Monday, October 2, 2023

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የክልል መንግሥታትን የሥልጣን ዘመን በሕገ መንግሥት ትርጓሜ ማራዘሙ የፈጠረው ውዝግብ

- Advertisement -spot_img

በብዛት የተነበቡ

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የዘንድሮውን ምርጫ ማካሄድ ባለመቻሉ ምክንያት የሚፈጠረውን የሥልጣን ክፍተት ሕገ መንግሥቱን በመተርጎም መፍትሔ እንዲሰጥ ለቀረበለት ጥያቄ ሰሞኑን በሰጠው የሕገ መንግሥት ትርጓሜ፣ ከፌዴራል መንግሥት አካላት በተጨማሪ የክልል መንግሥታት የሥልጣን ዘመንንም አንድ ላይ እንዲራዘም መወሰኑ በተለያዩ ወገኖች ዘንድ የሕጋዊነት ጥያቄና ሙግት ቀስቅሷል።

የፌዴሬሽን ምክር ቤት የክልል መንግሥታት ምክር ቤቶችንና አስፈጻሚ አካላትን የሥልጣን ዘመን እንዲራዘም የሰጠው ትርጓሜ፣ጋዊነት የሌለውና ባልቀረበለት ጉዳይ ላይ የተሰጠ የሕጋዊነት ችግር ያለበት ትርጓሜ በመሆኑ እንግዳ ነገር ነው ሲሉ የተለያዩ የሕግ ልሂቃን፣ እንዲሁም የሕገ መንግሥት ትርጉም ሒደቱን ለማገዝ ሙያዊ ምክረ ሐሳባቸው የሰጡ አንዳንድ የሕገ መንግሥት ምሁራን ጭምር ጥያቄ አንስተውበታል።

በፌዴሬሽን ምክር ቤት የትግራይ ክልል ተወካይ የሆኑ አባላትም፣ ምክር ቤቱ የክልልን የሥልጣን ዘመን የማራዘም መብት የለውም ሲሉ በወቅቱ ሞግተዋል። ለሕገ መንግሥት ትርጓሜው የውሳኔ ሐሳብ ያቀረበው የሕገ መንግሥት አጣሪ ጉባዔ በበኩሉ የክልል መንግሥታትን የሥልጣን ዘመን ማራዘም የተመለከተ ግልጽ ጥያቄ ባያቀርብም፣ ከተፈጠሩት አጠቃላይ ሁኔታዎች ይዘት አንፃር የክልል መንግሥታትን ጉዳይ መመርመር እንዳለበትና በትርጓሜ የውሳኔሳቡ እንዲካተት ማድረግ ተገቢ ሆኖ እንዳገኘው ይገልጻል።

የተጠየቀውና የተወሰነው የሕገ መንግሥት ትርጓሜ ምንድናቸው? የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዘንድሮ ምርጫን ቦርዱ ለማካሄድ እንደማይቻል ተረድቶ ከተቀበለ በኋላ፣ ሚያዚያ 7 ቀን 2012 ዓም ባካሄደው ስብሰባው በኮሮና ወረርሽኝ የጤናጋት ምክንያትና እሱን ተከትሎ በተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምርጫ ማካሄድ ካልተቻለ የሥልጣን ዘመናቸውን የጨረሱ ምክር ቤቶች የሥልጣን ዘመን ምን መሆን እንደሚችል የሕገ መንግሥት ትርጉም እንዲሰጥበት በመወሰን፣ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ልኳል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረበው የሕገ መንግሥት ትርጉም ጥያቄ ቃል በቃል የሚከተለውን ይመስላል።

‹‹….ምርጫ በሚደረግበት ወቅት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማወጅ የሚያስገድድ ሁኔታ ቢከሰትና በዚህም የተነሳ ምርጫ ማድረግ የማይቻል ቢሆን፣ የምርጫ ዘመናቸውን ያጠናቀቁ ምክር ቤቶችና የሥራ አስፈጻሚው የመንግሥት አካል የሥልጣን ዘመን ምን ይሆናል? ምርጫውስአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማወጅ ምክንያት የሆነው ክስተት ከተወገደ በኋላ በምን ያህል ጊዜ ውስጥ ሊከናወን ይገባል? ለሚሉት ጥያቄዎች ሕገ መንግሥቱ ምላሽ ባለመመለሱ የገጠመንን ችግር በመፍታት ረገድ፣ ሕገ መንግሥቱ ክፍተት አለበት የሚያስብል ነው። በመሆኑም ከፍ ብለው የተገለጹትን ድንጋጌዎች ከሕገ መንግሥቱለማና ግቦች፣ እንዲሁም መሠረታዊ መርሆዎች ጋር በማገናዘብ ትርጉም እንዲሰጣቸው በአብላጫ ድምፅ ወስነናል፤›› የሚል ነው።

