Monday, July 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
እኔ የምለዉየዘር ውርስ ይዘታቸው የተለወጡ አዝርዕት ለአገራችን ግብርና ሥር  ነቀል መፍትሔ ዕድል ወይስ...

የዘር ውርስ ይዘታቸው የተለወጡ አዝርዕት ለአገራችን ግብርና ሥር  ነቀል መፍትሔ ዕድል ወይስ ሥጋት? (የመጨረሻው ክፍል)

ቀን:

አማረ ተግባሩ (ዶ/ር)

የዘር ውርስ ይዘታቸው የተለወጡ አዝርዕት (Genetically Modified Organisms) ላይ የሌሎች አገሮች  ልምድ እጅግ ጠቃሚ መሆኑን አሁንም ደግሜ ማስገንዘብ እወዳለሁ። በየትኛው መንገድ እንሂድ ለሚለው፣ ወይም ደግሞ ሁለቱንም መንገድ አቻችለንና ሥርዓት ዘርግተን፣ የባዮፍቲ ቁጥጥሩንም ተቋማዊ (Biosafety Regulation) አድርገን ባዮክኖሎጂ በከፈተልን ዕድል ንጠቀምም ያልን ንደሆነ የሌሎች አገሮች ልምድ ያስፈልገናል። የግ ማሻሻያ እናድርግ እንኳ ብንል ያለነው በኮሮና ወረርሽኝ ዘመን መሆኑን ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት ተገቢ ነው። የዚህ ወረርሽኝ መዘዝ ገና ለረጅም ጊዜ እንደሚከተን በማወቅ የምግብና ጤና ዋስትና፣ የገቢ ምንጭና ሥራ ፈጠራ ላይ ላለን ይታና ተስፋ ይህ አዲሱ ቴክኖሎጂ በግብርናው ሥነ ምዳር ላይ ምን ያህል ር ነቀል ያመጣልናል? ወይስ ያልተጠበቀና ልንቆጣጠረው ወደማንችለው ችግር ውስጥ ይጨምረናልን? ብለን በደንብ ማሰብ ይኖርብናል። ሚዛናዊ ሆኖ ለመጓዝ እንድንችል ከዚህ በታች የታንዛኒያንና ኬንያን ልምድ በማሰስ ወደ አገራችን ሁኔታ በመመለስ ጽሑፌን እደመድማለሁ። 

ታንዛያ ምን ወሰነች? ለምን?

የታ መንግሥት እ.ኤ.አ. በኖቬምበር 2018 ባወጣው መግለጫ በአገሪቱ የግብርና ምርምር ጣቢያዎች የሚገኝ ማንኛውም የዘር ውርስ ይዘቱ የተለወጠ ምርምር እንዲታገድ፣ የሙከራ ጣቢያችም እንዲዘጉና በዚህ ምርምር አማካነት የተሰበሰበ መረጃ በመንግሥት እንዲወረስአለበለዚያም ባላበት እንዲደመሰስ ጥብቅ ትዕዛዝ ተላልፏል። በታንዛ ግብርና ስቴር ጃፕሄት ሃሱንጋ የተፈረመበት ይህ ድንገተኛና ያልተጠበቀ ውሳኔበተለይ ከሚመለከታቸው አዝርዕት መካከል በርካታ የአገሪቱ የግብርና ሳይንቲስቶች የተሳተፉበትና የደሙበት በቆሎ ይገኝበታል። አገሪቱ የዘር ውርስ ይዘቱ በተለወጠ በቆሎ ላይ ምርምር ማድረግ የጀመረችው እ.ኤ.አ. በ2016 ሲሆንይህ በዘር ምህንድስና ዝርያው የተለወጠው በቆሎ ድርቅንና በሽታን ይቋቋማል ተብሎ ተጠቆ ነበር።

