Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምየስደተኞች ቀን ሲታሰብ

የስደተኞች ቀን ሲታሰብ

ቀን:

በተለያዩ የዓለም አገሮች የሚፈጸም ጥቃት፣ ግድያ፣ ግጭትና ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚመጣው የሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሕዝቦች ከቀዬአቸው እንዲፈናቀሉ አድርጓል፡፡

እ.ኤ.አ. እስከ 2019 በዓለም 80 ሚሊዮን ያህል ሕዝቦች ተፈናቅለዋል፡፡ ከእነዚህ ስደተኞች 40 በመቶ ያህሉ ሕፃናት መሆናቸውንና በ2019 ብቻ ከ11 ሚሊዮን የሚበልጡ ሰዎች ከአገራቸው መሰደዳቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን (ዩኤንኤችሲአር) በሪፖርቱ አመላክቷል፡፡

በየዓመቱ ሰኔ 13 ቀን የሚከበረውን የዓለም የስደተኞች ቀን አስመልክቶ ዩኤንኤችሲአር የለቀቀው ሪፖርት እንደሚያሳየው፣ በ2019 የተመዘገበው የስደተኞች ቁጥር ከአሥር ዓመት በፊት ከተመዘገበው እጥፍ ነው፡፡

በዓለም ከተፈናቀሉት 80 ሚሊዮን ያህል ሰዎች 26 ሚሊዮኑ ስደተኛ ሲሆኑ፣ 4.2 ሚሊዮኑ ደግሞ የፖለቲካ ጥገኝነት የጠየቁ ናቸው፡፡ 45.7 ሚሊዮን በአገራቸው ሆነው ከቀዬአቸው የተፈናቀሉ መሆናቸውን ሪፖርቱ ያሳያል፡፡

ሰዎች ከቀዬአቸው በኃይል የሚፈናቀሉበት ሁኔታ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ አሁን ላይ በስፋት ከመስተዋሉም ባለፈ መደበኛ ሆኗል፡፡ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ሳህል አካባቢ፣ በጦርነት የላሸቁት የመንና ሶሪያ በዓለም ዜጎቻቸው ከሚፈናቀሉባቸው ቀዳሚ ስድስት አገሮች ውስጥ ይመደባሉ፡፡

የስደተኞች ቀን ሲታሰብ

 

 የሶሪያ፣ የቬንዙዌላ፣ የአፍጋኒስታን፣ የደቡብ ሱዳንና የማይናማር ዜጎች በዓለም ከተመዘገቡ ስደተኞች ሁለት ሦስተኛውን ይይዛሉ፡፡

ቱርክ ደግሞ በዓለም ከፍተኛውን የስደተኛ ቁጥር ከያዙ አገሮች በቀዳሚነት ስትገኝ፣ ከሶሪያ ብቻ የተሰደዱ 3.9 ሚሊዮን ሕዝቦችን አስጠልላ ትገኛለች፡፡

በማደግ ላይ ያሉ አገሮች የስደተኛ ጫና የበዛባቸው ናቸው፡፡ በ2019 ከተመዘገቡት 80 ሚሊዮን ስደተኞች 85 በመቶ ያህሉ የሚገኙት በማደግ ላይ ባሉ አገሮች ነው፡፡ ደሃ አገሮች ደግሞ 27 በመቶ ለሚሆኑ የፖለቲካ ጥገኝነት ጠያቂዎች አዎንታን ችረዋል፡፡

73 በመቶ ስደተኞች በጎረቤት አገር የተጠለሉ ናቸው፡፡ 68 በመቶ ስደተኞች ከዓለም አገሮች የተሰደዱ ሲሆን፣ ከሶሪያ 6.6 ሚሊዮን፣ ከቬንዙዌላ 3.7 ሚሊዮን፣ ከአፍጋኒስታን 2.7 ሚሊዮን፣ ከደቡብ ሱዳን 2.2 ሚሊዮን እንዲሁም ከማይናማር 1.1 ሚሊዮን ዜጎቻቸው በጦርነት፣ በግጭት፣ በጥቃትና ሞትን በመሸሽ ተሰደዋል፡፡

ቱርክ 3.6 ሚሊዮን ዜጎችን በማስጠለል ቀዳሚ የስደተኛ ተቀባይ አገር ስትሆን፣ ኮሎምቢያ 1.8 ሚሊዮን፣ ፓኪታን 1.4 ሚሊዮን፣ ኡጋንዳ 1.4 ሚሊዮን እንዲሁም ጀርመን 1.1 ሚሊዮን ስደተኞችን አስጠልለዋል፡፡

ወደቀያቸው የተመለሱትን ጨምሮ ባለፉት አሥር ዓመታት 100 ሚሊዮን ያህል ሰዎች ተሰደዋል፣ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል፡፡ በሶሪያ የተከሰተው ግጭት፣ የደቡብ ሱዳን የነፃነት ጥያቄ፣ በዩክሬን ያለው ሰላም ዕጦት፣ ወደ አውሮፓ የሚጎርፉ ስደተኞች መጨመር፣ ከማይናማር ወደ ባንግላዴሽ የሚጎርፉ ስደተኞች፣ ከካሪቢያንና ላቲን አሜሪካ የቬንዙዌላውያን መጉረፍ፣ በሳህል ቀጣና ያለው ግጭት፣ የአየር ንብረት በአፍጋኒስታን፣ በኢራቅ፣ በሊቢያ፣ በሶማሊያ፣ በማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ ያለው ግጭት፣ በኢትዮጵያ ያለው የውስጥ መፈናቀል፣ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎና በየመን ያለው መፈናቀል ባለፉት አሥር ዓመታት በዓለም ለተመዘገበው የስደተኞች ቁጥር መባባስ ተጠቃሽ ናቸው፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ ከዓመት ዓመት እየጨመረ የመጣው ስደትና የውስጥ መፈናቀል፣ ለአገሮችም ሆነ ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ከፍተኛ ጫናን ፈጥሯል፡፡ ቀድሞውንም የጤና፣ የመሠረተ ልማትና የሌሎችም አገልግሎቶች ችግር ባሉባቸው የስደተኛ ካምፖች፣ ከ2019 ማብቂያ ጀምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሌላ ሥጋት ሆኗል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት እንደሚለውም፣ ኮሮና ቫይረስ ከአገሩ የተሰደደውን፣  እዚያው በአገሩ ለተፈናቀለውና ስደተኛ ተቀባይ አገሮች ከፍተኛ ችግር እየፈጠረ ነው፡፡ የጤና አገልግሎት አለመሟላት፣ ገቢ አለመኖርና ለፆታዊ ጥቃት መጋለጥም ስደተኞችን ይበልጥ ለቫይረሱ ተጋላጭ እያደረገ ነው፡፡

ቫይረሱ ስደተኞችና ስደተኞችን አስጠልለው የሚኖሩ አገሮች ላይ ጫና መፍጠሩን ዩኤንኤችሲአር አስታውቆ፣ ኮቪድ-19 ከመከሰቱ በፊት መሠረታዊ ፍላጎታቸው የማይሟላላቸው ስደተኞች 15 በመቶ እንደነበሩና አሁን ላይ ወደ 70 በመቶ ማደጋቸውን አክሏል፡፡ 75 በመቶ ስደተኞች ደግሞ መሠረታዊ የጤና አገልግሎት ማግኘት አልቻሉም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...