ይህንን ተከትሎም የፌዴሬሽን ምክር ቤት በቀረበለት የሕገ መንግሥት ትርጉም ጥያቄ ላይ የውሳኔ ሐሳብ እንዲያቀርብለት በሥሩ ለሚገኘው የሕገ መንግሥት አጣሪ ጉባዔ የመራ ሲሆን፣ አጣሪ ጉባዔውም ጉዳዩን በጥልቀት መርምሮ የደረሰበትን የትርጉም ውሳኔ ሐሳብ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት አቅርቦ ምክር ቤቱ ሰኔ 3 ቀን 2012 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባውሳኔ ሐሳቡን ሙሉ በሙሉ በአብላጫ ድምፅ አፅድቆታል። የአጣሪ ጉባዔውን የውሳኔ ሐሳብ ተቀብሎ የሰጠው ትርጓሜም የሚከተለው ነው።

‹‹የኮሮና ወረርሽኝ (ኮቪድ 19) የሕዝብ ጤና ሥጋት ሆኖ ባለበትና የበሽታውንርጭት ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ፀንቶ በሚቆይባቸው ጊዜያትና ከተነሳም በኋላ አዲስ ምርጫ ተካሂዶ የሥልጣን ርክክብ እስኪፈጸም ድረስ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ የክልል ምክር ቤቶችና የፌዴራልና የክልል አስፈጻሚ አካላት የሥራ ዘመን እንዲቀጥል›› የሚለው አንደኛው ትርጓሜ ነው፡፡

ሌላኛው ትርጓሜ ደግሞ፣ ‹‹የኮቪድ 19 ሥርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ ምክንያት የሆነው ወረርሽኝለም አቀፍና አኅጉር አቀፍ የጤና ድርጅቶች የሚያወጡትን መረጃ መሠረት በማድረግ የጤና ሚኒስቴር፣ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትና የሳይንሱ ማኅበረሰብ አካላት ወረርሽኙ የሕዝብ ጤና ሥጋት አለመሆኑን ካረጋገጡበት፣ ይህም በሕዝብ ተወካዩች ምክር ቤት ከፀደቀበት ቀን ጀምሮ ከዘጠኝ ወራት እስከ አንድ ዓመት ባለው ጊዜ ውስጥ ምርጫው እንዲካሄድ፤›› የሚል ነው፡፡

የክልሎች የሥልጣን ዘመን ለማራዘም የቀረበውጋዊ ትንታኔ አጣሪ ጉባዔው ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ባቀረበው ዝርዝር የውሳኔ ሐሳብ ላይ፣ ለምን የክልል ምክር ቤቶች ሥልጣን መረዛምን እንደተመለከተ ትንታኔ ሰጥቶበታል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በምክር ቤቱ የቀረበው የሕገ መንግሥት ትርጉም ጥያቄና የሚሰጠው የትርጉምና የውሳኔ ሐሳብ ተፈጻሚነት፣ በፌዴራል ምክር ቤቶችናአስፈጻሚው አካላት ላይ ብቻ ነው? ወይስ በክልል ምክር ቤቶችናአስፈጻሚው አካላትና በክልል የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ላይ ጭምር ነው? የሚለውን ያመላክታል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረበው አጠቃላይ የትርጉም ጥያቄ በአጠቃላይ አገላለጽ የምክር ቤቶቹና የአስፈጻሚው አካል ሥልጣን እንዴት ይሆናል የሚል ቢሆንም፣ ለትርጉም ጥያቄው መነሻ የሆነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት፣ መጪውን ጠቅላላ ምርጫ ማድረግ አለመቻሉ እንደሆነ ያስቀምጣል። ጠቅላላ ምርጫ ማለት ደግሞ የፌዴራል ምክር ቤቶችን ምርጫ ብቻ የሚመለከት ሳይሆን፣ ሁሉንም የክልል ምክር ቤቶች የሚመለከት እንደሆነ ይገልጻል፡፡