ወደ ገበሬው ማሳ ከመግባቱ በፊት በሙከራ ጣቢያዎች ተዘርቶ እንደነበርለገበያም ሆነ ለገበሬው ከመለቀቁ በፊት ማረጋገጫ (Certified) ለማግኘት ተራ ይጠብቅ ነበር። በአ የግብርና ስቴር ትዕዛዝ ገዳ ብቻ ሳይሆን እስከ እ.ኤ.አ. 2018 ረስ የተደረገውን ምርምር በሚመለከት የተሰበሰበው መረጃ ጭምር ለመንግ የቁጥጥር አካል በውርስ እንዲገባና በሙከራ ጣቢያዎችም ያለው (GM) በቆሎ እንዲወገድ ወስኗል። ይህ ድንገተኛ ውሳኔ ያስከፋቸውም ያስደሰታቸውም ወገኖች ቢኖሩምበግብርና ስቴር በኩል የተሰጠው ዋነኛ ምክንያት የሚከተለው ነው። That GMO seeds will deny farmers the right to choose the kind of seeds they wanted,… That GMO seeds will wipe out traditional seeds and make farmers dependent on foreign seed merchants” (Japeth Hausnga, Minister of Agriculture November 2018).

ይህንን የመንግሥት ውሳኔ የታንዛ አገር አቀፍ አምራች ገበሬዎች በር ደግፎታል። በሌላ በኩል የታንዛ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚ አገሪቱ እ.ኤ.አ. በ2013 ያሳለፈችውን የግብርና ምርምር ፖሊሲ በመጥቀስ ይህንን በቆሎ የተመለከተው ገዳ አገሪቱ በባቴክኖሎጂ ዘርፍ የምታደርገውን ምርምር እንደማይገታው አስምሮበታል። የዚህ ምርምር አስፈላጊነትም የአገሪቱን የግብርና ምርት አስተማማኝና ጤናማ በሆነ መንገድየመደገፍና በሰውም ሆነ በተፈጥሮ ላይ ምንም ይነት ጉዳት በማያመጣ መንገድ የግብርናው ሥነ ዳር ያለበትንና ወደፊት የሚያጋጥሙትን ተግዳሮቶች ለመፍታት አጋዥ ከመሆን እንደማይከለክለው አስታውቋል።

በኬንያስ ምን በመደረግ ላይ ይሆን?

 እ.ኤ.አ. ማርች 31 ቀን 2020 ጆን ንጂራኒ ከኬንያ ራዊ ባዮሴፍቲ (Biosafety) ባለሥልጣን መሥሪያ ቤት ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ዶሪንግተን ኦሳይ ጋር ያደረገውን ቃለ ምልልስ Agri Business Global” በተባለው መጽሔት አውጥቶታል። ዋና ዳይሬክተሩም የዘር ውርስ ይዘታቸው የተለወጠ ጥጥና በቆሎን በተመለከተ ኬንያ አሁን የምትገኝበትን ሁኔታ አስረድተዋል። እሳቸው እንደሚሉት የባዮቴክኖሎጂ ጥጥ በተመለከተ በርካታ ሙከራዎች ረዘም ላሉ መታት የተደረገ ሲሆንበተፈጥሮ ሥነ ዳሩ ላይ ምንም ጉዳት እንደማያመጣ የመንግ የማረጋገጫ ምስክር ከመሰጠቱና ለገበያ ከመለቀቁ በፊትአንድ የመጨረሻ ሙከራ ለማድረግ በመዘጋጀት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ይህም ለዚህ ጥጥ ይስማማል ተብሎ የተመረጠው ሥነ ምዳር በሚገባ የተጠናና ለዚሁ ተብሎ የተከለለ መሆኑንም ጨምረው አስረድተዋል።

