Tuesday, April 16, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህል ቀለበታዊው የፀሐይ ግርዶሽ

 ቀለበታዊው የፀሐይ ግርዶሽ

ቀን:

‹‹በዕለተ ረቡዕ ባንድ ላይ ተፈጥራ፣

ብርሃን ከፀሓይ ወስዳ ማታ ምታበራ፣

የሥነ ተፈጥሮን ቃል ኪዳን አክባሪ፣

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ያስገኝዋን ውበት ጥበብን ተማሪ፣

ጨረቃ ባል ሆነች ለፀሐይ ቃል ገባች

ሙቀቴ ድምቀቴ ብርሃኔነሽ አለች፤

በምግባር ተጋርዳ ለውቢቱ ፀሐይ ቀለበት አሰረች፡፡››

በዕለተ እሑድ ሰኔ 14 ቀን 2012 ዓ.ም. ንጋት ላይ ቀለበታዊ የፀሐይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ ተከሰተ፡፡ ከኮንጎ፣ መካከለኛው አፍሪካ በሱዳን አድርጎ በኢትዮጵያ ያለፈው ግርዶሹ ላሊበላ ከተማ በተገለጠበት ወቅት ነበር የሀብከ ጥላሁን ‹‹ጨረቃ ባል ሆነች›› በሚል ርዕስ ስንኞችን ያሰረው፡፡

በኢትዮጵያ ከምዕራብ እስከ ሰሜን ምሥራቅ የታየው ባለቀለበት ቅርፅ የፀሐይ ግርዶሽ፣ በወለጋ፣ በከፊል ጎጃም፣ ጎንደር፣ ወሎና ደቡብ ትግራይ ተከስቷል፡፡

ቀለበታዊ ግርዶሽ ማየት የቻሉት ከተሞች መካከል ቤጊ፣ ሜቲ፣ መንዲ፣ ቡሬ፣ አገው ግምጃ ቤት፣ እንጅባራ፣ ግሽ ዓባይ፣ ሞጣ፣ ዳሞት፣ ጋይንት፣ ንፋስ መውጫ፣ ጋሸና፣ ሙጃ፣ ዋጃ፣ ቆቦ፣ ኮረም፣ አላማጣ፣ ጊራራ እና ላሊበላ ይገኙበታል፡፡

አዲስ አበባ፣ ሐዋሳ፣ ድሬዳዋ፣ መቐለ፣ ደሴ፣ አዳማየመሳሰሉት ከተሞች ያጋጠማቸው ከፊል የፀሐይ ግርዶሽ ነው፡፡

ግርዶሹ የሚፈጠረው ጨረቃ በፀሐይና በምድር መካከል ስትሆንና  ፀሐይ ሙሉ በሙሉ ተጋርዳ ብርሃን መስጠት ሳትችል በሚፈጠር ክስተት ነው፡፡ በሁለቱ መካከል ተጣጥማ በምትታይበት ወቅት በፀሐይ ዙርያ ሆና ቀለበታዊ ቅርፅ ታሳያለች፡፡

በላሊበላ ከተማ የሚታየውን ግርዶሽ ለማየት ዓለም አቀፍ ተመራማሪዎችና ቱሪስቶች በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ባይመጡም፣ የመንግሥት ሹማምንትና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተው ክስተቱን ተመልክተዋል፡፡

ጨረቃ ፀሐይን ሙሉ በሙሉ ስላልዘጋች በዙሪያው የሚያበራ የፀሐይ ብርሃን አስደናቂየእሳት ቀለበት”ን ፈጥሮ የታየ ሲሆን በላሊበላ ከተማ ድቅድቅ ጨለማ ይፈጠራል ተብሎ ቢጠበቅም አልሆነም፡፡  ፈለካዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ ጨረቃ ሙሉ በሙሉ ፀሐይን የምትጋርደው እ.ኤ.አ. 2020 ማብቂያ አካባቢደቡብ አሜሪካ ይሆናል፡፡