በሌላ በኩል ለትርጉም ጥያቄው መቅረብ ምክንያት የሆነውን የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣውአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተፈጻሚነትም በፌዴራል መንግሥት የተገደበ ሳይሆን፣ ክልሎችንም የሚጨምር መሆኑን ያስረዳል፡፡ በሕገ መንግሥት አንቀጽ 102 መሠረት በፌዴራልና በክልሎች ነፃና ትክክለኛ ምርጫ በገለልተኛነት እንዲካሄድ፣ ከማንኛውም ተፅዕኖ ነፃ የሆነ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ እንደሚቋቋም መደንገጉንና የዚህ ቦርድ መቋቋም ዋነኛ ዓላማም ገለልተኛ፣ ከማንኛውም ተፅዕኖ ነፃ የሆነ ምርጫ እንዲካሄድ ለማድረግና ለማስፈጸም መሆኑንም በትንታኔው አመልክቷል።

ከዚህም መረዳት የሚቻለው ቦርዱ እንዲቋቋም የተደረገው በፌዴራልና በክልሎች ምርጫን ለማስፈጸም እንደሆነ፣ ይህም የሚያስረዳው የፌዴራል መንግሥት ሥልጣን የምርጫ ሕግ የማውጣት ብቻ እንዳልሆነና በፌዴራል መንግሥት የሚወጣውን የምርጫ ሕግ በፌዴራልና በክልሎች የማስፈጸም ሥልጣንና ኃላፊነትም የፌዴራል መንግሥት መሆኑን በትንታኔው ሠፍሯል፡፡ አሁን የሕገ መንግሥት ትርጉም ጥያቄ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲያቀርብ፣ በጥቅሉ የምክር ቤቶችና አስፈጻሚው አካል ሥልጣን ምን እንደሚሆን የሚጠይቅ ቢሆንም፣ በሌላ በኩል ደግሞ ለሕገ መንግሥት ትርጉም ጥያቄ ምክንያት የሆነው የምርጫ ቦርድ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 102 መሠረት ጠቅላላ ምርጫ በፌዴራልና በክልሎች የምርጫ ክልሎች ለማካሄድ አቅዶ አለመቻሉን ባደረገው ምርመራ መረዳት እንደቻለ አመልክቷል። ቦርዱ ዝግጅት ጀምሮ የነበረው ጠቅላላ ምርጫን ለማካሄድ ሲሆን፣ በኮቪድ-19 ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ምክንያት ሳያደርግ ያቋረጠውም ይህንኑ ጠቅላላ ምርጫ በመሆኑ፣ የውሳኔ ሐሳቡ በፌዴራሉና በክልሎች የምርጫ ጊዜና በምክር ቤቶችና በአስፈጻሚዎች የሥራ ዘመን ላይ ተፈጻሚነት ሊኖረው ይገባል ብሏል።

በዚህ ላይ የተነሱ የሕጋዊነት ጥያቄዎች አጣሪ ጉባዔው የክልል ምክር ቤቶችና አስፈጻሚዎች የሥልጣን ዘመን እንዲራዘም በማለት ላቀረበው ትርጓሜ የሰጠውን የሕግ ትንታኔና አመክንዮ አስመልክቶ ሪፖርተር ያነጋገራቸውአጣሪ ጉባዔው ምርመራ ባደረገበት ወቅት ሙያዊ አስተያየታቸውን የሰጡት ዘመላክ አይተነው (/)፣ አጣሪ ጉባዔው በዚህ ጉዳይ ላይ ለደረሰበት የትርጉም ድምዳሜ የሰጠው ትንታኔ ደካማና አሳማኝ አለመሆኑን ገልጸዋል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፌዴራሊዝምና የአስተዳደር ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር የሕግ ምሁሩ ዘመላክ (ዶ/ር) አጣሪ ጉባዔው ጉዳዩን የመረመረበት ግልጽነትንና ሙያተኞችን ያሳተፈደት የሚደነቅና ተስፋ ሰጪ የነበረ ቢሆንምያቀረበው የውሳኔ ሐሳብ ግን ጎዶሎና የጠበቁትን ያህል እንዳልሆነ አስረድተዋል፡፡ ለአብነትም አጣሪ ጉባዔው የክልል መንግሥታትን የሥልጣን ዘመን ሊራዘም ይገባል ብሎ የወሰነበት የሕግ አመክንዮና ትንታኔ ደካማ ከመሆኑም በላይ፣ ለደረሰበት ድምዳሜ የሚያበቃ ሆኖ አላገኘሁትም ብለዋል