‹‹በቆሎን በተመለከተ ግን በተመሳሳይ መንገድ ለበርካታ ዘመናት ምርምር የተደረገና በሙከራ ደረጃ መረጃ በማሰባሰብ ላይ ስንሆንያልተጠበቁና ገና መልስ ያላገኘንባቸው የምርምር ተግዳሮቶች ገጠመውናል፤›› ሲሉ አስረድተዋል። እነህን ተግዳሮቶች ለመፍታት እንደገና መፈተሽ የሚኖሩብን በርካታ ጉዳዮች አሉ በማለት የዘር ውርስ ይዘቱ የተለወጠ በቆሎ በቶሎ ከራው ተሳክቶና የመንግ የማረጋገጫ ሰፊኬት አግኝቶወደ ገበሬው ማሳም ሆነ ወደ ገበያ በዚህ ጊዜ ይለቀቃል ማለት እንደማይችሉ አስገንዝበዋል። ዋናው ዳይሬክተር ከባዮሴፍቲ የቁጥጥር ሥርዓትን የማስከበር ላፊነት አገራዊ ላፊነትና ግዴታ መሆኑን በማውሳት፣ ‹‹ኬንያ ከ2012 ዓ.ም. ጀምሮ የዘር ውርሳቸው የተለወጡ አዝርዕቶችን ደ አገሯ እንዳይገባ ገዳ ያደረገች ቢሆንምወደፊት ይህ ገዳ ተነስቶ አገሪቱ ባዮቴክኖጂ የከፈተውን ዕድል ትጠቀም እንኳን ቢባል አገር በቀል ሆነውን በኬንያ ገበሬዎ እጅ ካለውና ከዘመን ዘመን ሲገላበጥ ከኖረው የበቆሎ ዝርያ አብሮ ጎን ለጎን የምናስኬድበትን የምርምር ሥርዓትና ደንብ እዘረጋለን እንጂየበ ዝርያዎቻችን በልውጥ በቆሎ እንዲተካ በማድረግ የዘር ብዝነት ከግብርናው ሥነ ምኅርሶ እንዲጠፋ አስተዋጽኦ አናደርግም፤›› ብለዋል። ይህንን ለማድረግ የቻሉ እንደ ብራዚል የመሰሉ አገሮችን በመጥቀስ፣ ‹‹የኬንያ ግብርና ምርምርም ይህንን ያስችለናል ብለን እናምናለን፤›› ሲሉ ቃለ ምልልሳቸውን ደምድመዋል።

እነዚህ አገሮች ልምድ ይህ ከሆነ ራሳችን የንቀስመው ትምህርት ምንድነው? 

ከሌሎች አገሮች ልምድ ለመማር የራሳችን ልምድ ምን አንደሚመስልና በራሳችን ሳይንቲስቶች አማካነት በግብርና ምርምር ጣቢያዎቻችን የተራውን ሥራ ብርታትና ድካም በሚገባ መገምገም ይኖርብናል። ባለን ላይ የምንገነባው ውቀት ምንድነው? ከማለት ያለፈ ምንም የተካና የአገራችን ግብርና ለሚያስፈልገው ነቀል ለውጥ፣ ዕውቀቱንም ቴክኖሎጂውንም ከውጭ ንዳለ ለመገልበጥ ወይም ለመመፅወት ባዶ እጃችንን ከቀረብንና አቋራጩም ከመሰለን ስኬታማ አንሆንም። ስለዚህም የራሳችንን ድክመትም ሆነ ብርታት ስንገመግም ይቅርታ የለሽ ችና በምናፍርበት ማፈራችንን በምንኮራብት ደግሞ ኩራታችንን ከመናገር ወደ ኋላ ማለት አይገባንም።  

በበኩሌ መንግሥት የአገር ውስጥና የውጭ የግል ባለብቶች በግብርናው ዘርፍ በመማራት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና እንዲጫወቱ ሁኔታዎችን አመቻችቶ እንደነበር በሰፊው ሲዘመርለት የነበረው ጉዳይ መጨረሻው ምን እንደሆነ ሳስታውስ ከማፈር ይልቅ አዝናለሁ። ደን እየተመነጠረና ዝብ በማፈናቀል ለውጭ ባለብቶች ሰፋፊ እርሻ ማስፋፊያ ተችሮ ነበር። ውጤቱ ግን ያ የተመነጠረውና ለሰፋፊ የግል እርሻ የተዘጋጀው መሬት አገሪቱ ከውጭ የምታስገባውን ምግብ ለመቀነስና የምታርተውንና ወደ ውጭ የምትልከውን በጥራትና በብዛት በማምረት የውጭ ምንዛሪ የምታገኝበት ላይ ያተኮረ አንዳልነበረ ይታወቃል። እነህ የውጭ ባለ ብቶች ያመረቱትና ለማምረትም የተጣደፉበት የውጭ ገበያ የሚፈልገውንና ላፈሰሱት መዋዕለ ንዋይ በለም ገበያ በአጭር ጊዜ ከፍተኛ ትርፍ አግኝተው፣ ደናችንን ጨፍጭፈው፣ ለዝብ መፈናቀል ምክንያት ሆነው፣ የመሬታችንን ምርታማነት አውድመው፣ የው ብታችንን መርዘውና በእነዚህ ከፍተኛ እርሻዎች ላይ ተቀጥረው በሚሩ ወንድና ሴት የዘመናዊ እርሻ ራተኞች ላይ የጤና ቀውስ ፈጥረው፣ ከግብር ነፃ ላስገቡት ንብረት ማንም ሳይጠይቃቸው ከአገር መልቀቃቸው የአደባባይ ሚስጥር ነው።

