Tuesday, April 16, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የመድን ኢንዱስትሪው ከ11 ቢሊዮን ብር በላይ የዓረቦን ገቢ እንደሚያስመዘገብ ይጠበቃል

ተዛማጅ ፅሁፎች

የአውሮፕላን አደጋ ለመድን ድርጅት የአንድ ቢሊዮን ብር ገቢ አስገኝቷል

በዘጠኝ ወራት አፈጻጸሙ ከ9.3 ቢሊዮን ብር የዓረቦን ገቢ እንዳስመዘገበ የሚጠበቀው የኢትዮጵያ የመድን ኢንዱስትሪ፣ ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናት በቀሩት የሒሳብ ዓመት ውስጥ ከ11 ቢሊዮን ብር በላይ የዓረቦን ገቢ ሊሰበሰብ እንደሚችል ይጠበቃል፡፡

17ቱ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ባለፈው ሙሉ ዓመት እንቅስቃሴያቸው የ9.1 ቢሊዮን ብር የዓረቦን ገቢ ብቻ ማስገባታቸው ይታወሳል፡፡ በ2012 ዓ.ም. ዘጠኝ ወራት ውስጥ ያስመዘገቡት የዓረቦን ገቢም ከዓምናው ሙሉ የሒሳብ ዓመት ገቢ አብላጫ ይዞ ተገኝቷል፡፡

ይህ አፈጻጸም በሒሳብ ዓመቱ አራተኛ ሩብ ዓመት ሊያስመዘግቡ የሚችሉት ገቢ ከአንድ ቢሊዮን ብር ሊሆን በመገመቱ፣ ኢንዱስትሪው ለመጀመርያ ጊዜ 11 ቢሊዮን ብር የሚደርስ የዓረቦን ገቢ እንደሚሰበስብ ይጠበቃል፡፡

ይህ ሊሳካ እንደሚችል እምነት ያሳደረውም ዘንድሮ በዘጠኝ ወራት ብቻ የሰበሰበው የዓረቦን ገቢ፣ ከዓምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ27 በመቶ ዕድገት ማሳየቱና የኮሮና ወረርሽኝ ከባድ ሥጋት በደቀነበት ወቅት የአገሪቱ መድን ኩባንያዎች ግን ከሌላው ጊዜም የተሻለ ውጤት ማሳየት መቻላቸው ነው፡፡ በኢንዱስትሪው ይህን ያህል ከፍተኛ ዕድገት ያስመዘገበበት ወቅት እንደሌለ የዘርፉ ባለሙያዎች ይጠቅሳሉ፡፡ ሆኖም አንዳንዶች በአጋጣሚ የተገኘ ውጤት መሆኑን በማውሳት ወደፊት ፈታኝ ጊዜ ሊገጥማቸው እንደሚችል ሥጋታቸውን አንፀባርቀዋል፡፡

የመድን ድርጅቶቹ ዘንድሮ ያስመዘገቡት የዓረቦን ገቢ በዚህን ያህል መጠን  እንዲያድግ ካስቻሉ ዋነኛ ምክንያት መካከል የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በ42 ዓመታት ታሪኩ ከፍተኛ የተባለውን የዓረቦን ገቢ በግማሽ ዓመቱ ውስጥ ብቻ ማሰባሰብ መቻሉ አንዱ ነው፡፡ ከ17ቱ ኩባንያዎች መካከል የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በዘጠኝ ወራት ውስጥ ያስመዘገበው የዓረቦን ገቢ በ50 በመቶ ገደማ ማደጉ በአጠቃላይ የኢንዱስትሪውን የዓረቦን መጠን ገቢ ከሌላው ጊዜ የተሻለ እንዲሆን አድርጎታል፡፡

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት የዘጠኝ ወራት ሪፖርት እንደሚያሳየው፣ ከሕይወትና ሕይወት ነክ ከሆኑ የመድን አገልግሎቶች ያገኘው የዓረቦን ገቢ 4.41 ቢሊዮን ብር ነው፡፡ መድን ድርጅትን ጨምሮ ሁሉም ኩባንያዎች በዘጠኝ ወራት ውስጥ በድምሩ 9.31 ቢሊዮን ብር ዓረቦን ማሰባሰብ ችለዋል፡፡

