Sunday, March 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየአትሌቲክስ አሠልጣኞች የቤት ለቤት ሥልጠና መስጠት ጀመሩ

የአትሌቲክስ አሠልጣኞች የቤት ለቤት ሥልጠና መስጠት ጀመሩ

ቀን:

2020 ኦሊምፒክ በ2021 የማይካሄድ ከሆነ ሊሰረዝ ይችላል ተባለ

በኦሊምፒክና በዓለም ሻምፒዮኗ ጥሩነሽ ዲባባ ስም የተሰየመው የአሰላው አትሌቲክስ ማሠልጠኛ ማዕከል የአሠልጣኞች ቡድን፣ ለአትሌቶች የቤት ለቤት ሥልጠና መስጠት መጀመራቸው ታወቀ፡፡ የቡድኑ ሥልጠና በዋናነት የሚያተኩረው  በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ከጥሩነሽ ዲባባ ማሠልጠኛ ማዕከል ወጥተው ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለሚኖሩ አትሌቶች እንደሆነ ተነግሯል፡፡

የማዕከሉ የአሠልጣኞች ቡድን እንዳስታወቀው ከሆነ፣ ይህ በዓይነቱ የመጀመርያ የሆነው ሥልጠና የኮሮና ቫይረስ  ሥርጭትን በመሥጋት ከማዕከሉ ወጥተው ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲሄዱ የተደረጉ ሠልጣኞችን ለማገዝና እግረ መንገዱንም የልምምድ ዕቅዶችን  ለመስጠት ያለመ ነው፡፡

ቡድኑ በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ሠልጣኞችን በሚኖሩበት ከተማና አካባቢ በመሄድ ምልከታ ማድረጉ በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡

የአሠልጣኞቹ ቡድን ከሁሉም የሥልጠና ዘርፎች በማውጣጣት በሁለት ምድብ በመክፈል ማለትም፣ አንደኛው ቡድን ከበቆጂ ከተማ ጀምሮ ኮፈሌ፣ ሻሸመኔና አርቤጎና መዳረሻውን ሲያደርግ፣ ሁለተኛው ቡድን ደግሞ ከሻሸመኔ በኋላ እስከ ጉጅ ያሉትን የማዕከሉ ሠልጣኞችን ያካተተ መሆኑም ተነግሯል፡፡

በምልከታው መሠረት የአሠልጣኞቹ ቡድን ከሠልጣኞቹ ጋር በተለይም የኮሮና ቫይረስ በሽታ መከላከያ ዘዴዎችና ስለቀጣዩ ሥልጠና በመነጋገር የልምምድ ዕቅዶችን ለሠልጣኞች መስጠቱ ገልጿል፡፡ ከልምምድ ዕቅዶቹ በተጨማሪ ለአትሌቶቹ የእጅ ንፅህና መጠበቂያ ሳኒታይዘርና አልኮል ጭምር ማከፋፈሉ ሲታወቅ፣ የሥልጠና ዕቅዱ ደግሞ ለአራት ሳምንት የሚያገለግል መሆኑም ተነግሯል፡፡

የጥሩነሽ ዲባባ ማሠልጠኛ ማዕከል መንግሥት አትሌቲክሱን ለማሳደግና ለማስፋፋት በሚል ካስገነባቸው ማዕከሎች ማለትም፣ አዲስ አበባ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ወጣቶች ስፖርት አካዴሚ ቀጥሎ የሚጠቀስ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በሌላ በኩል ጃፓን ዘንድሮ ልታዘጋጀው የነበረው የቶኪዮ ኦሊምፒክ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ወደ 2021 መሸጋገሩ ይታወሳል፡፡

ይሁንና የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ (አይኦሲን) በመጥቀስ ከሰሞኑ የሚወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከሆነ፣ ይህ ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ አሁን ባለው ሁኔታና አያያዝ ለ2021 ኦሊምፒክ ሥጋት መሆኑ አልቀረም፡፡ የአይኦሲ ፕሬዚዳንት ቶማስ ባህ  ወረርሽኙ ክትባት የማይገኝለት ከሆነ የ2020 ኦሊምፒክ የሚለውን ስያሜ ይዞ በ2021 ሊካሄድ የታቀደው ኦሊምፒክ ሙሉ በሙሉ እንደሚሰረዝ ተናግረዋል፡፡

የአትሌቲክስ አሠልጣኞች የቤት ለቤት ሥልጠና መስጠት ጀመሩ

 

‹‹የ2020 ኦሊምፒክ በ2021 መካሄድ አለመካሄድ የሚወሰነው፣ በአሁኑ ወቅት ዓለም የገጠማት የጤና ቀውስ መፍትሔ የሚያገኝ ከሆነ ብቻ ነው፡፡ ወረርሽኙን አስመልክቶ በዋናነት የዓለም ጤና ድርጅት የሚሰጠውን አስተያየት በመከተል ካልሆነ አይኦሲ ብቻው በሚወስነው የሚሆን አንዳች ነገር አይኖርም፤›› በማለት የአይኦሲ ፕሬዚዳንት ከሰሞኑ በሰጡት መግለጫ ማረጋገጫ መስጠታቸው የቢቢሲ ዘገባ አመልክቷል፡፡

አስተናጋጇ ጃፓንና ሌሎች ያደጉ አገሮች ኦሊምፒክ ከመካሄዱ በፊት ዓለም አቀፉን ወረርሽኝ ሊቆጣጠሩት እንደሚችሉ ተስፋ እንደሚያደርጉ ጭምር ፕሬዚዳንቱ መናገራቸው ታውቋል፡፡ ከዚህ ባለፈ ግን ኦሊምፒክም ሆነ ተሳታፊ አገሮች አሁን ባለው ሁኔታ የወረርሽኙ ሥርጭት በዚህ ጊዜ መፍትሔ ያገኛል የሚል ማረጋገጫ መስጠት እንደማይቻልም እየተነገረ ይገኛል፡፡

እ.ኤ.አ. በ1916፣ በ1940 እና 1944 ሊካሄዱ ታቅደው የነበሩት ሦስት ኦሊምፒያዶች በአንደኛና በሁለተኛው የዓለም ጦርነቶች ምክንያት መሠረዛቸው አይዘነጋም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...