Sunday, March 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
የሳምንቱ ገጠመኝየሳምንቱ ገጠመኝ

የሳምንቱ ገጠመኝ

ቀን:

እየተቸን እናግዛለን፣ እያገዝን እንተቻለን! ከዚህ ቀደምመስቀል አደባባይ ላይ ምን እየተሠራ ነው?” በሚል ርዕስጋቶቼንና ቅሬታዎቼን አጋርቼ ነበር። በቦታው ላይ ዋንኛ ባለድርሻ የሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የከተማ አስተዳደሩን ምን እየተሠራ እንደሆነ ማብራሪያ መጠየቋ ይታወሳል።

ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የከተማ አስተዳደሩ የቤተ ክርስቲያኒቱን መብትና ጥቅም የሚጋፋ ፕሮጀክት የመገንባት ፍላጎት እንደሌለው ለቤተ ክህነቱ በመግለጽ፣ ዝርዝር ዲዛይኖቹን እንዲያስረዱ በባለቤት በኩል ለዲዛይን ክለሳ (Design Review) የተመደቡ አርኪቴክቶች በአካል ጠቅላይ ቤተ ክህነት በመቅረብ ለቤተ ክርስቲያኒቱ አባቶች እንዲያስረዱ ከማድረጋቸውም በላይ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ የዲዛይንና የግንባታ ሒደቱን በጋራ የሚከታተሉ ባለሙያዎች እንድትመድብ ተደርጓል (ቤተ ክርስቲያኒቱ አስፈላጊ እንደሆነ ባመነችበት ጊዜ መግለጫ የምትሰጥበት ይመስለኛል)፡፡

ምንድነው የሚሠራው?

የፕሮጀክቱ ስያሜ እንደሚገልጸውከመስቀል አደባባይ፣ ላጋር ማዘጋጃ ቤትየሚያጠቃልል ምቹ የእግረኛ መንገድ ማስፋት፣ የቅርሶች ጥገና፣ የአፀዶች መትከል፣ የአረንጓዴ ሥፍራዎች ዝግጅት፣ የመኪና ማቆሚያና የመስቀል አደባባይን በተሻለ መልክ ማዘጋጀትን (Refurbishment) ያካትታል።

ዲዛይነሩ ማነው?

ፕሮጀክቱ የዲዛይን ግንባታ (Design Build) እንደ መሆኑ የግንባታ ሥራውን የተረከበው የቻይናው ሥራ ተቋራጭ በሥሩ አገር በቀል የሆነ አማካሪ ቀጥሯል። የከተማ አስተዳደሩ ደግሞ የዲዛይን ሥራውንና የግንባታ አስተዳደሩን ሙሉ በሙሉ በሥራ ተቋራጩ የተቀጠረው አማካሪ ቢሮ ላይ ላለመተው በራሱ የዲዛይን ክለሳ (Design Reviewer) አማካሪ በካቢኔው ይሁንታ ቀጥሯል።

በዲዛይኑ እነ ማን ተሳትፈዋል?

የመስክ ጉብኝት ባደረኩበት ወቅት ዋናው ተቆጣጣሪ አርኪቴክት (Chief Project Architect) እንዳብራሩልኝ የአርኪቴክቸር፣ የቅርስ ጥበቃ (Conservation) የከተማ ዲዛይን (Urban Design) ባለሙያዎች የሆኑ በርካታ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህራን አብረው እየሠሩ ይገኛሉ (አንዳንዶቹ ዲዛይነሮች የእኔም መምህራን የነበሩ ፕሮፌሰሮች ናቸው)፡፡ የመዋቅር ዲዛይኑን (Structural Design) የሚከታተለው አምስት ኪሎ የሚገኘው የምህንድስና ትምህርት ቤት መምህራን ቡድን መሆኑን አረጋግጫለሁ። ዲዛይኑ ከፍተኛ ጭነት እና ፍንዳታ እንዲቋቋም ታስቦበት መወጋጀቱን ታዝቤያለሁ።

የገጸ ምድር ዲዛይን (Landscape Design) የሚያጠኑ ባለሙያዎች በሥራ ተቋራጩ አማካሪ ሥር ተቀጥረው እየሠሩ ነው። በእኔ ምርመራ ዲዛይኑ የተሰጠበት አካሄድ የመርህ ጉድለት እንደተጠበቀ ሆኖ ፕሮጀክቱ ግን አገሪቱ አሉኝ በምትላቸው ምሥጉን የዲዛይንና የግንባታ ቁጥጥር ባለሙያዎች እጅ ላይ እንዳለ አረጋግጫለሁ።

የሚፈርሱ ቅርሶች አሉን?

