Friday, December 9, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisement -
  - Advertisement -
  ዜናየእነ ጄኔራል ሰዓረ መኮንን የፍርድ ቤት ክርክር ሒደት እንዲቀጥል ተወሰነ

  የእነ ጄኔራል ሰዓረ መኮንን የፍርድ ቤት ክርክር ሒደት እንዲቀጥል ተወሰነ

  ቀን:

  በመኖሪያ ቤታቸው በጠባቂያቸው ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም. በጥይት ተደብድበው ተገድለዋል የተባሉት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም የእነ ጄኔራል ሰዓረ መኮንን የፍርድ ቤት ክርክር፣ ከሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ በመደበኛ ፍርድ ቤት እንዲካሄድ ሰኔ 17 ቀን 2012 ዓ.ም. ተወሰነ፡፡

  በኅዳር ወር 2012 ዓ.ም. በፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በ13 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ ተመሥርቶ፣ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የፀረ ሽብርና በሕገ መንግሥት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ችሎት ክርክሩ ቀጥሎ የነበረና ዓቃቤ ሕግ ምስክሮቹን እንዲያሰማ ብይን ተሰጥቶ እያለ የኮሮና ወረርሽኝ መጋቢት 4 ቀን 2012 ዓ.ም. በኢትዮጵያ በመግባቱ፣ ፍርድ ቤቶች በከፊል ዝግ በመደረጋቸው ምስክሮች ሳይሰሙ ቀርተው ነበር፡፡

  ጄኔራል ሰዓረ መኮንንና ሜጀር ጄኔራል ገዛዒ አበራን በመግደል ወንጀል ከተከሰሱት 13 ተጠርጣሪዎች መካከል፣ አጃቢያቸው የነበረው አሥር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ መኮንን ላይ ለጊዜው ዓቃቤ ሕግ ይፋ ያላደረጋቸው ምስክሮች እንደሚሰሙ ፍርድ ቤቱ አስታውቋል፡፡ ዓቃቤ ሕግ ክስ መሥርቶባቸው ለተወሰኑ ወራት የቀረበባቸውን ክስ በመቃወም ሲከራከሩ የቆዩት አቶ አስጠራው ከበደ፣ አቶ ሲሳይ አልታሰብ፣ አቶ አበበ ፋንታ፣ አቶ አስቻለው ወርቁ፣ አቶ ተሾመ መለስ፣ አቶ ዓለምነህ ሙሌ፣ አቶ ከድር ሰዒድ፣ አቶ በለጠ ካሳ፣ የአብን አመራር አባል አቶ ክርስቲያን ታደለና ሌሎችም ተጠርጣሪዎች ለሕዝብ ጥቅምና የፖለቲካ ምኅዳሩን ለማስፋት በማለት፣ መንግሥት ክሳቸውን በማቋረጥ ከእስር እንዲፈቱ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

  ተከሳሾቹ በተለይ ከኮሮና ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ መንግሥት እንዲፈቱ  ሲያደርግ፣ አሥር አለቃ መሳፍንት በማረሚያ ቤት እንዲቆይ ተደርጎ ነበር፡፡ ዓቃቤ ሕግ  ሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ.ም. ምስክሮቹን በማቅረብ ምስክርነታቸውን በፕላዝማ ታግዞ ክርክር እንደሚያደርጉ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ መስጠቱ አስታውቋል፡፡

  ክርክሩ እንዲደረግ የተወሰነው ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ክርክሩን ለመቀጠል በመጠየቁ፣ ችሎቱ ጥያቄውን ተቀብሎ ከሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ በተከታታይ መስማት እንደሚጀመርና የተጎጂ ቤተሰቦችና ውስን ሚዲያዎች መከታተል እንዲችሉም ተፈቅዷል፡፡

  spot_img
  - Advertisement -

  ይመዝገቡ

  spot_img

  ተዛማጅ ጽሑፎች
  ተዛማጅ

  በኦሮሚያ ክልል የተፈጸመው ጭፍጨፋና ሥጋቱ

  ኦሮሚያ ክልል ከቀውስ አዙሪት መላቀቅ ያቃተው ይመስላል፡፡ ከ200 በላይ...

  እናት ባንክ ካፒታሉን ወደ አምስት ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ወሰነ

  መጠባበቂያን ሳይጨምር የባንኩ የተጣራ ትረፍ 182 ሚሊዮን ብር ሆኗል እናት...

  ቡና ባንክ ዓመታዊ ትርፉን ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ማሻገር ቻለ

  ቡና ባንክ በ2014 የሒሳብ ዓመት ዓመታዊ የትርፍ ምጣኔውን ለመጀመርያ...