Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበኢትዮጵያ ላይ የተቃጣውን የሳይበር ጥቃት ማክሸፉን መንግሥት ገለጸ

በኢትዮጵያ ላይ የተቃጣውን የሳይበር ጥቃት ማክሸፉን መንግሥት ገለጸ

ቀን:

ጥቃቱ ከተፈጸመባቸው መካከል ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ይገኝበታል

ግብፅ በህዳሴ ግድብና በአጠቃላይ የዓባይ ውኃ ላይ ያላትን ጥቅም አስከብራለሁ የሚል ቡድን በኢትዮጵያ የመንግሥትና የግል ተቋማት ላይ ፈጽሞት የነበረውን የሳይበር ጥቃት ማክሸፉን፣ የመረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) አስታወቀ።

ሰኔ 15 ቀን 2012 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች፣ በ13 የመንግሥትና በአራት መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት ድረ ገጾች ላይ መፈጸማቸውን ኢንሳ አስታውቋል። ጥቃቶቹ በዋናነት የተፈጸሙት ከዓርብ ሰኔ 12 ዓ.ም. ጀምሮ እንደነበር የገለጸው ኢንሳ፣ የጥቃት ሙከራው ያነጣጠረው በአገሪቱ የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ የደኅንነት መሥሪያ ቤቶችና የግል ድርጅቶች ላይ እንደነበር አስታውቋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የሳይበር ጥቃት ሙከራው የተቃጣው ሳይበር ሆረስ ግሩፕ (Cyber Horus Group)፣ አኑቢስ ዶት ሃከር (AnuBis Hacker) እና ሴኪዩሪቲ ባይ ፓስ (Security By Pass) በተባሉ የሳይበር አጥቂዎች አማካይነት መሆኑን ኢንሳ ጨምሮ ገልጿል፡፡

የሳይበር ጥቃቱን ፈጽመዋል ከተባሉት ቡድንኖች መካከል፣ ሳይበር ሆረስ ግሩፕ (Cyber Horus Group) የተባለው ጥቃቱን በኢትዮጵያ የመንግሥት ተቋማት ላይ መፈጸሙን አል መስሪ አል ዩም በተባለ የዓረብ ሚዲያ ሰኔ 13 ቀን 2012 ዓ.ም. በይፋ አስታውቆ ነበር።

ሳይበር ሆረስ ግሩፕ፣ አኑቢስ ዶት ሃከርና ሴኪዩሪቲ ባይ ፓስ በማለት ራሳቸውን የሚጠሩት ሦስቱ የሳይበር ጥቃት አድራሽ ቡድኖች ስለፈጸሙት ጥቃት ኃላፊነቱን እንደወሰዱ፣ ኢንሳ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ዋና ዓላማቸውም በህዳሴው ግድብ ላይ በተለይም ከግድቡ ውኃ አሞላል ጋር በተያያዘ ሁሉን አቀፍ ተፅዕኖ በአገሪቱ ላይ ለመፍጠር መሆኑን ቡድኖቹ ራሳቸው መግለጻቸውን ከኢንሳ መግለጫ ለመረዳት ተችሏል፡፡

የሳይበር ጥቃት የተሰነዘረባቸው ተቋማት አብዛኞቹ በድረ ገጽ ግንባታ ሒደት ደኅንነታቸውን ታሳቢ ያላደረጉ፣ እንዲሁም የደኅንነት ፍተሻ ያላደረጉና ከፍተኛ የሳይበር ደኅንነት ተጋላጭነት የነበረባቸው እንደሆኑ ኢንሳ ማረጋገጡን ገልጿል፡፡

ኢንሳ አስቀድሞ ቅድመ ዝግጅት በማድረጉ ምክንያት ይህን መጠነ ሰፊ የሳይበር ጥቃት መከላከል ባይችል ኖሮ ጥቃቱ በአገሪቱ ላይ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖሊቲካዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት ሊያስከትል ይችል እንደነበር አስታውቋል፡፡ በመከላከሉም ሊደርሱ የሚችሉ ከፍተኛ አደጋዎችን ማስወገድ መቻሉንና ይኼንንም ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥልበት አረጋግጧል፡፡

ወደፊት መሰል ጥቃቶች በስፋት፣ በረቀቀ መንገድና ከተለያዩ ሥፍራዎች ሊሰነዘር እንደሚችል ግምት ውስጥ በማስገባት ግለሰቦችም ሆኑ ተቋማት “.et domain” ከመጠቀማቸው በፊት የድረ ገጻቸውን ደኅንነት አረጋግጠው እንዲጠቀሙ፣ ራሳቸውን ከሳይበር ደኅንነት ተጋላጭነት ለመከላከል አስፈላጊዎቹን የጥንቃቄ ዕርምጃዎች መውሰድ እንደሚኖርባቸው አሳስቧል።

ተቋማት ከኢንሳ ጋር በመተባበር የደኅንነት ተጋላጭነታቸውን መድፈን እንዳለባችው፣ የተለያዩ የሳይበር ደኅንነት ጥቃት ሙከራዎች ሲያጋጥሟቸውም ሆነ ሙያዊ ድጋፍ ሲያሻቸው ለኢንሳ በማሳወቅ አስፈላጊውን ትብብርና ድጋፍ ማግኘት እንደሚችሉም አስታውቋል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...