ሎችም በምግብ ዋስትና ላይ ያተኮረ የምርት እንቅስቃሴ የነበራቸው የውጭ ባለብቶች እንደነበሩ ቢሰማምምንና ለምን ያህል ጊዜ እንዳመረቱ መረጃው የለም። እነህም ባለብቶች ይዘውት ወደ አገራችን የገቡት ‘ምርጥ ዘር’ ምን ያህል በበቂ የተመረመረና ለአገራችንና ለአካባቢው ሥነ ምዳር (Agroecological System) የሚስማማ ወይም የማይስማማ መሆኑ ምንም መረጃ ሳይቀርብበት የተቸረው መሬት እንዳለ ምድረ በዳ ሆኖ ቀርቷል። ይህን ስናይ በመንግሥት በኩል የምግብ ዋስትናን ለማረገጋጥና ከምግብ አስመጭነትና ተመፅዋችነት ለመገላገል በሚል የሚጀመረው ሁሉ ዳር ሳይደርስ ተሰናክሎ የሚቀርበት ምክንያት በቅድሚያ መመርመር ይኖርበታል።

ይህ አገራዊ ሳራ ላይ እንዴት ልንደርስ እንደቻን ግልነት የተሞላው ግምገማ ሳናደርግየዘር ውርስ ይዘታቸው የተለወጡ አዝርዕት ደ አገራችን እንዳይገቡ ገዳ የተደረገባቸው አዝርዕቶች ወደ ግብርናው ሥነ ምዳር ለማስገባት በቅድሚያ የምክር ቤት የግ ማሻሻያ እንዲቀርብ እንዲደረግበት የተያዘው እሽቅድድም በአገራችን ግብርና ምርምርና ልማት ቤተሰብ ጥያቄ ቢቀርብበት የሚገርም አይሆንም። አሁንም በበቂ ይመከርበት የባዮቴክኖሎጂ ጥጥ፣ ቀጥሎም በቆሎ፣ ከዚያ ወደ እንት ቢገባና ምልባትም በተመሳሳይ መንገድ የውጭ ባለብቶች በግብርናው ሥነ ምዳር መዋዕለ ንዋያቸው የሚያፈሱበት ሆኖ ቢለቀቅ ውጤቱ ባለፈው ከተራው ስህተት  እንዲያውም በከ ሁኔታ እንደማይደገም ምን ማረጋገጫ አለን? እንዲያውም በቡናውና ጤፉ ላይ እንደ ደረሰው የእንቱን ተፈጥሯዊ ዝያ ሚስጥር (Germplasm) ማዘረፍና ከአገር እስከ ማስኮብለል እንደማንደርስ ዋስትናው ምንድነው?