መድን ድርጅት ያስመዘገበው የዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ49.7 በመቶ ወይም የ1.46 ቢሊዮን ብር ብልጫ አስመዝግቧል፡፡ 17ቱም ኩባንያዎች ያሰባሰቡት የዓረቦን መጠን ካለፈው ዓመት ዘጠኝ ወራት አፈጻጸም ጋር ሲነፃፀር የሁለት ቢሊዮን ብር ብልጫ አለው፡፡

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ከፍተኛ ዕድገት ላሳየበት የዓረቦን ገቢ ምክንያት ከሆኑት መካከል በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ላይ ለደረሰው አደጋ ከኢቪዬሽን ኢንዱስትሪ መድን ሽፋን ያገኘው ያልተጠበቀ የዓረቦን ገቢ ከቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኝ ስላገዘው እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

የዓረቦን መጠኑን 49.7 በመቶ ካሳደገው የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ባሻገር፣ ከፍተኛ ዕድገት በማስመዝገባቸው ከሚጠቀሱት የግል ድርጅቶች ውስጥ የሁለት የግል ኩባንያዎች ዕድገት የ35 በመቶ ድርሻ መያዝ መቻሉም ለዘርፉ ከፍተኛ ውጤት ተጠቃሽ ነው፡፡ ኢትዮ ላይፍ እንዲሁም ቡና ኢንሹራንስ ኩባንያዎች እያንዳንዳቸው የ35 በመቶ የገቢ ዕድገት አስመዝግበዋል፡፡

በኢንሹራንስ ኢንዱስትሪው በ2012 ዘጠኝ ወሮች ከሰበሰበው አጠቃላይ የዓረቦን መጠን ውስጥ 8.82 ቢሊዮን ብሩ ሕይወት ነክ ካልሆነ ኢንሹራንስ የተገኘ ሲሆን፣ 490 ሚሊዮን ብሩ ደግሞ ከሕይወት ኢንሹራንስ የተሰበሰበ መሆኑን ያመላክታል፡፡ ሕይወት ኢንሹራንስ ለብቻው 16 በመቶ ማደጉንም ያሳያል፡፡

ያነጋገርናቸው የኢንሹራንስ ባለሙያ በአሁኑ ወቅት የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪው ያስመዘገበው ውጤት እንዴት ሊታይ እንደሚችል ሲገለጽ፣ የዓረቦን ገቢው መጠነኛ ዕድገት ያሳየ መሆን ካለበት አንፃር ሲታይ ግን እንደ ዕድገት የሚታይ አለመሆኑ ነው፡፡

ኮሮና ቫይረስ ቢኖርም መጀመርያ ኢንሹራንስ ኢንዱስትሪ አድጓል ለማለት፣ ኢንሹራንስ የሚለካው የግብርና ኢንሹራንስና የሕይወት ኢንሹራንስ ዘርፍ ሲያድግ ነው፡፡

 ስለዚህ በግብርና የምትተዳደር አገር የግብርና ኢንሹራንስና የሕይወት ኢንሹራንስ ሲያድግ ነው ኢንዱስትሪ አደገ የሚባለው ብለዋል፡፡ ከዚሁ ጋር ተያይዞ አሁን ይጀመራል ተብሎ የሚጠበቀው የታካፉል ኢንሹራንስና የጋራ ኃላፊነት ኢንሹራንሶች ሲያድጉ ነው አጠቃላይ ኢንዱስትሪው አደገ የሚባለው፡፡

አሁን መጠነኛ ጭማሪ ያሳየው ዕድገት በተለያዩ መለኪያዎች እንለካው ከተባለ  ዕድገቱን የሚያሳይ አይደለም፡፡ ምክንያቱም የኢንሹራንስ ተደራሽነቱ አሁንም ገና ነው፡፡ የኢንሹራንስ ግንዛቤው ያልጨመረ በመሆኑና ሁሉ በአጋጣሚ ከጨመረው ዓረቦን ጋር ይያያዛል ብለው እንደ ምሳሌ የጠቀሱትም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካጋጠመው አደጋ ጋር ተያይዞ የተገኘ በመሆኑ፣ አጠቃላይ የኢንዱስትሪውን ዕድገት የሚያሳይና የፖሊሲን አቅጣጫ ጭምር የሚያስት ነው፡፡

መታወቅ ያለበት ኢንዱስትሪው ለዓመታት ያላደገው መዋቅራዊ ችግሮች ተለይተው እነሱ ላይ ባለመሠራቱና አሁንም መጠነኛ ለውጥ ስለታየ ብቻ አደጋ መባሉ አግባብ ያለመሆኑን እኝሁ ባለሙያ ጠቁመዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች