ላይ ችግር ሊፈጥር እንደሚችል አሳስባ ነበር።

ኢትዮጵያ ለተመድ በላከችው ምላሽ ደብዳቤ የግብፅን ሥጋት እንዳጣጣለች በረቡዕ ግንቦት 12 ቀን 2012 ዓ.ም.ትም መዘገባችን ይታወሳል። ሪፖርተር ያገኘው ኢትዮጵያ ለተመድ የላከችው ምላሽ ደብዳቤ ‹‹ኢትዮጵያ በተፋሰሱ አገሮች መካከል መተማመንን ለመፍጠር ባላት ፅኑ ፍላጎት መሠረት ለስኬታማ የሦስትዮሽ ድርድር ያልተቆጠበ ጥረቷን ትቀጥላለች፤›› ይላል። ‹‹ምንም እንኳ ሁላችንም በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ውስጥ ብንሆንም፣ ኢትዮጵያ መተማመንን ለመፍጠር ባላት ፅኑ ፍላጎት የተነሳ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ በመጀመሪያው ዙር የግድቡ የውኃ ሙሌት ላይ ውይይት እንዲደረግ ለግብፅና ለሱዳን መሪዎች ... ኤፕሪል 20 ቀን 2020 መልዕክት ልከው ነበር፡፡ ነገር ግን ግብፅ እንደተለመደው የቀረበውን ጥያቄ ሳትቀበል ቀርታለች፤›› ይላል።

ኢትዮጵያ ለተመድ የፀጥታው ምክር ቤት በላከችው በዚህ ደብዳቤ የግድቡን ግንባታና ሙሌት ዓለም አቀፍ ሕጎችንና ጉልህ ጉዳት ያለማድረስ መርሆችን፣ እንዲሁም ሦስቱ አገሮች በተፈራረሙት የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት መሠረት ማከናወኗን እንደምትቀጥል አስታውቃለች።

ኢትዮጵያ ደብዳቤዋን ከላከች የተወሰኑ ቀናት በኋላ የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጉዳዩን እየተከታተሉት እንደሆነ ገልጸው፣ ሦስቱ አገሮች በተፈራረሙት የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት መሠረት ተቀራርበው እንዲወያዩ አሳስበዋል።

ይህንን ተከትሎም ባለፈው ሐሙስ በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይና በሱዳኑ አቻቸው መካከል ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ በዚህም ውይይት ሦስቱ አገሮች ያለ ሦስተኛ ወገን ጣልቃ ገብነት፣ የቴክኒክ ውይይታቸውን ተመልሰው ለማካሄድ ተስማምተዋል። ይህ የሁለቱ መሪዎች ወይይት ከተጠናቀቀ ከሰዓታት በኋላ የግብፅ መንግሥት ወደ ሦስትዮሽ ውይይት ለመመለስ መወሰኑን አስታውቋል።

የሦስትዮሽ የቴክኒክ ውይይቱ የሚካሄደው በአሜሪካ በነበረው ተመሳሳይ ውይይት የተደረሰበት የስምምነት ማዕቀፍ መሠረት በማድረግ፣ መግባባት ያልተደረሰባቸውን ጉዳዮች በመፍታት እንደሚቀጥል የኢትዮጵያና የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትሮች በትዊተር ገጻቸው አመልክተዋል። ይህንንም ውይይት ለማስጀመር ለሦስቱ አገሮች የውኃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ኃላፊነት ተሰጥቷል።

በጉዳዩ ላይ ሪፖርተር ያነጋገራቸው ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ አንድ የኢትዮጵያ መንግሥት የሥራ ኃላፊ፣ ግብፅ አቋሟን ቀይራ ወደ ሦስትዮሽ ድርድር ለመመለስ የወሰነችው ቀደም ብላ በተከተለችው መንገድ ኪሳራ ስለደረሰባት እንደሆነ ገልጸዋል። ግብፅ በህዳሴ ግድቡ ላይ ያላት ፍላጎት በቴክኒክ እንደማይፈታ ስለምትረዳ ዘወትር የምትመርጠው የፖለቲካ መፍትሔ እንደሆነ የገለጹት ኃላፊው፣ በዚህ እምነቷ የአሜሪካ መንግሥትን ብታስገባም ውጤት አለመምጣቱን፣ በተመድ የፀጥታ ምክር ቤት በኩል ጫና ለመፍጠር ያደረገችው ጥረትም በተመሳሳይ ውጤት ባለመምጣቱ ወደ ሦስትዮሽ ድርድር ለመመለስ እንደወሰነች አስረድተዋል፡፡

ይህ ማለት ግን አቋሟን ቀይራለች ማለት እንዳልሆነ የገለጹት ኃላፊው፣ እንደገና በሚጀመረው ድርድርም በቴክኒክ ጉዳዮች ትርጓሜዎችን በማዛባት ወደ ሦስትዮሽ ድርድር ብትመለስም፣ ኢትዮጵያ በያዘችው አቋም ምክንያት ወደ ስምምነት መምጣት እንዳልቻለች በመክሰስ እንዲቋረጥ ማድረጓ እንደማይቀር ጠቁመዋል፡፡ በዚህ መንገድ ክሶችን በማቅረብ ኢትዮጵያ በመጪው ሐምሌ ወር ግድቡን መሙላት እንዳትጀምር ጫና እንዲደረግባት ለማድረግ ካልሆነ በስተቀር፣ ግብፅ የያዘችው አቋም ፈጽሞ ከኢትዮጵያ የሚታረቅ እንዳልሆነ አስታውቀዋል፡፡

ለአብነትም ኢትዮጵያ የቴክኒክ ቡድን ድርድሩ በግድቡ የውኃ ሙሌትናዓመታዊ ኦፕሬሽን ላይ ማተኮር እንዳለበት ስታነሳ፣ ግብፅ ግን የረዥም ጊዜ የግድቡ ኦፕሬሽንና የውኃ ሙሌቱም አጠቃላይ የዓባይ ተፋሰስ ተፈጥሯዊ ፍሰትን የተመለከተ እንዲሆን ትፈልጋለች ብለዋል። ይህ የግብፅ መከራከሪያ ድርድሩ ከግድቡ አልፎ በኢትዮጵያ ግዛት የሚገኘውን የዓባይ ውኃ በዚህ ስምምነት ውስጥ የማስገባት ፍላጎትን የያዘ በመሆኑ፣ በዚህ ጉዳይ ላይ መደራደር ለኢትዮጵያ የዓባይን ውኃ አሳልፎ እንደ መስጠት ስለሆነ ስምምነት ላይ መድረስ እንደማይቻል ኃላፊው አመልክተዋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...