 የባዮቴክኖሎጂ ጥጥ ዋነኛውና እጅግ ወሳኙ የማሻሻጫ ምክንያትበሽታን የመከላከል አቅሙ ላይ የተመረተ ነው። እስካሁን በአገራችን የጥጥ ተክልን ሲፈታተን የኖረው በሽታ ሃምራዊ (Bollworms) የሚባለው እንደሆነ፣ የአገራችን የግብርና ምርምር ሊቃውንካሳተሟቸው ጥናቶች መረዳት ይቻላል። ይህ ጥጥ ይህንን በሽታ እንዲቋቋምልን ከሆነ ከ1970 መጨረሻ አንስቶ እስከ 1989ዎች መጀመ ድረስ የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት (EIAR) በራሱ አገር በቀል ተመራማሪዎች ይህንን ተባይ ለመቆጣጠርና ለምርት ማሽቆልቆል ያሳደረውን ተፅዕኖ ለመግታት የሚያስችበርካታ ሙከራዎችን በማድረግእጅግ ስኬታማ ውጤት ተገኝቶ እንደነበር የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩትን የምርምር ታሪክና በለም አቀፍ ግብርና ምርምር የታተሙ ጥናቶችን መልሶ መፈትሽ ይቻላል  (Tsedeke Abate 2019)።

ይህ ላይ ትኩረት ያደረገ ውጤት የሚያስፈልገው ድጋፍ ቀርቦለት ተጠናክሮ ተቋማዊ መሆን ይችል መቅረቱ ከፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ጋር የተያ ባለን ላይ ከመንባት ይልቅ በማፍረሱ የግብርና ምርምርን በመሸንሸንና እንደ ቅርጫ ሥጋ ለሚፈልግ ሁሉ በማዳረሱ ላይ በማተኮራችን ነው። ይህ ጉዳይ መልሶ የሚፀፅ ቢሆንም፣ በአሁኑ በአገራችን የግብርና ራማሪዎች እጅ ያለ ቀት በመሆኑ መልሶ ለመንባት የሚስችል ሥርዓት በመፍጠር ተቋማዊ ማድረግ ይቻላል። ለባዮቴክኖሎጂ ጥጥ ዝርያ ለዚሁ የሚያስፈልገውን ማዳበሪያን የተባይ መከላከያ ባለቤት ሆኑት ለም አቀፍ ኩባንያዎች ጋር በጥቅማችን ላይ እንደ ጠንካራ ባለድርሻ አካል ተደራዳሪ በመሆንየምንፈልገውን ለመቀበል የማንፈልገውን ለማለት እንችላለን።

በዚህ ዘርፍ ዕውቀት ያለው ማንኛውም የውጭ ሰው የመልካሳን ግብርና ምርምር ጣቢያ ጎብኝቶ የአገራችን የበቆሎ ሳይንቲስቶች ያዳቀሉዋቸው የተለያዩ የበቆሎ ዝርያዎች እነ (BH611, BH546, BH547) በሚሰጡት ከፍተኛ ምርት፣ ድርቅ፣ ተባይና በሽታ የመቋቋም (Yield Per Hectar, Drought, Stress and Pest and Disease Resistance) ችሎታቸው የዘር ውርስ ይዘቱ ከተለወጠ በቆሎ እንደሚያስንቁና በምንም መለኪያ ቢኬድ ሚዛን እንደሚደሊያረጋግጥ ይችላል። ለዚህም ደግሞ ማመሳከሪያ እንዲሆን ለም አቀፍ የግብርና ምርምርና ልማት ጆርናሎች ላይ ስለነዚህ ዝርያዎች የታተሙ ጥናቶችን መመርመር ይቻላል (Tsedeke Abate (PhD). Homegrown Africa. Ethiopia. 2020)።

በቆሎንም ሆነ እንሰትን በተመለከተ በአገራችን የተራውን ድንቅ ራና ከዚህም ስኬታማ ጀርባ ላሉት የአገራችንን ልጆች ልፋት ውቅና በመስጠት ላይ የተመረተ ግምገማ በማድረግከውጭ የጎደለውን ለመሙላት እንሄዳለን እንጂ ብዙ ያልተመለሱ ጥያቄዎች ያሉበትን ልውጥ በቆሎና ገና በቂ ውቀትና መረጃ ወደ ሌለን እንሰት ጭምር በማለፍእነዚህ የምግብ ዋስትና አዝርዕቶች ውርሳቸው በተለወጡ (Transgenic) በሆኑ ቆሎና እንሰት ለመተካት የአገሪቱን በምክር ቤት አንዲሻሻል መቻኮል የከፋ ችግር ውስጥ ሊከተን ይችላል። በአንድ የምክክር መድረክ በአገራችንና በለም አቀፍ ደረጃ ብቸኞቹ የእንሰት ተመራማሪዎች የ65 ሚዮን ዝብ የምግብ ዋስትና የሆነን አገር በቀል ዝርያ ያጋጠውን የምርታማነትና የበሽታ መቋቋም ችግር ለመፍታት በባዮቴክኖሎጂ እንሰት ለመተካት መሞከርበተፈጥሮ ሥነ ምዳር ላይ ጦርነት እንደማወጅ ይቆጠራል እስከ ማለት መድረሳቸውን አዚህ ላይ ማስታወስ እወዳለሁ። 

