Monday, May 29, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ልናገርበተስፋና በሥጋት የተከበበው የአገራችን ፖለቲካና የመፍትሔ አቅጣጫ ምልከታ

በተስፋና በሥጋት የተከበበው የአገራችን ፖለቲካና የመፍትሔ አቅጣጫ ምልከታ

ቀን:

በከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር)

ይህ አጭር ጽሑፍ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያለኝን ግንዛቤ በመዳሰስ አሁን ላለንበት አጣብቂኝ አበርክቶ አላቸው የምላቸውን አካላት በመጠቆም መንግሥት፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች አገራችን ካለችበት ችግር ተላቃ ወደ ተረጋጋ ፖለቲካ ሁኔታ መመለስ ስለሚችሉበት መፍትሔ ለማሳየት ይሞክራል፡፡ በተጨማሪም አምነስቲ ኢንተርናሽናል እ.ኤ.አ. ሜይ 29 ቀን 2020 በአገራችን የሰብዓዊ መብት አያያዝ ላይ ያወጣው መግለጫን በተመለከተ የራሴን ወፍ በረር ግምገማ በማድረግ በሪፖርቱ ዙሪያ መደረግ ስላለበት ሥራ በመጠቆም፣ አሁን ያለንበት ወቅት ከብሽሽቅ ይልቅ ትብብርን የሚጠይቅ በመሆኑ በአንድነት መሥራት እንዳለብን ምክር ለመስጠትም ይሞክራል፡፡

 አሁን በአገራችን በስፋት ከመንግሥት እስከ ተፎካካሪ ፓርቲዎች የሚታየው የፉክክርና ተራ የብሽሽቅ ፖለቲካ ወደ ትብብርና ምክክር መሸጋገር ካልቻለ፣ ባለፉት ዓመታት የታዩት መልካም ጅማሮዎች እየፈረሱ ነገሮች  ከድጡ ወደ ማጡ መሄዳቸው አይቀርም። ፈረንጆች እንደሚሉት የትኛውም የጭቆና ትግል ፍሬ አፍርቶ ተጨቋኝ ወደ ሥልጣን መንበር መጥቶ በአግባቡ ተጨቋኞችን ነፃ ሳያወጣ ጊዜ ባክኖ ጨቋኝ ከሆነ አሊያም መሆን ከጀመረ፣ ወይም መጨቆን ጀምሯል የሚል ዕሳቤ (perception) በስፋት ከነገሠ በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርም ነውና ነገሩ ወደ ተነሳበት ከዚያም በባሰ መውረዱ አይቀርም ማለትfrom Zero to Hero to Zero” እንደሚሉት፣ ዑደቱ ይህን መከተሉ ተፈጥሯዊ ነው። ፖለቲካ በስትራቴጂካዊ ሥራ እንጂ ዝም ብሎ በዕድል አይስተካከልም።

እንደ እኔ ትዝብት አገራችን በርካታ አንገብጋቢ ጉዳዮች ቢኖሩባትም በርካታዎቹ አገራዊ አጀንዳዎች እየተቋጩና እየተስማማን ሌላ እየጀመርን አይደለም።  በሰንደቅ ዓላማ፣ በአገረ መንግሥት ምሥረታ፣ በሕገ መንግሥት፣ በአገራችን መንግሥታዊ አወቃቀር፣ ወዘተ. የተቀራረበ አቋም ለማምጣት መሥራት ለአገራዊ መረጋጋትና ለሠለጠነ የፖለቲካ ባህል መጎልበት የሚኖረው አበርክቶ ቀላል አይደለም የሚል እምነት አለኝ፡፡