ከማዘጋጃ ቤቱ በላጋር እስከ መስቀል አደባባይ ያሉትን ቅርስ የሆኑ ሕንፃዎች (Heritage Buildings) እና ሐውልቶች (Monuments) አንድ በአንድ ለመጎብኘትና በግንባታው የሚደርስባቸው ተፅዕኖ ይኖር እንደሆን ለማጥናት ዕድል አግኝቻለሁ።

የፕሮጀክቱ አማካሪ አርኪቴክት በዝርዝር እንዳስረዱኝና በግሌ የዲዛይን ጥናቶቹን እንዳየኋቸው አንድም የሚነካም ሆነ የሚፈርስ ሕንፃና ሐውልት የለም። በቅርስ ጥበቃ ኤክስፐርቶች ምክር የሚታደሱና ከቅርሶቹ ጋር ወደሚሄዱ አገልግሎቶች (Adaptive Reuse) የሚቀየሩ ግን ይኖራሉ።

የመስቀል ደመራ ዕጣ?

የዲዛይኑም ሆነ የግንባታው ማዕከል በዩኔስኮ የተመዘገበው የደመራውና የመስቀል በዓል አከባበር እንደመሆኑ ይህንኑ መንፈሳዊ እሴት ይበልጥ ለማድመቅና ምቹ ለማድረግ ብዙ እንደተሠራ ታዝቤያለሁ።

ለምሳሌ ደመራው የሚተከልበት ቦታ እንደ መንፈሳዊ ትውፊቱ ከታች ጀምሮ የመጣ ድንግል መሬት ላይ እንዲተከል የተሠራ ሲሆን፣ በገጸ ምድሩ ላይ የተለየ ማድመቂያ ዲዛይን (Surface Aarticulation) ተዘጅቶለታል (ጥንት ንግሥት ዕሌኒ እንደተከለችው ሁሉ ደመራው ከሥሩ በሚገኙ በምድር ቤቶቹ ምክንያት በመጣ ተንሳፋፊ ኮንክሪት ላይ ሳይሆን ተለይቶ በተዘጋጀ መሬት ላይ እንዲተከል ዲዛይኑ ተዘጋጅቷል)፡፡

ግንባታው መቼ ይጠናቀቃል?

የፕሮጀክት ቢሮው ባለሙያዎች እንዳስረዱኝ ለመጪው አዲስ ዓመት የሚደርሰው የደመራው መትከያና አካባቢው መቀመጫ ደረጃዎች ይሆናሉ። ቀሪው የመኪና ማቆሚያ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራዎች እስከ ገና (ታኅሳስ ወር መጨረሻ) ድረስ ሙሉ በሙሉ እንደሚጠናቀቁ ይጠበቃል።

ማጠቃለያ

ከዚህ ቀደም እንዳነሳሁት በዚህ ፕሮጀክት ላይ የነበሩኝ የመርህ (የቅደም ተከተል፣ የአዋጭነት ጥናት፣ የዲዛይን ውድድር፣ ወዘተ) ቅሬታዎች እንደተጠበቁ ሆነው ሥራውን ግን በምንችለው ሁሉ እንደ ዜጋ ማገዝ አለብን ብዬ አምናለሁ። በግሌ በዲዛይኑ ውስጥ ቢካተቱ፣ ትኩረት ቢያገኙ የምላቸውን የባለሙያ ሐሳቦች ለማካፈል ዕድል አግኝቻለሁ። ለዚህም ነውእየተቸን እናግዛለን፣ እያገዝን እንተቻለን!” የምለው።

በአገራችንአኩራፊ እረኛ ቁርሱ ዕራት ሆኖ ይጠብቀዋል (ያውም ቀዝቅዞ) እንደሚባለው የአገርን መልክና የዜጎች ሕይወት በእጅጉ የሚቀይሩና ተፅዕኖ የሚያሳርፉ ፕሮጀክቶችን በአካሄድ ቅሬታ መንግሥትን አኩሩፎ ከዳር ቆሞ በደረቁ ከመተቸት በሐሳብ እየተከራከርን በሥራ ደግሞ እየተጋገዝን መጓዝ አለብን እላለሁ።

መንግሥትም የአካሄድ ችግሮቹን ለማረም የዜጎችን ሙያዊ ትችት ለመቀበል በወቃሽነት ብቻ ሳይሆን፣ በገንቢ ሱታፌ (Constructive Engagement) በቀናነት ሊያየው ይገባል እላለሁ። አሁንም ለግልጽነት (Transparency) እና ለአሳታፊነት (Participatory) ትኩረት ይሰጥ እላለሁ።

ዮሐንስ መኮንን፣ ከአዲስ አበባ)

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...