Friday, September 29, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየአፍሪካ ኅብረት በህዳሴ ግድብ ድርድር ውዝግብ ላይ ሊወያይ ነው

የአፍሪካ ኅብረት በህዳሴ ግድብ ድርድር ውዝግብ ላይ ሊወያይ ነው

ቀን:

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውዝግብን በተመለከተ የአፍሪካ ኅብረት በቀጣዮቹ ቀናት ሊወያይ መሆኑን የሪፖርተር ምንጮች ገለጹ።

ውይይቱን የጠሩት የወቅቱ የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛ መሆናቸውን የገለጹት ምንጮች፣ ውይይቱንም የአፍሪካ ኅብረት የፀጥታ ምክር ቤት አባል አገሮች ተወካዮች እንደሚታደሙት ለማወቅ ተችሏል።

የውይይቱ ዓላማም በህዳሴ ግድቡ ላይ በኢትዮጵያ፣ በግብፅና በሱዳን መካከል ለተፈጠረው አለመግባባት መፍትሔ ለመፈለግ እንደሆነ፣ ‹‹አፍሪካዊ መፍትሔ ለአፍሪካዊያን ችግሮች›› የአፍሪካ ኅብረት እ.ኤ.አ. ለ2020 ባሰበው መርህ የሚመራ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

ኢትዮጵያም የህዳሴ ግድቡን በተመለከተ ያለው አለመግባባት በአፍሪካ ኅብረት ባስቀመጠው መርህ መፈታት እንዳለበት የምታምን ሲሆን፣ በዚሁ እምነቷ መሠረትም ሰሞኑን ሲካሄድ የነበረው የኢትዮጵያ፣ የግብፅና የሱዳን ድርድር ከመጀመሩ በፊትም ከአውሮፓ ኅብረትና ከአሜሪካ ታዛቢነት ይልቅ አፍሪካዊያን እንዲታዘቡ ለግብፅና ለሱዳን ጥያቄ አቅርባ ነበር።

ድርድሩን ኡጋንዳና ሩዋንዳ እንዲታዘቡ ጥያቄ ብታቀርብም ግብፅ ጥያቄውን ሳትቀበለው መቅረቷን የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ዓርብ ሰኔ 19 ቀን 2012 ዓ.ም. ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሳፊ ፋኪ ጋር ተገናኝተው መክረዋል፡፡ የአፍሪካ ኅብረት በኢትዮጵያ፣ ግብፅና በሱዳን መካከል በህዳሴ ግድቡ ላይ ያለውን አለመግባባት ‹‹አፍሪካዊ መፍትሔ ለአፍሪካዊ ችግሮች›› በሚለው መርህ መሠረት ለመፍታት አቋም መያዙን በትዊተር ገጻቸው ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ዓርብ ማምሻውን በትዊተር ገጻቸው ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን የተለያዩ የቢሮ አመራሮች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል። ውይይቱም ታላቁ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ በኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ መካከል ያለውን ልዩነት ከአፍሪካ በሚመነጭ መፍትሔ ለመፍታት ያለመ እንደነበር ገልጸዋል።

ይህንን አኅጉራዊ ጠቀሜታ ያለው የከፍተኛ አመራሮች ስብሰባ ያስተባበሩት የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበር የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፎሳ እንደሆኑ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ፣ ምሥጋናቸውንም ለፕሬዚዳንቱ አቅርበዋል። ‹‹የፓን አፍሪካዊነት መንፈስ ያለው አኅጉራዊ ተቋማችን ለአፍሪካ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸውን ውይይቶች ለማካሄድ ትክክለኛው ሥፍራ ነው። ታላቁ የህዳሴ ግድብ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የላቀ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትና የጋራ ብልፅግና የሚያገኙበትን ዕድል ይዟል፤›› ሲሉም ተናግረዋል።

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ አምባሳደር ታዬ አፅቀ ሥላሴም በትዊተር ገጻቸው፣ ‹‹ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ›› በሚለው የአፍሪካ ኅብረት መርህ መሠረት በሚደረግ እውነተኛ ድርድር፣ የህዳሴ ግድቡን አለመግባባት ለመፍታት ኢትዮጵያ ቁርጠኛ መሆኗን አስታውቀዋል።

ይህ በአንዲህ እንዳለ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ረዳት ጸሐፊ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩ ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች አሜሪካ በህዳሴ ግድቡ ላይ ያለውን አለመግባባት ለመፍታት በማለት የምታደርገውን ገለልተኛ ያልሆነ ጣልቃ ገብነት እንድታቆም፣ ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በጋራ ባስገቡት ደብዳቤ መጠየቃቸው ተሰምቷል። አሜሪካ አሁን እያሳየች ያለችውን የግብፅ ደጋፊነት ወደ ጎን በማድረግ፣ በገለልተኝነት የሽምግልና ሚናወን እንድትወጣ ጠይቀዋል፡፡ በኢትዮጵያ ላይ ጫና ማድረግ ድርድሩን ያደናቅፈዋል ማለታቸው ታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...