ምክረ ሳብ 

1 የአገራችን ምክር ቤት ግ ማሻሻያ እንዲያደርግበት የተፈለገው አሁን በቅድሚያ የባዮቴክኖሎጂ ጥጥ በሰፊው እንዲስፋፋ ነው። ከዚያ ቀጥሎ ለአገራችን የምግብ ዋስትና ወሳኝ የሆኑትን እነ በቆሎና እን የመሳሰሉት ባለ ተራ ሆነው ተቀምጠዋል። የሌሎች አገሮች ልምድ የሚነግረን የዘር ውርስ ይዘታቸው የተለወጡ (Genetically Modified) እንደ ጥጥና በቆሎ የመሳሰሉት ለም መሬትን ምድረ በማድረግና የግብርናውን ሥነ ዳር ለበሽታ በማጋለጥበአርሶ አደሮችም ሆነ በመንግሥታት ላይ ኪሳራ ማድረሳቸውን ነው። ይዋል ይደር እንጂ በአገራችንም መከሰቱ አይቀርም። ይህ አደጋ ከመከሰቱ በፊት በጠቅላይ ኒስትር ዓብይ የሚመራው መንግሥትና በግብርናው መስክ ከፍተኛ ላፊነት ላይ የተቀመጡበግብርና ምርምሩ ሊደመጡ የሚገባቸውን ባለድርሻ አካላት ምክር መስማት ተገቢ ነው። ስለዚህም ይህንን አሳሳቢ ጉዳይ ፖለቲካዊ ከማድረግ ተጠንቅቀንባዮቴክኖሎጂ ሊያስገኝልን ለሚችለው ትና ዕድገት ክፍት ሆነንና በዚሁ የምርምር ውጤት ላይ የተመረተ ምክር ማቅረብ የሚችሉት እንዲደመጡ ማድረግ የመንግሥት ላፊነት ነው። 

2 ገንዘቡንና የዘር ውርስ ይዘታቸው የተለወጡትን አዝርዕት ይዘውልን ከውጭ የገቡት ወገኖች ለአገራችን ግብርና ነቀል መፍት እነርሱ እጅ ያለ የሚያስመስለው፣ ግልነትም ሆነ ሚዛናዊነት የጎደለው አካሄድ የከፋ ጉዳት እንደሚያስከትል በማየት በቶሎ መታረም ይኖርበታል። አገር በቀል ዝርያዎችን ብዝነት እንዳይሸረሸሩጥብቀንና ሥርዓት አበጅተን የዘር ውርስ ይዘታቸው የተለወጡትን አዝርዕት ጋር አቻችለንም እንሂድ ብንል ምርጫው በበቂ የተመከረበት የራሳችን ውሳኔ መሆነ አለበት። አቻችሎ የመዱንም አማራጭ እንከተል ካልን ኬንያ ምን ያህል እንደተሳካላት እንመርምር፡፡ የዚህች ጎረቤት አገር ልምድ ጠቃሚ ከመሰለን ለአገራችን እንዲመች አድርገን ለመቅረፅ ብቃቱ ያላቸው የግብርና ምርምር፣ ባዮቴክኖጂ፣ ባዮሴፍቲና የኤክስቴንሽን ሰርቪስ አዋቂዎች ሊያግዙ ይችላሉ። 

