Tuesday, May 30, 2023

በኮሮና ወረርሽኝ ወቅት በሕፃናትና በሴቶች ላይ ጥቃት በመፈጸም የተጠረጠሩ ክስ ተመሠረተባቸው

- Advertisement -spot_img

በብዛት የተነበቡ

የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል በቤት ውስጥ የነበሩ ሕፃናትና ሴቶች ላይ ጥቃት በመፈጸም በተጠረጠሩ በርካታ ግለሰቦች ላይ 23 የክስ መዝገቦች ሲከፈቱ፣ በ94 መዝገቦች ላይ ደግሞ ፖሊስ ምርመራ እያከናወነ መሆኑ ታወቀ፡፡

የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች ባለፈው ሳምንት በሴቶችና በሕፃናት ላይ በቤት ውስጥ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለመዳኘት ክፍት መሆናቸውን፣ የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ፉአድ ኪያር ለሪፖርተር አስታውቀዋል፡፡

በተለይ በአዲስ አበባ ወንድና ሴት ሕፃናትን ጨምሮ ከ100 በላይ ጥቃቶች በቤተሰቦቻቸውና በቅርብ ዘመዶቻቸው መፈጸሙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ሕፃናት ቢሮ ኃላፊዎች በመግለጻቸው፣ ፖሊስ ባደረገው ምርመራ የጠረጠራቸውን በርካታ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር አውሎ በ23 መዝገቦች ክስ እንዳቀረበባቸው ታውቋል፡፡

ፍርድ ቤቶች መዘጋታቸውን እንደ አጋጣሚ በመቁጠር የቤት ውስጥ ጥቃት መጨመሩን፣ ወደ ፍትሕ አካላት የሚመጡ ጥቆማዎችም መቆማቸውን የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ወ/ሮ አዳነች አበቤ አስታውቀዋል፡፡ ከሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር፣ ከጠቅላይና ከመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች ተወካዮች፣ ከአዲስ አበባ ሴቶችና ሕፃናት ጉዳይ ቢሮ ኃላፊዎችና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ተወካዮች ጋር ባደረጉት ውይይት የሴቶችና የሕፃናት ጥቃት የሁሉም ቤተሰብ ጥቃት በመሆኑ፣ ሁሉም ሊታገለውና ሊያስቆመው የሚገባ ሕገወጥ ድርጊት መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ክፍተቶችን በመጠቀም በራስ ዜጎች ላይ የሚፈጸመው የቤት ውስጥ ጥቃት አሳዛኝ፣ አሳፋሪና ነውር መሆኑን የጠቁሙት ወ/ሮ አዳነች፣ ክስ ከተመሠረተባቸው 23 ተከሳሾችና ምርመራ እየተደረገባቸው ካሉት 94 ተጠርጣሪዎች በተጨማ፣ በአራት የክስ መዝገቦች ክስ ቀርቦባቸው የነበሩ ተከሳሾች የቅጣት ውሳኔ የተላለፈባቸው መሆኑንም  አስታውቀዋል፡፡

በሴቶችና በሕፃናት ላይ የሚደርሱ ማናቸውንም ዓይነት ጥቃቶች ለመከላከልና ድርጊቱን በሚፈጽሙ ላይ በሕግ አግባብ ተገቢውን ቅጣት ለመጣል፣ ፍርድ ቤቶች ክፍት መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ትኩስ ጽሑፎች

ተዛማጅ ጽሑፎች

- Advertisement -
- Advertisement -