Saturday, December 3, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናየኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ዋና ሥራ አስፈጻሚ የኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ

  የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ዋና ሥራ አስፈጻሚ የኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ

  ቀን:

  የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው በማገልገል ላይ የነበሩት ወ/ሪት ሌሊሴ ነሜ፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾሙ።

  ወ/ሪት ሌሊሲ ወደ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የተዘዋወሩት የኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ሆነው ላለፉት ሁለት ዓመት ገደማ ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ አበበ አበባየሁ፣ በራሳቸው ፈቃድ ከኃላፊነታቸው በመልቀቃቸው ነው።

  የኢንቨስትመንት ኮሚሽነር በመሆን የተሾሙት ወ/ሪት ሌሊሴ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ለሁለት ዓመት ገደማ ያገለገሉ ሲሆን፣ ከዚያ አስቀድሞ በኦሮሚያ ክልል የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኃላፊ ሆነው ሠርተዋል።

  የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር በመሆን ላለፋት ዓመታት ያገለገሉት አቶ አበበ፣ ከዚያ አስቀድሞ በጠቅላይ ሚኒስትር በአማካሪት ሠርተዋል፡፡ በጥቅሉ ለአምስት ዓመታት በተለያዩ የመንግሥት ኃላፊነቶች ላይ ሲያገለግሉ ቆይተዋል። ሪፖርተር ያነጋገራቸው አቶ አበበ በፈቃዳቸው ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት ኃላፊነታቸውን እንደለቀቁ ገልጸው፣ ከማክሰኞ ሰኔ 16 ቀን 2012 ዓ.ም. አንስቶም መልቀቂያቸው ተቀባይነት አግኘኝቶ መሰናበታቸውን ገልጸዋል። አቶ አበበ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይም ከኃላፊነት መልቀቃቸውን የገለጹ ሲሆን፣ ቀጣይ የሥራ ሕይወታቸው ከመንግሥት ኃላፊነት ውጪ እንደሚሆንም አስታውቀዋል።

  ከነበሩበት ኃላፊነት በፈቃዳቸው ሲለቁም በተለያዩ የመንግሥት ኃላፊነቶች አገራቸውን እንዲያገለግሉ ለፈቀዱላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ከፍተኛ ምሥጋናቸውን ገልጸው፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩን እምነት በማግኘታቸውና በኃላፊነት ቆይታቸው ወቅትም ለነበራቸው ወንድማዊነትና ያልተቆጠበ ድጋፍም አመሥግነዋል።

   አቶ አበበ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ በመሆን የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ያገኙ ሲሆን፣ የሁለተኛ ዲግሪያቸውን ከደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ በዓለም አቀፍ ንግድና ኢንቨስትመንት ሕግ አግኝተዋል። በተጨማሪም ከብሪታንያ ደንዲ ዩኒቨርሲቲ በኢነርጂ ሕግና ፖሊሲ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል።

  የኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ሆነው የተተኩት ወ/ሪት ሌሊሴ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ከፍተኛ አመራሮች መካከል በዕድሜ በጣም ወጣቷ ናቸው። ወ/ሪት ሌሊሴ በሲቪል ምሕንድስና የመጀመርያ ዲግሪያቸውን ያገኙ ሲሆን፣ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በቢዝነስ አስተዳደር አግኝተዋል።

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...