3 በያዝነው እ.ኤ.አ 2020 ማለትም የኮሮና ወረርሽኝ በአገራችን ከመግባቱ ቀደም ብሎ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብ ድርጅት ይፋ ባደረው ሪፖርት፣ እ.ኤ.አ. በ2019 ከለም እጅግ የከፋ የምግብ ዋስትና ችግር ያለባቸው ተብለው ከተዘረዘሩት አሥር አገሮች መካከል አገራችን ኢትዮጵያ አንዷ ሆና ተመዝግባለች (202093 እስከ 96)። ከ70 በመቶ በላይ በገጠር የሚኖረው ዝብ ለበርካታ ይነት የድህነት መለኪያዎች (Multidimensional Poverty Index) የተጋለጠ ሲሆን በተደጋጋሚ በሚከሰት ድርቅ ለዘር ያስቀመጠውን በልቶ የጨረሰ፣ አርሶም ሆነ አርብቶ ለማደር የቋጠረው ቅርስ የወደመበትና የተሻለ አየር ንብረት ለውጥ እንኳን ቢያጋጥም ከተረጂነት ተላቆና አገግሞ በቶሎ አምራች ለመሆን የማይችል እንደሆነ በሌላም ተጨማሪ ጥናት ተዘክሯል (OPHI, September 2019)።  ይህ ልንጋፈጠው የሚገባ እውነታ ፊታችን ላይ ተደቅኖ ትኩርታችን የዘር ውርስ ይዘታቸው የተለወጡ አዝርዕ ላይ? ወይስ ችግር የማይፈታው (Resilient) አገር በቀል የምግብ አቅርቦት ሰንሰለታዊ ርዓት (Domestic Agri-Food System and Sutainable Supply Chain) መገንባት?

4 በዚህ ድንገተኛና አስቸጋሪ የኮሮና ወረርሽኝ ወቅት የግብርና ምርምርና ኤክስቴንን አገልግሎት ትኩት መጠትና ተደሽም መሆን አለበት የምለው በገጠርም በከተማም የተረሱ፣ የተገፉና የተፈናቀሉ፣ የምግብ ጦት በሚያስክትለው የጤና እክል በቀላሉ ለሚተላለፍና ፅኑ ለሆነ ተላላፊ በሽታና የተመጣጠነ ምግብ ጦት (Malnutrition) የተጋለጡት ላይ ነው። እነ ከላይ የጠቀስኳቸውን ዜጎች ከመጀመያውም የረጅም ዘመን ረሃብተኞች ናቸው። ቀደም ሲል ከፍተኛ ልሚ ንጥረ ነገሮች እጥረት የተጋለጡ በመሆናቸው ከኮሮና ወረርሽኝ በፊት ወደ ጤና ጣቢያዎች በመሄድ አስፈላጊውን ክትትል ለማግኘት ዕድል ያላገኙ ናቸው። በዚህ በኮሮናና ድህረ ኮወቅት ወንዶችም ሴቶችም እኩል ተጠቂ ቢሆኑም ለተደራረበ ጥቃት የሚጋለጡት ሴቶች፣ ፃናት፣ በእርግዝና ላይ ያሉ ወይም የሚያጠቡ ደሃ እናቶችና አቅመ ደካማ አዛውንቶች ስለሆኑ መንግትና ሌሎችም ባለ ድርሻ አካላት ያለውን ትና ግብዓት የእነህን ዜጎች ቸኳይ የምግብና ጤና ዋስትና ማረጋገጥ ላይ በማዋል በዚህ ላይ የሚገኘው አመርቂ ውጤት ዘለቄታዊ መሆኑ በጥናት ሲረጋገጥትኩታችንን የዘር ውርስ ይዘታቸው የተለወጡ አዝርዕት ላይ ለምንሸጋገርበት ወይም ሁለቱንም አቻችለን ለመሄድ ዘለቄታው የሚያስተማምን ሥርዓት ከመገንት የሚከለክለን የለም። ስለዚህም ቅድሚያው ችግር የማይፈታው አገር በቀል የምግብ አቅርቦት ሰንሰለታዊ ርዓ የመገንባቱ ስትራቴጂካይታ የዘር ውርስ ይዘታቸውበመለወጥ የበለጠ ተጠቃሚነትን ያስገኛሉ የሚባሉትንም አዝርዕችም በዚሁ ውስጥ ተገቢ ቦታቸውን እንዲይዙ ማድረግ ይችላል። 

