Sunday, June 16, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ምርት ገበያ 700 ሺሕ ቶን የሚጠጋ ምርት ከ36 ቢሊዮን ብር በላይ አገበያየ

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በ11 ወራት ውስጥ 698,349 ቶን ምርት በ36.1 ቢሊዮን ብር በማገበያየት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት አኳያ በምርት መጠንና በግብይት አፈጻጸም ብልጫ ያለው ውጤት ማስመዝገቡን አስታወቀ፡፡

ምርት ገበያው ካለፈው ዓመት አኳያ በመጠን የአሥር በመቶ እንዲሁም በዋጋ የ16 በመቶ ጭማሪ ያስመዘገበበት የ11 ወራት የግብይት አፈጻጸሙን በማስመልከት ይፋ እንዳደረገው፣ ዘንድሮ በግብይት መጠን የዕቅዱን 96 በመቶ አሳክቷል፡፡ በግብይት ዋጋም በአሥር በመቶ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

ምርት ገበያው በበጀት ዓመቱ 281 ሺሕ ቶን ቡና በ22.3 ቢሊዮን ብር ያገበያየ ሲሆን፣ ይህም በምርት መጠንና በዋጋ ከሌሎች ምርቶች አኳያ ትልቁን ድርሻ እንዲይዝ አድርጎታል፡፡ ምርት ገበያው 240 ሺሕ ቶን ሰሊጥ በ10.4 ቢሊዮን ብር እንዲሁም 76 ሺሕ ቶን አኩሪ አተር በ1.05 ቢሊዮን ብር፣ 51.361 ቶን አረንጓዴ ማሾ በ1.4 ቢሊዮን ብር እንደተገበያየም ገልጿል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ 45 ሺሕ ቶን ነጭ ቦሎቄ 966 ሚሊዮን ብርና አምስት ሺሕ ቶን ቀይ ቦሎቄ በ72 ሚሊዮን ብር አገበያየቷል፡፡ ከዚህ ግብይት ውስጥ ቡና 40 በመቶና ሰሊጥ 34 በመቶ ድርሻ ያላቸው መሆኑም ታውቋል፡፡

ከዚህ ግብይት ውስጥ የቡና ምርት በመጠን አኳያ ሲታይ የዕቅዱን ከስድስት በመቶ በላይ አስመዝግቧል፡፡ ካለፈው ዓመት አንጻርም የአንድ በመቶ አነስተኛ ጭማሪ አሳይቷል፡፡ በዋጋ በኩልም ከዕቅዱ 14 በመቶ ሲያስመዘግብ፣ ካለፈው ዓመት አንጻር በ19 በመቶ ጨምሯል፡፡ የሰሊጥ ግብይትም በመጠን ረገድ ከዕቅዱ 93 በመቶ በዋጋው ደግሞ 102 በመቶ እንዳስመዘገበ ይኸው የምርት ገበያው መረጃ ያሳያል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዚህ ዓመት ግብይቱ በኢትዮጵያ ምርት ገበያ በኩል እንዲከናወን የተደገረው አረንጓዴ ማሾ ከዕቅዱ በላይ በመጠን 50 በመቶ ተገበያየቷል፡፡ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በግብይት ዋጋና በመጠን ከእጥፍ በላይ ጭማሪ እንዳሳየ አስታውቋል፡፡

ምርት ገበያው የኢትዮጵያ ወጪ ንግድ በኮሮና ቫይረስ መዛመት ምክንያት እንዳይስተጓጎል የሠራተኞችንና የገበያተኞችን ደኅንነት ለመጠበቅ አስፈላጊ የመከላከል ዕርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል፡፡ በዚህም መሠረት በሁሉም ቅርንጫፎችና የኤሌክትሮኒክ ግብይት ማዕከላዊ የምርት ቅበላና ግብይት በተጠናከረ ሁኔታ እየተካሄደ እንደሚገኝም ገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች