Sunday, March 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትለካፍ አካዴሚ ሥጋት የሆነው ጅምርና የሚኒስትሯ ጉብኝት

ለካፍ አካዴሚ ሥጋት የሆነው ጅምርና የሚኒስትሯ ጉብኝት

ቀን:

በአዲስ አበባ ሲኤምሲ አካባቢ ከ12 ዓመት በፊት በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ሙሉ ወጪ የተገነባው የምሥራቅ አፍሪካ ወጣቶች እግር ኳስ አካዴሚ አገልግሎት ሊጀምር ነው፡፡

ካፍ ኢትዮጵያን ጨምሮ በእግር ኳስ ልማት ወደ ኋላ ለቀሩ አባል አገሮች ከሚያደርገው የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ በተጨማሪ ታዳጊ ወጣቶች የሚፈሩባቸው የማዕከላት ግንባታ ያከናውናል፡፡ የዚህ ዕቅድ አካል ተደርጎ የሚጠቀሰውና በአዲስ አበባ ያስገነባው የምሥራቅ አፍሪካ ታዳጊ ወጣቶች የእግር ኳስ አካዴሚ ይጠቀሳል፡፡

ይሁንና የአካዴሚው ግንባታ በካፍ ሙሉ ወጪ የተሸነፈ ቢሆንም፣ ፕሮጀክቱ በታቀደለት ጊዜ ሊጠናቀቅ ባለመቻሉ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ድረስ ለአገልግሎት አልበቃም፡፡ የአካዴሚው ተጠሪነትም በሕግና በውል ተለይቶ ባለመቀመጡ የተነሳ፣ በአካዴሚው ቅጥር ግቢ ለተጨማሪ የማዘውተሪያ ግንባታ እንደሚውል ሲጠበቅ የነበረው ክፍት ቦታ፣ በአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን አማካይነት ‹‹ባለቤት አልባ ነው›› በሚል አጥሩ እንዲፈርስ የተደረገበት አጋጣሚ መደረጉ ተሰምቷል፡፡ ይሁንና ፈረሳው በመንግሥት ሰዎች ትዕዛዝ እንዲቆም መደረጉ የሚናገሩ አልጠፉም፡፡

በዚህ ሁኔታ ውስጥ የሚገኘውን ይህን የምሥራቅ አፍሪካ ታዳጊ ወጣቶች የእግር ኳስ አካዴሚ፣ ባለፈው ዓርብ ሰኔ 19 የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ሒሩት ካሳው (ዶ/ር)፣ የስፖርት ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዱቤ ጅሎ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ወጣቶች አካዴሚ ዋና ዳይሬክተር አቶ አምበሳው እንየው፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራና የሌሎች ተጠሪ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች ማዕከሉ የሚገኝበትን ሁኔታ ጎብኝተዋል፡፡    

ማንነታቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ምንጮች ለሪፖርተር እንደገለጹት ከሆነ፣ ምናልባትም ለዚህ ጉብኝት መነሻ የሆነው፣ ይህ በአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን አማካይነት የተጀመረው የአጥር ፈረሳ ጉዳይ በዋናነት ተጠቃሽ ነው፡፡

ለግንባታው መጓተት የፕሮጀክቱን የግንባታ ጨረታ ያሸነፈው ግብፃዊ ተቋራጭ የነበረ መሆኑን በመጥቀስ፣ ከግንባታ ጥራት ጋር በተያያዘ ተቋራጩ ግንባታ እንዲያቋርጥ ከተደረገ በኋላ ግንባታው ለሌላ ተቋራጭ ተላልፎ የተሰጠበት አካሔድም በራሱ ችግር ያለበት ነው በሚል ሲቀርቡ የነበሩ ቅሬታዎችን ሪፖርተር ሲዘግብ መቆየቱ አይዘነጋም፡፡

የተጠሪነት ወሰንን ጨምሮ በብዙ ችግሮች ተተብትቦ ‹‹በግንባታ ላይ ነው›› በሚል ከ12 ዓመት በላይ የዘገየው ይህ የካፍ አካዴሚ፣ ከሰሞኑ ጉብኝት በኋላ በቅርቡ አገልግሎት እንደሚጀምር ከስፖርት ኮሚሽን የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

አካዴሚው 42 ደረጃቸውን የጠበቁ መኝታ ክፍሎችን ጨምሮ አንድ ያለቀለት የእግር ኳስ ሜዳ ሲኖረው፣ ሁለተኛው ሜዳ ደግሞ ከሰሞኑ በአዲስ አበባ ስፖርት ኮሚሽን የአጥር ፈረሳ ዕርምጃ የተወሰደበት ክፍት ቦታ ይጠቀሳል፡፡ በተጨማሪም የተለያዩ ጅምናዚየሞች፣ የምግብ አዳራሾች፣ የልብስ ማጠቢያ ማሽኖችና መፀዳጃ ቤቶች፣ የስፖርተኞች ልብስ መቀየሪያ ክፍሎች ይኖሩታል ተብሏል፡፡  

 በጉብኝቱ ማጠቃለያ ላይ ሹማምንቱና ኃላፊዎቹ በአካዴሚው ቅጥር ግቢ ችግኝ ተክለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...