Monday, April 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበጎርፍ አደጋ የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር ከ300 ሺሕ በላይ ደረሰ

በጎርፍ አደጋ የተፈናቀሉ ዜጎች ቁጥር ከ300 ሺሕ በላይ ደረሰ

ቀን:

በሰሎሞን ይመር

ከመበደኛው መጠን በላይ እየጣለ በሚገኘው የበልግ ዝናብ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች ቁጥር 470 ሺሕ በላይ መድረሱን፣ እንዲሁም 300 ሺሕ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው ተገለጸ፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የኢትዮጵያ ሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ ባወጣው ሳምንታዊ ሪፖርት መሠረት፣ ከሰሞኑ በጣለው ዝናብ የተከሰተው ጎርፍ በሶማሌ፣ በአፋር፣ በደቡብ፣ በኦሮሚያ ክልሎችና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ በርካታ አካባቢዎች ላይ ጉዳት ማድረሱን አስታውቋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በሚያዚያ ወር መጨረሻ ብሔራዊአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት እየጣለ ባለው ከመደበኛ በላይ የበልግ ወቅት ዝናብ ምክንያት በተከሰተው ጎርፍ፣ ከ220 ሺሕ በላይ ዜጎች መጎዳታቸውንና 110 ሺሕ በላይ ደግሞ ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ይህ አኃዝ ይፋ ከተደረገ በኋላም በጎርፍ ጉዳት የደረሰባቸውና የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር፣ በከፍተኛ መጠን በመጨመር ላይ እንደሚገኝ የተመድ ሪፖርት አመላክቷል፡፡ በአሁኑ ወቅትም የተጎጂዎች ቁጥር እየጨመረ ከ470 ሺሕ በላይ እንደ ደረሰና ከ300 ሺሕ በላይ ዜጎችም ከቀዬአቸው መፈናቀላቸውን አስታውቋል፡፡

በተለይ ባለፈው ሳምንት በሊበን ዞን፣ ዶሎ አዶ፣ ኮልማንዮ፣ በምዕራብ ጉጂ ዞን ገላናና ቡሌ ሆራ፣ በቦረና ዞን ሞያሌ፣ በጉጂ ዞን ሊበን፣ እንዲሁም በባሌ ዞን ጊኒር፣ ጎሎልቻ፣ ጋሰራ በተባሉ አካቢዎች የጎርፍ አደጋው ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ታውቋል፡፡

በሶማሌ ክልል በተለይ ጎርፍ የከፋ አደጋ ሲያደርስ፣ በክልሉ ዘጠኝ ዞኖች ውስጥ በሚገኙ 26 ወረዳዎች ውስጥ ሥርጭት እንደነበረውና በእነዚህ አካባቢዎች ውስጥ የሚኖሩ 342 ሺሕ ሰዎች በጎርፍ አደጋ ጉዳት እንደ ደረሰባቸው ተመልክቷል፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ከ198 ሺሕ በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸው ይፋ ተደርጓል፡፡

ምንም አንኳ እየቀረበ ያለው ድጋፍ ውስንነት ቢኖረውም መንግሥትና የሰብዓዊ ድጋፍ ሰጭ አጋሮቹ በአሁኑ ወቅት በጎርፍ ለተጎዱና ለተፈናቀሉ ዜጎች የምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎችን እያቀረቡ እንደሚገኝ የተመድ ሪፖርት አስታውሶ፣ በሶማሌ ክልል ሸበሌ ዞን በጎርፍ ክፉኛ በተጠቁ አካባቢዎች ለሚገኙ ዜጎች አፋጣኝ የምግብ ዕርዳታ ለማድረስ የሚደረገውን እንቅስቃሴ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደከተተው አስታውቋል፡፡ የውኃው ከፍታ መጠን በቀላሉ ለመንቀሳቀስ ባለማስቻሉ፣ የክልሉ መንግሥት የድጋፍ ሥራውን የሚያግዙ ጀልባዎችና ሔሊኮፕተሮች  እንዲቀርቡለት  ለፌደራል መንግሥት ጥያቄ ማቅረቡም ታውቋል፡፡

በተመሳሳይ የአፋር ክልል የአደጋ ዝግጁነትና ምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት፣ በክልሉ በጎርፍ አደጋ ጉዳት ከደረሰባቸው ውስጥ ለግማሽ ያህሉ ብቻ ከመጠባበቂያ የምግብ ክምችቱ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ በመጥቀስ፣ ከብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ተጨማሪ ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎች እንዲደረግለት ጥያቄ ማቅረቡን ለማወቅ ተችሏል፡፡

በአገሪቱ የበልግ ዝናብ ሥርጭትና መጠን ከሚጠበቀው በላይ እየጨመረ በመምጣቱ፣ በተለያዩ አካባቢዎች እየተስተዋለ የመጣውን የጎርፍ አደጋ ታሳቢ ያደረገ ለቀሪው የበልግ ወቅት የሚያግዝ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡ ብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ብሔራዊ የጎርፍ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓት በመዘርጋት ላይ እንደሚገኝና በመጪው ሳምንት ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

በተለያዩ አካባቢዎች በሚያዝያ ወር የጣለው ከፍተኛ የዝናብ መጠን፣ በበልግ ወቅት የጎርፍ ክስተተ ሲያስከትል መቆየቱን የረዥም ጊዜ ትንበያዎች ያሳያሉ፡፡  ከድርቅ በመከተል የጎርፍ አደጋ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ብሔራዊ ሥጋት በመሆን መዝለቁ ይገለጻል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም...

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...