ቀደም ብሎ በተፈጠረው አለመረጋጋት ምክንያት በኦሮሚያና ሶማሌ ክልል አዋሳኝ ከመኖሪያ ቀዬአቸው የተፈናቀሉት ወገኖች ከሠፈሩባቸው የተለያዩ አካባቢዎች አንዱ የሱሉልታ አካባቢ ነው፡፡ በቦታው ሠፍረው አዲስ የሕይወት ምዕራፍ ቢጀምሩም ኑሮአቸው የተደላደለ አይደለም፡፡ እነዚህን ድጋፍ የሚሹ የኅብረተሰብ ክፍሎች የአዳማ አጠቃላይ ሆስፒታል ከአጠቃላይ ምርመራ ባለፈ፣ ለሴቶች የንፅህና መጠበቂያ፣ የሳኒታይዘር፣ የምግብ ዘይትና በካምፑ ውስጥ ያለውን መፀዳጃ ሥፍራ የማፅዳት ሥራን ጨምሮ የአምስት ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