የክልሎች ሉዓላዊ ሥልጣን ከሚገለጽባቸው ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮች አንዱ ራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደር መብታቸው ሆኖ ሳለ፣ አጣሪ ጉባዔው የክልሎች መሠረታዊ የሥልጣን ባለቤትነት መገለጫዎች የሆኑትን ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌዎች በትንታኔው ሳይገመግም አስተዳደራዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ተመሥርቶ የሥልጣን ዘመናቸው እንዲራዘም መወሰኑና ይህንንም ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ማቅረቡ ስህተት እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡

የክልሎችን ሥልጣን አብሮ ሊራዘም አይገባም ከሚሉ ወገኖች ተርታ እንዳልሆኑ የሚናገሩት የሕግ ምሁሩ፣ በአጣሪ ጉባዔው የቀረበው አመክንዮ ግን ወደዚያ ለመድረስ የሚያስችል ነው ብለው እንደማያምኑ ገልጸዋል።

አጣሪ ጉባዔው ጉዳዩን በመረመረበት ወቀት ሙያዊ አስተያየታቸውን ከሚገኙበት ኔዘርላንድስ ሆነው በቪዲዮ ኮንፈረንስ ሙያዊ አስተያየታቸውን የሰጡት ሌላው የሕገ መንግሥት ምሁር አደም ካሴ (/)፣ አጣሪ ጉባዔው የክልል መንግሥታትን የሥልጣን ዘመን እንዲራዘም የሚል ውሳኔ ሐሳብ ማቅረቡን፣ ምክር ቤቱም ይህንኑ ተቀብሎ ማፅደቁን ‹‹ያልተጠበቀ እንግዳ ነገር ሲሉ›› ገልጸውታል።

አደም (/) ጉዳዩን አስመልክቶ በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት አስተያየት ውሳኔው ተገቢ አይደለም ያሉባቸውን ምክንያቶችም በመጠኑ አብራርተዋል። ‹‹አንደኛ የክልል መንግሥታት የሥልጣንን ዘመን በራሳቸው ሕገ መንግሥት እንጂ፣ በአገሪቱ ሕገ መንግሥት ተወስኖ አልተቀመጠም፤›› ብለዋል። ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚደረግ ምርጫ በአንድ ወቅት በመላ አገሪቱ መካሄዱ ግልጽና አሳማኝ እንደሆነ ያመለከቱት የሕግ ምሁሩ፣ ነገር ግን የሁሉም የክልል መንግሥታት ምክር ቤቶች ምርጫ በአንድ ቀን መፈጸም አለበት ለማለት የሚያስችል ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌም ሆነ ምክንያት አለመኖሩን አስረድተዋል፡፡

ነገሩን በምሳሌ ሲያስረዱም፣ ‹‹የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሥልጣን ዘመኑን ሳያጠናቅቅ ቢፈርስ፣ የክልል ምክር ቤቶችም አብረው ይፈርሳሉ ማለት አይደለም። በተመሳሳይ የአንድ ክልል ምክር ቤት የሥልጣን ዘመኑ ሳያልቅ ቢፈርስ በዚያው ክልል ብቻርጫ ይከናወናል እንጂ፣ ወደ ተቀሩት ክልሎች ምክር ቤቶችም ሆነ የፌዴራል ምክር ቤቶች አይተላለፍም፤›› ሲሉ መከራከሪያ አቅርበዋል።

የክልል ምክር ቤቶች የሥልጣን ዘመን በአገሪቱ ሕገ መንግሥት ተወስኗል ቢባል እንኳን፣ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር በመሆን የክልሎቹን ሁኔታ አንድ በአንድ በማየት መወሰን ይገባ እንደነበረ በመግለጽ የውሳኔውን ተገቢነት ጠይቀዋል።

በተመሳሳይ ለአጣሪ ጉባዔው ሙያዊ አስተያየታቸውን የሰጡት ሌላው የሕገ መንግሥት ምሁር ዮናታን ፍሰሐ (/) በሰጡት አስተያየት፣ የፌዴራልርዓትን ከሚከተሉ ሌሎች አገሮች ሕገ መንግሥት በተለየ መንገድ የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ስለክልል መንግሥታት አደረጃጀትና አሠራር የሚደነግገው አለመኖሩን ጠቁመዋል። ከሌሎች አገሮች በተቃራኒ የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ይህንን ጉዳይ ክልሎች በራሳቸው ለሚያወጡት ሕገ መንግሥት እንደተወ ይገልጻሉ።

