Sunday, March 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየደብረ ብርሃን አትሌቲክስ ማሠልጠኛ ማዕከል ነባር አሠልጣኞችንና አትሌቶችን እንደሚያሰናብት አስታወቀ

የደብረ ብርሃን አትሌቲክስ ማሠልጠኛ ማዕከል ነባር አሠልጣኞችንና አትሌቶችን እንደሚያሰናብት አስታወቀ

ቀን:

የደብረ ብርሃን አትሌቲክስ ማሠልጠኛ ማዕከል የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ተከትሎ ከማዕከሉ እንዲወጡ የተደረጉ ነባር የማዕከሉ አሠልጣኞችና አትሌቶች ለሚቀጥለው የማዕከሉ የሥልጠና ዘመን እንደማይጠራ አስታወቀ፡፡ ተቋሙ በቀጣይ ሊከውን ያሰበውን ዝርዝር ዕቅድም ይፋ አድርጓል፡፡

የኢትዮጵያን አትሌቲክስ ለማስፋፋትና ለማሳደግ መንግሥት ከ2000 ዓ.ም. ጀምሮ በአገር አቀፍ ደረጃ በወቅቱ ያደጉ ክልሎች ተብለው በሚታወቁት በትግራይ (ማይጨው)፣ በአማራ (ደብረ ብርሃን)፣ በኦሮሚያ (በቆጂ) እና በደቡብ ክልል (ሀገረ ማርያም) ላይ እንዲቋቋሙ ካስደረጋቸው የአትሌቲክስ ማሠልጠኛ ማዕከላት የደብረ ብርሃን አትሌቲክስ ማሠልጠኛ ማዕከል አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ማዕከሉ ዓለም አቀፍ በሆነው ኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት የ2012 ዓ.ም. የሥልጠና ዘመን በማቋረጥ ሠልጣኞችንና አሠልጣኞችን ማሰናበቱ ይታወሳል፡፡

ማዕከሉ በቀጣዩ ዓመት ማከናወን ስለሚገባው ዕቅድና ስለሚከተለው የአሠራር ሥርዓት ያዋጣል ያለውን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር የተለያዩ ውሳኔዎችን ማሳለፍ መቻሉን አስታውቋል፡፡ ተቋሙ የደረሰበትን ውሳኔ መነሻ በማድረግ በማዕከሉ ድረ ገጽ ይፋ ባደረገው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ የማሠልጠኛ ማዕከሉን ለማዘመንና ውጤታማ ለማድረግ ከሚቀጥለው የውድድር ዓመት ጀምሮ አዳዲስ አሠራሮች ይተገብራል፡፡

በዚሁ መሠረት በ2012 ውድድር ዓመት የሥልጠና ዘመን በመጠናቀቁ አትሌቶችንም ሆነ አሠልጣኞችን በዚህ ዓመት ድጋሚ ወደ ማዕከሉ እንዲገቡ ጥሪ እንደማይደረግ፣ ለ2013 የውድድር ዓመት ወደ ማሠልጠኛ ማዕከሉ በመመለስ ሥልጠና እንዲቀጥሉ የሚደረጉ አሠልጣኞችን በውጤት በመመዘን ሥልጠናቸውን እንዲቀጥሉ ቅድመ ሁኔታዎችን እንደሚያመቻች፣ ከነበሩት አሠልጣኞች መካከል የሥልጠና ጊዜያቸውን በዓመቱ ውስጥ ከሚያጠናቅቁ አትሌቶች መካከል የጠነከሩትና ለክለብ የሚመጥኑትን እንዲሁም የክለብ ዕድል የሚያገኙትን ወደ ክለቦች መልቀቅ፣ የክለብ ዕድል የማያገኙት ደግሞ የሥልጠና ዘመኑን የውድድር ዕድል ታሳቢ በማድረግ በድጋሚ ዕድል እንዲያገኙ እንደሚደረግ በመግለጫው ተመልክቷል፡፡

ወደ ክለብ በሚሔዱት ሠልጣኞች ምትክ በ2012 የውድድር ዓመት ወልድያ ከተማ ላይ ተደርጎ በነበረው የመላ አማራ ጨዋታዎች ላይ የተመረጡትን አትሌቶችና በማዕከሉ በመሠልጠን ላይ የነበሩ አትሌቶች የሥልጠና ዘመናቸውን ባይጨርሱም ባሳለፉት የሥልጠና ዘመን በነበራቸው የሥራና የሥልጠና አፈጻጸም እንዲሁም ቀጣይ ሁኔታዎች በመገምገም ውጤታማዎቹን እንደሚያስቀጥል መግለጫው ያስረዳል፡፡

በግምገማው ወቅት ደካማ የሆኑትን አትሌቶች ድጋሚ ዕድል እንደማይሰጥም ማዕከሉ አስታውቋል፡፡ ነባር አሠልጣኞችን በተመለከተ ማዕከሉ ‹‹ነባር›› በሚለው መመዘኛ ብቻ ድጋሚ ጥሪ እንደማያደርግላቸው ጭምር አስረድቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...