የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ አበበ አበባየሁ ከኃላፊነታቸው ለቀቁ።
ላለፉት ሁለት ዓመታት ገደማ በኮሚሽነርነት ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ አበበ በራሳቸው የግል ምክንያት ከኃላፊነት ለመልቀቅ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ጥያቄ አቅርበው ውሳኔ ሲጠባበቁ ነበር።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ አበበ ያቀረቡትን የመልቀቂያ ጥያቄ ሰሞኑን እንደተቀበሉት ሪፖርተር ከታማኝ ምንጮቹ ለማረጋገጥ ችሏል።
በአቶ አበበ ምትክ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው በማገልገል ላይ የሚገኙት ሌሊሴ ነሜ እንደሚተኩ የሪፖርተር ምንጮች ጠቁመዋል።