መደምደሚያ

በአገራችን የምንፈልጋቸውንና መስማት የምንፈልገውን የሚናገሩልንን የማዳመጥሌሎችን መስማት የማንፈልገውን የሚነግሩንን የማግለል በሽታ ከላይ እስከ ታች እንዳለ የታወቀ ነው። አዲስ ሰዎችን ማለትም የማናውቃቸውንና የማያውቁንን፣ የጋችግራንንም ቢሆን ጠንቅቀው የማያውቁና ልምዱ ሌላቸውን በወረት ማስጠጋትና ዕድል መስጠት፣ የሚያውቁንና የምናውቃቸውን የጋራ ችግራችንን ጠንቅቀው የሚያውቁትን እንጀራችንና የተጠቀምንበትን የሥልጣን ወንበር ያሳጡን ይመስል እንዳናዳምጣቸውና እንዳይደመጡ ዕድሉን መከልከል ልንገላገለው ያልልን አሳዛኝ ልማድ ነው። ተወደደም ተጠላ የግብርናውን ሥነ ምዳር የአጭርም ሆነ የረጅም ጊዜ ችግር ለመፍታት የግድ በለም አቀፍ ደረጃ የተከበሩና ምርጥ የግብርና ዝርያዎችን ተፈጥሯዊ ይዘት በመጠበቅ ምርታማነትን፣ በሽታን፣ ውርጭን ድርቅንና፣ ለጤና አስፈላጊ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን አብሮ በማዳቀልና በባዮቴክኖሎጂው ዘርፍ ምጉን በማከናወን ስመ የሆኑትን የአገራችንን የግብርና ምርምር ሊቀ ሊቃውንትየምክክር ሳብ ከመቀበል በስተቀር ሌላ አማራጭ ሊኖረን አይገባም።

ሁለቱን አማራጮች አቻችለንም ሆነ ሳናቻችል በየትኛው አቅጣጫ እንድንሄድ መምከር የሚችሉት እነርሱ ብቻ እንጂ የዘር ውርስ ይዘታቸው የተለወጡ አዝርዕትንም ማዳበሪያውንም፣ የተባይ መድኒት መከላከያውን በሞኖፖል የሚያመርቱትና የሚያከፋፍሉት በውጭ ያሉ የለም አቀፍ ኩባንያዎችና ቀስቃሾቻቸው አይደሉም። ስለዚህም የእነርሱ ምክር ለማዳመጥ ዜጎች ጫና ማድረግ አስተያየት ከአገራዊ ምርጫም ሆነ ሌላ ፖለቲካዊ ጉዳይ ያላነሰ አንገብጋቢ ነው። መንግሥት በአጣዳፊ መድረኩን በማመቻቸት በዚህ ጉዳይ ላይ አስፈላጊውን ምክክር ለማድረግ ፈቃደኛ በመሆንየግብርናው ሥነ ዳር ተመልሶ ማገገም የማይችልበት ውደመት ላይ እንዳይደርስ የትውልድ አደራና ላፊነት አለበት። ስለዚህም ይህንን አሳሳጉዳይ ፖለቲካዊ ከማድረግ ተጠንቅቀን ባዮቴክኖሎጂ ሊያስገኝልን ለሚችለው ትና ዕድገት ክፍት ሆነን በዚየምርምር ውጤት ላይ የተመረተ ምክር ማቅረብ የሚችሉት እንዲደመጡ ማድረግ የመንግሥት ላፊነት ነው። 

ከአዘጋጁ፡- ጸሐፊው በሲዬር ሶሻል ሳይንቲስት ደረጃ የቀድሞ ለም አቀፍ ግብርናና ልማት ድርጅት ተመራማሪ የነበሩ ሲሆኑ፣ ጽሑፉ የእሳቸውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ መሆኑን እየገለጽን በኢሜይል አድራሻቸው [email protected] ወይም  [email protected] ማግኘት ይቻላል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...