Wednesday, December 7, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊሕግ የሚጥሱ የነዋሪዎች ቁጥር እንደ ኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች በየቀኑ እየጨመረ መሆኑን ፖሊስ...

  ሕግ የሚጥሱ የነዋሪዎች ቁጥር እንደ ኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች በየቀኑ እየጨመረ መሆኑን ፖሊስ አስታወቀ

  ቀን:

  መንግሥት የኮሮና ወረርሽኝ ለመከላከል ያወጣውን አዋጅ ድንጋጌና የጤና ባለሙያዎችን ማሳሰቢያና ሕግ የሚጥሱ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች፣ እንደ ቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥራቸው እየጨመረ መሆኑን ፖሊስ ገለጸ፡፡

  የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ፋሲካ ፈንታ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ላለፉት ሦስት ሳምንታት በአገር አቀፍ ደረጃ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር በየቀኑ እየጨመረ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት በርካቶች ከፍተኛ ሥጋት ቢገባቸውም፣ በተቃራኒው የሚንቀሳቀሱና ምናልባትም ለሌሎች ጠንቅ ይሆናሉ ተብለው ሥጋት የፈጠሩ ነዋሪዎች መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡

  መንግሥት ከሚያዝያ 8 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ በሥራ ላይ እንዲውል ያወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከሚያስፈጽሙ ተቋማት አንዱ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መሆኑን አስታውሰው፣ በሚያደርገው ድንገተኛ ፍተሻ እያጋጠመው ያለው ሕገወጥነት አስደንጋጭ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

  ግንቦት 15 ቀን 2012 ዓ.ም. በአሥሩም ክፍላተ ከተሞች ፖሊስ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ 1,887 ግለሰቦች ጫት ሲቅሙ፣ ሺሻ ሲያጨሱ፣ ጠጅ፣ አረቄ፣ ቢራና ሌሎች መጠጦችን በአንድ ቤት በአማካይ ከ30 እስከ 40 በመሆን ሲጠጡ መያዛቸውን አስረድተዋል፡፡

  በአንድ ቀን ይህንን ያህል ሰው ሕግ በመጣስና የጤና ባለሙያዎችን ምክር በመተላለፍ በጠባብ ክፍል ውስጥ መገኘት፣ ምን ሊባል እንደሚችል ግራ የሚያጋባ ነገር ነው ሲሉ ሁኔታውን አስረድተዋል፡፡

  ከእነዚህ 1,887 ግለሰቦች መሀል ሁለትና ሦስት ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ቢሆኑ መላው የከተማው ነዋሪ እንደተያዘ አመላካች ስለሆነ፣ መንግሥት የመጨረሻውን ዕርምጃ መውሰድ መጀመሩን ተናግረዋል፡፡ ፖሊስ በየቀኑ የሚይዛቸውን ሕግ የተላለፉና ሕገወጥ ተግባር ፈጻሚዎችን ቢያስር ቦታ እንደማይበቃ፣ ቫይረሱ ካለባቸውም ሌላ ጉዳት ስለሚሆን 1,476 ሰዎችን መክሮ መልቀቁን ገልጸዋል፡፡ 411 ግለሰቦች በሌላ ጊዜ በተለያዩ ድርጊቶች ውስጥ የተሳተፉ ስለነበሩ፣ የክስ ፋይል ተከፍቶባቸው ክስ ለመመሥረት እየተሠራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

  ቀደም ባሉት ቀናት ተይዘው ክስ የተመሠረተባቸው ከ640 በላይ ግለሰቦች የሦስት ወራት እስራትና እስከ 20 ሺሕ ብር የሚደርስ ቅጣት እንደተጣለባቸው ኮማንደር ፋሲካ ተናግረዋል፡፡ መደበኛ ወንጀሎች የሚባሉት ሌብነት፣ ቅሚያ፣ በጦር መሣሪያ አስፈራርቶ መዝረፍ፣ ወዘተ የወንጀል ድርጊቶች 17 በመቶ ቀንሰው ባሉበት ሁኔታ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የወጣባቸው የወንጀል ድርጊቶች በመጨመራቸው፣ ሕጉን በአግባቡ እየፈተሸ ፖሊስ ዕርምጃውን እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በኦሮሚያ ክልል የተፈጸመው ጭፍጨፋና ሥጋቱ

  ኦሮሚያ ክልል ከቀውስ አዙሪት መላቀቅ ያቃተው ይመስላል፡፡ ከ200 በላይ...

  እናት ባንክ ካፒታሉን ወደ አምስት ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ወሰነ

  መጠባበቂያን ሳይጨምር የባንኩ የተጣራ ትረፍ 182 ሚሊዮን ብር ሆኗል እናት...

  ቡና ባንክ ዓመታዊ ትርፉን ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ማሻገር ቻለ

  ቡና ባንክ በ2014 የሒሳብ ዓመት ዓመታዊ የትርፍ ምጣኔውን ለመጀመርያ...