በፖለቲካ ፓርቲዎችና በመንግሥት መካከል መደጋገፍና ጤናማ የሆነ የፉክክር ባህል አይታይም፡፡ በርካታ ተፎካካሪ ፓርቲዎችና ማኅበረሰብ አንቂዎች (activists)  የራሳቸውን አማራጭ መንገድ ከማሳየት ይልቅ፣ በመንግሥት በሚፈጠሩ ስህተቶች ላይ ህልውናቸው የተመሠረተ እስኪመስል እሱን እያጎሉ በጥሎ ማለፍ ሴራ ተጠምደዋል፡፡ በአንድ በኩል ስናይ መንግሥትም ለእያንዳንዱ ጉዳይ ትርጉም ሰጥቶ ዕርማት በማድረግና እስካሁን ያገኛቸውን ድሎች ጠብቆ ለመሄድ ያሉትን ተቋማት የማሻሻልና የማጠናከር፣ እንዲሁም አዳዲስ የተቋማት ግንባታና አስተማማኝ የፖለቲካ መሥራት አለመቻሉን ወይም ከተሠሩም በተገቢው ለሕዝብ ማሳወቅ አለመቻሉን በሌላ በኩል ስናይ፣ እጅግ የጓጓንለት ለውጥና የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ተስፋ አሁንም በመስቀለኛ መንገድና ከባድ ፈተና ውስጥ መሆኑን እንድንቀበል እንገደዳለን።

ባለፉት ሁለት ዓመታት በርካታ አኩሪናለምን ያስደመሙ ለውጦች ብዙዎቹ እንደሚሉት በአገራችን መመዝገባቸው የሚደነቅ ቢሆንም፣ የእዚያኑ ያህል አሳፋሪ የሰብዓዊና የዴሞክራሲ ችግሮች በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች ታይተዋል። ለእነዚህ ጥፋቶች መከሰት መንግሥትና መንግሥታዊ ያልሆኑ (non state actors) በአንድም በሌላ መልኩ አበርክቶ አላቸው።

በሌላ በኩል አምነስቲ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያን የሰብዓዊ መብት አያያዝ ችግሮችንና ለጥፋቶቹ መከሰት ኃላፊነት ያለባቸውን መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ አካላትን ገለልተኛ ሆኖ መዳሰስ አለመቻሉን ስናይ ደግሞ ሪፖርቱ የገጠመንን ችግር ለመፍታት ከማገዝ ይልቅ፣ ተሰባሪ ለሆነው ሽግግርና የፖለቲካ ፓርቲዎች ተራክቦና የድንጋይ ውርወራ ፖለቲካ መሣሪያ  በመሆን የአገራችን የፖለቲካ ሕመምን ለማከም የራሱን መጠነኛ አስተዋጽኦ ማድረግ አልቻለም፡፡ ይልቁንም  በቁስል ላይ እንጨት ስደድበት እንዲሉ ያባባሰው  ይመስላል። ያም ሆነ ይህ ለዚህ ሪፖርት ከእነ ችግሩም ቢሆን ትኩረት ሰጥቶ  መንግሥት ተገቢ መልስ መስጠቱ፣ ወደፊት መሰል ችግሮች እንዳይፈጠር ስለሚረዳ ችላ ብሎ ማለፍ አይገባም።

በሌላ በኩል በበርካታውዝብ ተስፋ የተጣለባቸውና እናቶች በፀሎትና በዕንባ ክፉ አይንካህብለው ዘወትር እየፀለዩላቸው ያሉት ቅላይ ሚኒስትር ዓብይ፣ አሁን ያንዣበብንን የሥጋት ጥላ ቀርፈው፣ አገሪቷን ለማዳን ከባድ ፈተና የተደቀነባቸው ይመስላል። ምንም የተጋረጠብን ፈተና ከባድ ቢሆን ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመስጠት ማስተካከያ ዕርምጃ ከወሰዱ ጊዜው አልረፈደም። በመሆኑም ቅላይ ሚኒስትሩ የኮሮናን ሥጋት፣ የምርጫውን ጉዳይ፣ ከህዳሴው ግድብ ጋር ተያይዞ ያለውን እሰጥ አገባ፣ ከሱዳን ጋር ያለው የድንበር ውዝግብ፣ ከሕወሓት ጋር ያለው ጭቅጭቅ፣ ያልተቋጨው የደቡብ ክልል የክልል አደረጃጀት ጥያቄና የኮሮና ወረርሽኝን ተከትሎ የተፈጠረው ከፍተኛ የኢኮኖሚ ድቀት ተሻግረን የምንወዳትን አገር በጠንካራ መሠረት ላይ ለመጣል ወሳኝ የሆነ፣ ከፉክክር ይልቅ ትብብርን መሠረት ያደረገ አመራር መስጠት  ይጠበቅባቸዋል።