በመሆኑም የክልል ምክር ቤቶችንና የክልል አስፈጻሚ መንግሥታትን የተመለከተ ማንኛውም ውሳኔ፣ በዋናነት የክልሎቹን ሕገ መንግሥት መሠረት አድርጎ መወሰን እንደሚገባው አመልክተዋል። ‹‹ይህ ማለት ግን የክልል መንግሥታት ውሳኔ ከአገሪቱ ሕገ መንግሥት ጋር የተጣጣመ መሆኑ መፈተሽ ይኖርበታል፤›› ብለዋል።

ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ ሌላ የሕገ መንግሥት ምሁር ደግሞ፣ አጣሪ ጉባዔውም ሆነ ምክር ቤቱ ክልሎችን አስመልክቶ የሰጡት ትርጓሜ ባልተጠየቁት ጉዳይ ላይ የተሰጠ ትርጉም መሆኑን ጠቁመዋል።

የሕግና የፖለቲካ ጉዳዮች ተንተኝ የሆኑት ሌላው የሕግ ባለሙያ አቶ አብዱ ዓሊ ሒጅራ ግን ነገሩን ከሌሎቹ በተለየ ሁኔታ በመመልከት፣ አጣሪ ጉባዔው የክልል መንግሥታትን የሥልጣን ዘመን ማራዘሙ ተገቢ እንደሆነ ይከራከራሉ። እንደ የፖለቲካ ሥልጣን በምርጫ በሚገለጽ የሕዝብ ይሁንታ ብቻ እንደሚያዝ የሚያመለክተው የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 9 በመላ አገሪቱ ሳይሸራረፍ ተግባራዊ የሚደረግ በመሆኑ፣ ይህንን ምርጫ ደግሞ በአሁኑ ወቅት ማድረግ የማይቻል ስለሆነ የክልል መንግሥታት ሥልጣን መራዘሙ ትክክል እንደሆነ ይከራከራሉ።

አሁን ባለው ሁኔታ በርካታ ክልሎች ርዕሰ መስተዳደር ስለሌላቸው በምክትል ርዕሰ መስተዳደር እየተዳደሩ እንደሆነ ያስታወሱት አቶ አብዱ፣ ይህንን ሲያደርጉ ሕገ መንግሥቱን ጥሰው ሥልጣን መያዛቸውንና የክልላቸውን ሕዝብ ባልመረጠው መሪ እንዲተዳደር ማድረጋቸውን የሚዘነጉ ፖለቲከኞች፣ የተሰጠውን ውሳኔ ተቃውመው የሕገ መንግሥቱ ጠበቃ ሆነው ሲከራከሩ ማየት የሚጋጭ ነው ሲሉም ትችታቸውን ሰንዝረዋል።

ጉዳዩ ከላይ በተገለጹት የሕጋዊነት ክርክሮች ብቻ የታጀበ አይደለም። የተጠየቀውን የሕገ መንግሥት ትርጉም ከመጀመሪያው አንስቶ የሚቃወመው ሕወሓትና የሚያስተዳድረው የትግራይ ክልል አመራሮች፣ እንዲሁም ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) ጨምሮዘንድሮ ምርጫ በወቅቱ በትግራይ ክልል እንደሚካሄድ እየገለጹ ነው። ለዚህም የክልሉ መንግሥት አስፈላጊውን የፖለቲካና የምርጫ ዝግጅት በማድረግ ላይ እንደሚገኝ በተደጋጋሚ እየገለጹ ናቸው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ሰሞኑን ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጥያቄ የቀረበላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (/) በበኩላቸው፣ ተቃራኒ የፖለቲካ አቋሞችን መግለጽ መብት እንደሆነ፣ ነገር ግን ንግግሩን ወደ ተግባር መቀየር ሕገ መንግሥቱን መጣስ በመሆኑ እንደማይቻል አስጠንቅቀዋል። ነገር ግን የትግራይ ክልል ምክር ቤት ዓርብ ሰኔ 5 ቀን 2012 ዓ.ም. ምርጫ ለማካሄድ መወሰኑን አስታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ትኩስ ጽሑፎች

ተዛማጅ ጽሑፎች

- Advertisement -
- Advertisement -