Saturday, November 26, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ማኅበራዊየዘረመል ልውጥ ህያዋንን በኢትዮጵያ ለማምረትና ለመጠቀም የሚደረገውን እንቅስቃሴ በመቃወም ፊርማ ማሰባሰብ ተጀመረ

  የዘረመል ልውጥ ህያዋንን በኢትዮጵያ ለማምረትና ለመጠቀም የሚደረገውን እንቅስቃሴ በመቃወም ፊርማ ማሰባሰብ ተጀመረ

  ቀን:

  በዓለም ላይ በርካታ ጠቀሜታ ያላቸው ሰብሎች መገኛና የብዝኃ ሕይወት ዋና ማዕከል በሆነችው ኢትዮጵያ፣ በዘረመል ምህንድስና የተለወጡ ምርቶችን ለመጠቀም የሚደረገውን እንቅስቃሴ በመቃወም በዓለም አቀፍ ደረጃ ፊርማ ማሰባሰብ ተጀመረ፡፡

  ፔለም ኢትዮጵያ ኮንሰርትየም በሚመራውና የኢትዮጵያ ሲቪክ ማኅበረሰብ አባላት እየተሳተፉ በሚገኙበት የተቃውሞ ፊርማ ማሰባሰብ፣ እስከ ዓርብ ግንቦት 21 ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ 40 የውጭ ድርጅቶችና ከ11 በላይ የአገር ውስጥ ሲቪክ ማኅበራት ፊርማቸውን አኑረዋል፡፡

  በኢትዮጵያ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ሳይደረግና የሕዝብ አስተያየት ሳይሰጥበት በዘረመል ምህንድስና የተለወጡ (GMO) ልውጠ ህያዋንን ለማምረትና ለመጠቀም የሚደረገው እንቅስቃሴ ትክክል አለመሆኑን ለመንግሥት ለማሳወቅ እየተሳተፉ የሚገኙ የሲቪክ ማኅበረሰብ አካላት ባወጡት የአቋም መግለጫ፣ መንግሥት በኢትዮጵያ ያለውን የዘረመል ምህንድስና እንቅስቃሴ ዳግም ሊያጤን ይገባል ብለዋል፡፡

  የአሜሪካ ግብርና መሥሪያ ቤት ጥር 27 ቀን 2012 ዓ.ም. “Agricultural Biotechnology Annual Report (ET 2019-0010)” (የግብርና ጥበብ-ሕይወት ዓመታዊ ግምገማ) በሚል ርዕስ ባዘጋጀው ሪፖርት፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ለገበያ የሚሆን የባዮቴክኖሎጂ (ቢቲ) ጥጥ እንዲመረትና ለአፍሪካ ተስማሚና ውኃ ቆጣቢ የሆነ የበቆሎ ሰብል በተከለለ ቦታ የሙከራ ምርምር እንዲካሄድ ፈቀደ ብሎ ማተቱን ያስታወሰው የሲቪክ ማኅበራቱ የአቋም መግለጫ፣ በደቡብ አፍሪካ ድርቅ የሚቋቋም ልውጥ የዘረመል በቆሎ የተፈለገውን ምርት ሳያስገኝ መቅረቱንና በቢቲ ጥጥ ምክንያት የተከሰቱ ችግሮችን መንግሥት እንዲያጤን ጠይቀዋል፡፡

  የፔለም ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር የአፈር ሳይንቲስቱ ኃይሉ አርዓያ (ዶ/ር) እንደሚሉት፣ ኢትዮጵያ በዘረመል ምህንድስና የተለወጡና በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ቁጥጥር ሥር ያልሆኑ ሰብሎችን ለመጠቀም ከምትንቀሳቀስ ይልቅ፣ በአገሪቱ ባሉ የተለያዩ ግብርና ምርምር ተቋማት በምርምር የሚገኙ የተሻሻሉ ዝርያዎችን ብትጠቀም የበለጠ ተጠቃሚ ትሆናለች፡፡

  የዘረመል ምህንድስናን የሚደግፉ አካላት ቴክኖሎጂው ምርት ለማብዛት፣ በሽታንና ድርቅን ለመቋቋም ያስችላል የሚል ምክንያት ቢኖራቸውም፣ ኃይሉ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ችግሯ ማምረት አይደለም ይላሉ፡፡

  ያለውን የእርሻ ቦታ በሙሉ አቅም አለመጠቀም፣ የመሠረተ ልማት አቅርቦት ወሰን መሆንና የገበያ ትስስር አለመዘርጋት የግብርናው ዘርፍ ችግሮች መሆናቸውን ያስረዳሉ፡፡ የዘረመል ምህንድስና ሲነሳ በተደጋጋሚ የሚነሳው በቆሎ፣ በምዕራብ ወለጋ ተፈጥሮውን በጠበቀ መንገድ በገፍ በተመረቱባቸው የቀደሙ ዓመታት ኩንታሉን በ20 ብር የሚገዛ ጠፍቶ እንደነበርም በምሳሌ ያስታውሳሉ፡፡

  በግብርና ሥርዓት ውስጥ ያሉ ችግሮችን በመቅረፍና በኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ተቋማት ውስጥ ከለውጥ ህያዋን ሳይሆን፣ ከራሳቸው ባህሪ በመነሳት የተሻሻሉ ዝርያዎችን በመጠቀም ምርቱን ማብዛት እንደሚቻል በመጠቆም፣ ልውጠ ህያዋን በአርሶ አደሩም ሆነ በሕዝቡ ላይ ችግር ይዘው ሳይመጡ መንግሥት ቅድመ ጥንቃቄ እንዳያደርግ አሳስበዋል፡፡

  መንግሥትም የዘረመል ምህንድስና ምርቶች ላይ ተቋማዊ የቁጥጥር ሥርዓት ተዘርግቶ ሕዝባዊ የምክክር መድረክ እስኪከናወን ድረስ፣ የዘረመል ልውጥ ህያዋን የማሳ ላይ ሙከራና ለሽያጭ የሚውል የሰብል ምርት ላይ ከአምስት ዓመት ያላነሰ እግድ እንዲጥል፣ ዘረመል ልውጥ ህያዋን በግብርና ሥርዓተ ይካተቱ ወይስ ይቅሩ የሚለው ላይ ሕዝባዊ ውይይት እንዲደረግ፣ ኢትዮጵያ የካርታኼና ፕሮቶኮልን ለማስፈጸም የገባችውን ቃል እንድታከብር፣ የዘረመል ልውጥ ምርቶችን ለመቆጣጠር ግልጽና አሳታፊ አሠራሮች በተግባር እንዲውሉ እንዲያደርግ የሲቪክ ማኅበራቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img
  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  የትርፍ መጠኑን በ127 በመቶ ያሳደገው አቢሲኒያ ባንክ ካፒታሉን በ2.5 ቢሊዮን ብር እንዲያድግ ወሰነ

  የአቢሲኒያ ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩ  ካፒታል በ2.5 ቢሊዮን ብር...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን 55 ቢሊዮን ብር ለማድረስ ወሰነ

  የአዋሽ ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ ዛሬ ህዳር 17 ቀን 2015...

  ከብሔራዊ ባንክ እውቅና ያገኘው ፔይሊንክ አክሲዮን ማህበር ምሥረታውን አካሄደ

  ከገንዘብ ንክኪ ነፃ የሆነ የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ለመተግበር ያቀደው...