የተለያዩ የተፎካካሪ ፓርቲዎችና ማኅበረሰብ አንቂዎችም እየተፎካከርነውና እየተበሻሸቅነው ያለነው ከአንድ ግለሰብ ወይም የፖለቲካ ፓርቲ ሳይሆን፣ በበርካታ ውጫዊና ውስጣዊ ችግሮች ተወጥራ የተያዘችው አገራችሁን መሆኑን በመገንዘብ በአርቆ አሳቢነት ለትብብር ልብን ክፍት ማድረግ ይገባል። በጣም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ ከፈጣሪ ቀጥሎ መንግሥትንና ተፎካካሪ ፓርቲዎችን ነገዬን ታሳምራላችሁ ብሎ ከማይሞላው የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴው ተጠምዶ እንደሚውል አውቃችሁ፣ ወደ ሠለጠነ የትብብር መንፈስ መመለስን ለነገ አታሳድሩ።

የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች፣ አባገዳዎች፣ ሃደ ሲንቄዎች፣ ባሊቆች (የስልጤ የአገር ሽማግሌዎች)፣ ገራዶችና ኡጋዞች በመንግሥትና በተፎካካሪ ፓርቲዎች፣ በብልፅግናና በሕወሓት መካከል የተፈጠረውን እሰጥ አገባና ፉክክር ወደ የሠለጠነ የውይይትና የትብብር መንፈስ ለመቀየር የሚጠበቅባቸውን ሚና ሊወጡ ይገባል። በተለይ በፌዴራል መንግሥቱና በትግራይ ክልል መካካል ያለው እሰጥ አገባና የብሽሽቅ ፖለቲካ መርገብ ለአገራችን መረጋጋት ያለው አበርክቶ ከፍተኛ እንደሆነ አምናለሁ፡፡

በመሆኑም የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማት አባቶች በራሳቸው ተነሳሽነት ሁለቱ አካላት ተቀራርበው ልዩነታቸውን እንዲያጠቡ ለማድረግ የዕርቅና የአንድነት መሥራት አለባቸው፡፡ አንደ አገር አገር አቀፍ የዕርቅና የአንድነት ፕሮግራም መከናወንም ለአገራችን መረጋጋት ያላቸው አበርክቶም ቀላልይደለም፡፡ በጥቅሉ ሁላችንንም ያሳፈረችው መርከብየፉክክር ቤት ሳይዘጋ ያድራልበሚባለው ብሂል በእኛ ያልተገባ ብሽሽቅና ፉክክር ሰጥማ ሊያጠቋት ላሰፈሰፉ ጠላቶች በማቀበል፣ አገርናዝብ ክፉኛ ተጎድቶ ሁላችንም ከማለቅ ለመዳን ፈጥነን ሚዛኑን ወደ ጠበቀ ፉክክርና ትብብር መግባት አስፈላጊ መሆኑን አውቀን ሳይረፍድ ወዲዚያው መሻገር ያሻል ባይ ነኝ።

ከአዘጋጁ፡- ጸሐፊው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማኅበራዊ ሥነ ሰብዕ (Social Anthropology) ትምህርት ክፍል የሕግ ብዝኃነት ባለሙያ ሲሆኑ፣ ጽሑፉ የእሳቸውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እየገለጽን በኢሜይል አድራሻቸው [email protected] ማግኘት ይቻላል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመስቀል አደባባይ የመግቢያ ክፍያ ለምን?

ወጣቶች፣ ሕፃናትና አረጋውያን ሳይቀሩ መንፈሳቸውን የሚያድሱበት እንዲሁም ሐሳባቸውን በነፃነት...

በሕገ መንግሥቱ የተዋቀረው ‹‹የብሔር ፖለቲካ›› እና ‹‹ሥርዓቱ›› ያስከተለው መዘዝና መፍትሔው

(ክፍል አራት) በዓቢዩ ብርሌ (ጌራ) ባለፈው ጽሑፌ (በክፍል ሦስት) አሁን ያለው...

የኢትዮጵያ ኅብረተሰብና የመንግሥት መሪ ምሥል

በበቀለ ሹሜ በ2015 ዓ.ም. መጋቢት ወር ውስጥ ይመስለኛል በ‹ሸገር ካፌ›...

ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ ያደረገው አዋጅ የፍትሐዊነት ጥያቄ አስነሳ

በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ስምንት ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ በማድረግ ተቋማዊና...