ግርዶሹ በአፍሪካ፣ በመካከለኛው ምሥራቅና በእስያ ሲያልፍ በተለያዩ አገሮች የሚገኙ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የቀጥታ ሥርጭት ሽፋን ሰጥተውታል፡፡ በኢትዮጵያ ከአላማጣ ከተማ ክስተቱን እየተከታለለ ካሠራጨው የትግራይ ቴሌቪዥን በስተቀር፣ አገራዊው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (ኢቲቪ) እና ሌሎች ጣቢያዎች አለማሠራጨታቸው ለምን ያሉ ቁጥራቸው ጥቂት አይደለም፡፡ ኢቲቪና የአማራ ቲቪ በተወሰነ መልኩ ከትግራዩ ጣቢያ ወስደው ማሳየታቸው አልቀረም፡፡

በሰሜን ዋልታ የተከሰተው ግጥምጥም

በሰሜናዊ ንፍቀ ክበብ ፀሐይ ከምድር ወገብ በጣም ከምትርቅበት  ቀናት አንዱ ጁን 21 ቀን 2020 (ሰኔ 14 ቀን 2012) ሲውል የዓመቱ ፀሐይ ረዥም ሰዓት የሚታይበት ቀን ይሆናል፡፡ ይህም በሰሜናዊ ንፍቀ ክበብ ባሉ አገሮች የበጋ ወቅት መጀመርያ ነው፡፡ ይህ የቀኑ ብርሃን 18 ሰዓታት በላይ የሚዘልቅበትን የፀሐይ ክስተትሰመር ሶልስቲስ” በግእዙ “ዕቱተ ዮን” (ፀሐይ ከምድር ወገብ የምትርቅበትበጋ ወቅት) ይሉታል፡፡ ዕለቱንም የተለያዩ የአውሮፓ አገሮች እንደየባህላቸው ያከብሩታል፡፡

የዘንድሮ አከባበር ግን እንደሁሌው ብቻ ሳይሆን በዕለቱ ከተከሰተው ቀለበታዊ የፀሐይ ግርዶሽ ጋር ተገጣጥሞላቸው አክብረውታል፡፡ ይህም በሰሜናዊ ንፍቀ ክበብ ባሉ አገሮች የበጋ ወቅት መጀመርያ ሲሆን፣ ከምድር ወገብ በሚገኙ አገሮች ከኢትዮጵያ በቀር የክረምት ወቅት የሚጀምርበት ነው፡፡ በኢትዮጵያ ባሕረ ሐሳብ መሠረት ግን ክረምት በይፋ የሚገባውና ወቅቱን ከፀደይ የሚረከበው ሰኔ 26 ቀን ነው፡፡

ግርዶሹ ወደ ደቡብ ሱዳን፣ ኢትዮጵያና ኤርትራ ከመሻገሩ በፊት የተነሳው ከኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ነው፡፡ በቀይ ባሀር በኩል ወደ የመን፣ ፓኪስታን፣ ሰሜናዊ ህንድ፣ ቻይናና ታይዋንን አቋርጦ በፓስፊክ ውቅያኖስ አክትሟል፡፡

የቀለበታዊ ግርዶሽ አጠቃላይ ጉዞውመሬት፣ ጨረቃና ፀሐይ ኅብር በፈጠሩበት ጁን 21 ቀን- ከምዕራብ ወደ ምሥራቅ 12 አገሮችን አካልሏል፡፡ በደቡብ ምሥራቅ እስያ በመጥፎ የአየር ሁኔታ ማየት የተቸገሩ ቢሆንም በሌሎች በርካታ አገሮች ውስጥ በከፊል ግርዶሽ መታየቱ ተዘግቧል፡፡

በሰሜን ዋልታ የተገጣጠሙት ሁለቱ ክስተቶች ዳግም ዕውን የሚሆኑት ከ19 ዓመት በኋላ ነው፡፡

የአፍሪካ የሥነ ፈለክ ማኅበር፣ ስለ ቀለበታዊ ግርዶሽና በተያያዥ ጉዳዮች ዙርያ ግንዛቤን የሚፈጥሩ ፖስተሮችና የተለያዩ ኅትመቶች ከማዘጋጀቱ ባለፈ ነፃ የአንድሮይድ መተግበሪያንም አማርኛን ጨምሮ በተለያዩ ቋንቋዎች አዘጋጅቶ ማሠራጨቱ ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም...

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...